text
stringlengths
140
24k
summary
stringlengths
13
164
ለአመታት ሲንከባለል እንደቆየ የሚነገርለትን የሲዳማ ብሄር የክልልነት ጥያቄ ምላሽ የሚሰጠው የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ድምፅ አሰጣጥ ዛሬ ረቡእ ሀዳር አስር ቀን ሁለት ሺህ አመተ ምህረት በመላው ሲዳማ ዞን ይከናወናል። ከሁለት ነጥብ ሶስት ሚሊዮን በላይ መራጮች ድምፅ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ከተመሰረተ የመጀመርያው የክልልነት ህዝበ ውሳኔ የሆነው የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ውጤት በኋላ፣ የመጀመርያው አዲስ የፌዴራል መንግስቱ አባል ክልል ሊመሰረት ይችላል። የሲዳማ የክልልነት...
የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ድምፅ አሰጣጥ ዛሬ ይካሄዳል
አንድ መቶ ሰማኒያ አንድ በመጋቢት ሁለት ሺህ አስር የኢህአዴግ አመራር ለውጥ የፌደራል መንግስት ሚናውን ተነጥቆ መቀሌ የመሸገው የህወሀት አመራር ምን እያሰበ ነው ምን እያደረገ ነው በፖለቲካ ሚናው የት ላይ ነው የሽብር እቅዶቹስ ምንድን ናቸው በሚሉት አንኳር ጉዳዮች ላይ የሚከተለው የተረጋገጠ መረጃ አለ ዋና አላማ ተብለው የተያዙት ሁለት እቅዶች ሲሆኑ ዝርዝርና ሁለገብ ጉዳዮች ላይ የሚተገበሩ አቢይ ስትራቴጂዎችም አሉ። እቅድ አንድ በስልጣን ላይ ያለውን ቡድን አስወግዶ በብሄር ብሄረሰቦች ...
ህወሀት ምን እያሰበ ነው ሙሏለም ገብረመድህን
የኮቪድ ወረርሽኝን ለመግታት በኢትዮጵያ የ እንድናገለግልዎ ማስክዎን ያድርጉ ንቅናቄ በትምህርት ቤቶች እንደሚካሄድ የትምህርትና የጤና ሚኒስቴሮች አስታወቁ። የእንድናገለግልዎ ማስክዎን ያድርጉ ንቅናቄ እንደሚካሄድ የገለፁት የትምህርት ሚኒስትር ጌታሁን መኩሪያ ዶክተር እና የጤና ሚኒስትር ሊያ ታደሰ ዶክተር ጥር ቀን ሁለት ሺህ አመተ ምህረት በጋራ በሰጡት መግለጫ፣ ንቅናቄው የሚካሄደው ማክሰኞ ጥር ሀያ አምስት ቀን ነው። በሁሉም የትምህርት ተቋሞች የሚገኙ ተማሪዎችና አስተማሪዎች ሁሉም ማስክ በማድረግ በትምህ...
የ እንድናገለግልዎ ማስክዎን ያድርጉ ንቅናቄ በትምህርት ቤቶች ሊካሄድ ነው
አዲስ አበባ ፣ ሀምሌ ሁለት፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ አንድ ሺህ አራት መቶ አርባ ሶስትኛው የኢድ አል አድሀ አረፋ በአል በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በበዩ ልዩ ሀይማኖታዊ ክዋኔዎች ተከብሯል። በድሬዳዋ አየር መንገድ አካባቢ በሚገኘው የኢድ መስገጃ ሜዳ የተከበረው የአረፋ በአል ላይ በብዙ ሺህ የሚገመቱ የገጠርና የከተማ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ተሳትፈዋል። በበአሉ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ ወርሰሜ እና የካቢኔ አባላት፣ የየመስጅዱ ኢማሞች፣ ኡላማዎች እና ሼሆች ተሳታፊ ሆነዋል። ...
አንድ ሺህ አራት መቶ አርባ ሶስትኛው የኢድ አል አድሀ አረፋ በአል በድሬዳዋ በልዩ ልዩ ሀይማኖታዊ ክዋኔዎች ተከበረ
ታመመ ቢሏቸው አንበሳ ባለበት ሊጠይቁት ሄዱ የምድር ሁሉ አራዊትይሄንኑ ሰምታ የጦጣ ብልጣ ብልጥ ሳትጠይቀው ቀረች ሳትገባ ወደ ውስጥ ለምን ብለው ቢሏት መለሰች ጦጢቷ የገቡት ሳይወጡ ጉዱ ሳይጣራ ቀኑም ሆነ ሌቱ እንዴት ብዬ እጄን ልስጥ እስከ ማእሌቱ አራዊቱ ለአንበሳ ያላቸው ክብር እጅግ ድንቅ ነው። ሲታመም እጅግ አሳሰባቸው እንጂ ይሄ ጉልበተኛ በቃ እጁን ይሰጠናል ብለው አሰቡ። አያ አንበሶ ግን ይብሱን ጉልበት አፈራና ፈረጠመ። አራዊቱም በጣም ፈሩት። ከዚያም በሁለት ተከፈሉ።አንደኞቹ፡ ምነው እንዳመመ...
አስራ ስድስቱን ዝንጀሮዎች ባንድ ጥይት ሰፋኋቸው ቢለው፤ እኔን የገረመኝ ያንተ አገር ዝንጀሮዎች አሰላለፍ ነው አለው
ኢሳት ጥቅምት በመዲናይቱ አዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ የአገልግሎት ስራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ የንግድ ድርጅቶች በኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ ምክንያት ኪሳራ እየደረሰባቸው መሆኑን አስታወቁ።የእንግዶች መቀነስ ከተጠበቀው በላይ እየሆነ መምጣቱን የገለፁት የሆቴል ተቋማት የኢንተርኔት አገልግሎት እልባት ባለማግኘቱ ኪሳራን እያደረሰባቸው እንደሆነ ገልፀዋል።ጉዳዩ የሚመለከተው የመንግስት አካል በተለይ የሆቴል ድርጅቶች እየደረሰባቸው ያለውን ኪሳራን ግምት ውስጥ በማስገባት በግብር ክፍያቸው ላይ ማስተካከያን እ...
የንግድ ድርጅቶች በኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ ምክንያት ኪሳራ እየደረሰባቸው መሆኑ ተገለፀ
በድሀረ ምርጫ ዘጠና ሰባት ተከስቶ በነበረው ውዝግብ ምክንያት በተለየ የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ሲከናወኑ፣ የነበሩት የአዲስ አበባና የድሬዳዋ ከተሞች ምክር ቤቶች ምርጫዎችና የአካባቢ ምርጫዎች፣ ከመጪው አመት ጀምሮ የኢትዮጵያ ምርጫ በቦርድ በሚያዘጋጀው ጠቅላላ ምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ከ አመታት ቆይታ በኋላ እንዲከናወኑ ተወሰነ። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ረቡእ ሀምሌ ሀያ አራት ቀን ሁለት ሺህ አመተ ምህረት ባካሄደው የአራተኛ አመት የስራ ዘመን ሁለተኛ አስቸኳይ ስብሰባ፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ለምክር ...
የአዲስ አበባና የድሬዳዋ ምክር ቤቶች ምርጫ ከ አመታት ቆይታ በኋላ ከአጠቃላይ ምርጫ ጋር እንዲካሄድ ተወሰነ
በተስፋዬ ወልደ ዮሀንስ ሀይሌ ትንሽ ቦታ ብንጣላ መታረቂያ ብንታረቅ ለመጣያ ብንታሰር ይቅር ማያ ይቅር ብንል መታሰሪያ ትንሽ እንተው ባዶ ቦታ። ጥግ ድረስ የለም ስራ፣ ጥግ ድረስ የለም ፋታ። በልባችን ደግ በኩል፣ እንፈልግ ባዶ ቦታ የጳጉሜ አይነት ትንሽ ቦታ ለዘመን መለዋወጫ። ነብይ መኮንን የሚያልፍ አይመስልም ያልነውም፣ መስከረም ብለን የጀመርነውን አመት አገባደን በቁጥር አሻግረን ለሌላ አምላክ ቢፈቅድና ብንኖር ብለን ለምናስበው ሌላ መስከረም አሻግሮ ሊያስረክበን የቀናት ቆይታ ብ...
የአዲስ አመት ምኞት ለለውጥ ፈላጊ አገር
በቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት አውቶማቲክ የአየር ጠባይ መመዝገቢያ መሳሪያዎች ተከላ በ ሚሊዮን ብር እያካሄደ መሆኑን ብሄራዊ ሚቲዎሮሎጂ አስታወቀ። በአለም አቀፍ ደረጃ በየአመቱ መጋቢት ቀን የሚከበረውን የሚቲዎሮሎጂ ቀን ምክንያት በማድረግ ባለፈው ሰኞ በአዳማ ከተማ በተካሄደ መርሀ ግብር ላይ ነው፣ የብሄራዊ ሚቲዎሮሎጂ ዋና ዳይሬክተር አቶ ፈጠነ ተሾመ ይህን የገለፁት። በአፍሪካ ቀዳሚ የሆነውን የኢትዮጵያ አየር መንገድን የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ፣ ከበረራ ጋር ተያያዥነት ያላቸው መስሪያ ቤቶች በተሻለ ፍጥነ...
ብሄራዊ ሚቲዎሮሎጂ በ ሚሊዮን ብር የዘመናዊ መሳሪያዎች ተከላ እያካሄደ ነው
ለተስፋዬ እድል መስጠት ሬዲዮ መሆን ነው የኢትዮጵያ ስም ሲጠራ፣ ከፍ ከፍ ሲል የዘር ወባው የሚነሳበት ተስፋዬ ገብረ አብ አሜሪካ ገብቶ የሚያናግረው ሚዲያ በማጣቱ በሚዲያ ረሀብ እየተሰቃየ መሆኑ ተሰምቷል። በክፉም ይሁን በመልካም ከሚዲያ መገለል የማይወደው ተስፋዬ ሻእቢያን የሚያጋልጥ መፅሀፍ ፅፌአለሁና አናግሩኝ እያለ በዳያስፖራ ያሉትን ሚዲያ እየለመነ፣ በራቸውን እያንኳኳ መሆኑ ተነግሯል በተለይ የተንቀሳቃሽ ምስልና የሬዲዮን። ዛጎል እንደዘገበው ከሆነ እስካሁን እድሉን የሰጠው የለም። ተስፋዬ ከ...
ተስፋዬ ገብረ አብ የሚዲያ ያለህ እያለ ነው
ሚያዚያ ፯ ሰባት ቀን ፳፻፮ አመተ ምህረት ኢሳት ዜና የኢትዮጵያ ምርጥ ዘር ድርጅት እንዳስታወቀው ባለፉት አመታት ለአርሶደሩ የቀረቡ የምርጥ ዘር ማሻሻያ ዝርያዎች የመብቀልና ምርት የማፍራት ችግር ገጥሞአቸዋል። በዚህም የተነሳ በየአመቱ ከአንድ መቶ ሀምሳ ሺ ኩንታል በላይ ምርጥ ዘር ለብክነት እየተዳረገ ነው። በዚህ አመት ብቻ ሀያ አምስት ሺ ዘጠና ሰባት ኩንታል ምርት ዘር ባክኖ መቅረቱን ድርጅቱ አስታውቋል። በየአመቱ ጥራታቸውን ያልጠበቁ ዝርያዎች ያለአግባብ እየቀረቡ ከሁለትአሽ ሄከታር በላይ መሬት ተገ...
በምርጥ ዘር ጥራት መጓደል ምክንያት ከፍተኛ ሀብት እየባከነ ነው ተባለ
የእስራኤል መንግስት በአስር ሺህዎች ለሚቆጠሩ አፍሪካዊያን ስደተኞች ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ካልሆንም እስር እንደሚጠብቃቸው ማስጠንቀቂያ አውጥቷል። ስደተኞቹ እሰራኤልን በሚቀጥሉት ሶስት ወራት ውስጥ ለቀው ለመውጣት ከተስማሙ ሶስት ሺህ አምስት መቶ ዶላር ይሰጣቸዋል ተብሏል። በአማራጭነትም ወደሀገራቸው ካልሆነም ወደሌላ ሶስተኛ ሀገር የመሄድ ምርጫም ቀርቦርላቸዋል። ነገር ግን ከቀነገደቡ በኋላ እስራኤል ውስጥ ለመቆየት ከወሰኑ ከሚያዚያ ወር ጀምሮ ስደተኞቹን ማሰር እንደሚጀምሩ ባለስልጣናቱ አስጠንቅቀዋል። ...
እስራኤል አፍሪካዊያን ስደተኞች እንዲወጡ አዘዘች