doc_id
stringlengths
1
5
text
stringlengths
42
393k
118
እምዬ ምኒልክ የጥቁሮች አባት ወርኃ የካቲት ብቅ ሲል አፍሪካዊው ጀግና የጥቁሮች አባት እምዬ ምኒልክ ይታወሱኛል። የአፄ ምኒልክ ታላቅ ገድል አይወሳ Vs በታሪካዊ መገፋፋት የተፈጠረው አነስተኛ ቁርቁስ አይነሳ የሚሉ አይመቹኝም። ምክንያቱም አጤ ምኒልክ የአማራ ወይም የኦሮሞ የብቻ ሳይሆኑ የኢትዮጵያ መሪ ነበሩና። የጉንጭ አልፋው ክርክር መነሻ ይገርማል። ዛሬ አፄ ምኒልክ አጠፉ ብለን ብንወስድ፦ ማን ይከሰስ ማን ይካስ ዳኛው ማነው የሚቀጣውስ መልሱ ማንም፤ ተጠያቂው ዘመን ወቅት ነው። አልገባንም እንጂ ...
119
ምኒልክን አለማወቅ ይቻላል ግን የመጀመሪያውን ባቡር፣ የቀደመውን መኪና፣ አንድ ብሎ የጀመረውን አስኳላ ማወቅ ምኒልክን ማወቅ ነው፡፡ ነጭና ጥቁር እኩል ነው ብሎ ማመን፣ ጥቁር ነጭን ድል እንዳደረገ መስማት፣ የመጀመሪያው ሆስፒታል ሪፈር ተጽፎ መምጣት ምኒልክን ማወቅ ነው፡፡ ከሄኖክ ስዩም በድሬቲዩብ ሰሞኑን አንድ ሰው ምኒልክን አላውቅም አለ ተብሎ እዚሁ መንደር ከዚህም ከዚያም የሚባለውን አደመጥሁ፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ባለች ከዛሬዋ ይልቅ በትናንትናዋ በምትመካ ሀገር ምኒልክን አለማወቅ ብዙ አይገር...
120
ባልና ሚስት ከአንድ ወንዝ ይቀዳሉን እንጂ በተመሳሳይ ቀን ይወለዳሉንስ አልሰማንም ነበር የመድኃኒት ጥቂት ይበቃል እያለች፤ የምኒልክ እናት አንድ ወልዳ መከነች፡፡ ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 112011 ዓም አብመድ ንጉሠ ነገሥት ከንግሥት፤ እምዬ ምኒልክ ከእቴጌ ጣይቱ፤ ርሀቤ ምኒሊክ ከብርሃን ዘ ኢትዮጵያ ጣይቱ፤ በአራት ዓመታት ልዩነት ነሐሴ 12 ቀን 1836 እና ነሐሴ 12 ቀን 1832 ዓም ሚስት እና ባል በቅደም ተከተል ከኢትዮጵያ ምድር ፈለቁ፡፡ በኢትዮጵያውያን ወግና ባሕል ብዙም ባልተለመደ መልኩ ሚስት ባል...
121
‹‹እምዬ ምኒልክ ለጣልያን ምርኮኞች ለበሽታቸው መድኃኒት፣ ለርሀባቸው ጉርስ ሆነዋል፡፡›› የታሪክ ተመራማሪ ባሕር ዳር፡ የካቲት 212011 ዓምአብመድ ለሰዓታት የዘለቀው የፋሺስትና የኢትዮጰያውያን ከባድ ጦርነት ተጠናቅቋል፡፡ ዓለም ልታምነው ያልፈለገችውን መራራ እውነት በግድ ተግታለች፡፡ አምሳለ ሰው ነጭም ጥቁርም እንደሆነ በበላይነት ማሳየት በሚያስፈልገው ዓለም ሁለት ክፍለ ዘመናትን ቢወስድም በጣልያኖች እጅ መንሳት ከ123 ዓመታት በፊት እውን ሁኗል፡፡ ‹‹ከእንግዲህ ብሞትም ሞት የሁሉም ነውና ስለእኔ ...
122
ዳግማዊ ምኒልክ ዳግማዊ ምኒልክ «ማንም ሰው ለመማርና ለመሠልጠን መድከም አለበት።» በ፲፰፻፺፰ ዓም ስለትምሕርት ያስነገሩት አዋጅ ደ ጃዝማች ምኒልክ መቅደላ ላይ ከባድ ዝናብ ጥሎ ባደረበት ሰኔ ፳፬ ቀን ፲፰፻፶፯ ዓም በ’ቆቂት በር’ ከሃያ ተከታዮቻቸው እና ከእናታቸው ከወይዘሮ እጅጋየሁ ጋር አምልጠው ወደአባታቸው ወዳጅ ወደ ወሎዋ ገዥ ወይዘሮ ወርቂት አመሩ። ሆኖም ወይዘሮ ወርቂት በቴዎድሮስ እጅ ወድቆ የነበረውን ልጃቸውን አመዴ አሊ ሊበንን ማስፈቻ ይሆነኛል በሚል ምኒልክን እና ተከታዮቻቸውን በእስር ይዘ...
123
«ማንም ሰው ለመማርና ለመሠልጠን መድከም አለበት።» በ፲፰፻፺፰ ዓም ዳግማዊ አጤ ሚኒሊክ ስለትምሕርት ያስነገሩት አዋጅ ነው፡፡ ዝክረ ንጉሰነገስት ዳግማዊ አጤ ሚኒሊክ ንጉሰነገስት ዳግማዊ አጤ ሚኒሊክ ልክ በዛሬው ቀን ታህሳስ ፫ ነበር እረፍተ ሞታቸው የተሰማው፡፡ «ማንም ሰው ለመማርና ለመሠልጠን መድከም አለበት።» በ፲፰፻፺፰ ዓም ዳግማዊ አጤ ሚኒሊክ ስለትምሕርት ያስነገሩት አዋጅ ነው፡፡ «እናንተ አንድ ልብ ከሆናችሁ በምቀኝነት እርስ በርሳችሁ ተዋግታችሁ ካላለቃችሁ በቀር ኢትዮጵያን አገራችንን ለሌላ ለባ...
124
አፄ ምንሊክ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የፈፀሟቸው አምስት ለማመን የሚከብዱ ዘግናኝ ታሪካዊ ወንጀሎች ስለ አፄ ምንሊክ ብዙ ግዜ ጥሩ ጥሩ ነገሮችን ፅፊያለሁ። ነገር ግን ታሪክን ታሪክ የሚያሰኘው ጥሩውንም መጥፎውንም ስናውቅ ነውና አፄ ምንሊክ ከሰሩት ጥሩ ነገር ባሻገር የሰሩትን አምስት ታሪካዊ ጥፋቶች ደግሞ እንደሚከተለው በአጭሩ አስቀምጣለሁ። 1ኛ በዘር ተከፋፍሎ እርስ በእርሱ በፍቅር እየተዋጋና በሰላም እየተገዳደለ ሲኖር የነበረውን ጨዋ ህዝብ በግድ አንድ ሁን ብለው መንግስት መስረተው ያለ ፍላጎቱ በሰላ...
86
አፄ ምኒልክ ደም መፈሰስን እናስቀር ብለው ንጉሥ ጦናን ለመኑት። ንጉሥ ጦና ግን ኃይሉን አሟጦ መዋጋት ስለመረጠ በምኒልክ ሠራዊት ላይ ከባድ ጉዳት አደረሰ። በመጨረሻ ግን ቆሰለና ተማረከ። ዳግማዊ ምኒልክ ጦናን አይቀጡ ቅጣት ከመቅጣትና መንግስቱንም አሽቀንጥረው ጥለው ሥልጣኑን ለጦር መሪዎቻቸው ከመስጠት ይልቅ ደግነት የተሞላበት ምህረት አድርገውለት እንደሚገብርላቸው ቃል ካስገቡት በኃላ ወደ ሥልጣኑ መለሱት። ምኒልክ ተበቃይ አልነበሩም። ይቅር ባይ፣ በተጨባጭ እውነታ ላይ የተመሰረተ ምክንያታዊ አስተሳሰብ ...
87
የዳግማዊ ምኒልክ የክተት አዋጅ ከወራሪዎቹ እንቅስቃሴ አንፃር ከተጠበቀበት ወቅት ዘግይቷል፡፡ ይህም በአፍሪካና አውሮፓ ሀገሮች አይን ምንሊክን እንደ ፈሪ እንዲታዩ አድርጎ ነበር ይላል ራይሞን ጆንስ የአድዋ ጦርነት በሚለው መፅሀፉ፡፡ ፀሀፊው ሲቀጥል የመሪ ብልህነት የሚለካው ቸኩሎ በመወሰኑ ሳይሆን በወቅቱ ያሉትን አመቺ ሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ ውሳኔ ሲያሳልፍ ነው ይላል፡፡ የክተት አዋጁ በራሱ በወቅቱ ኢትዮጵያ የነበረችበትን የፈተና ጊዜ ማለፍንና የመረጋጋት ዘመን መምጣቱን ገላጭ ከመሆኑም በላይ፤ ህዝቡ...
88
‹‹አጼ ምኒሊክን ልክ እንደ አባቴ ነው የምወዳቸው።›› ስዊዘርላንዳዊው ቢትወደድ ባሕር ዳር፡ የካቲት 222011 ዓምአብመድ ቢትወድድ አልፈርድ ኢልግ፡ ያልተዘመረለት የኢትዮጵያ ባለውለታ ዳግማዊ ዓፄ ምኒሊክ በልጅነታቸው ከዓፄ ቴዎድሮስ ጋር አንደመቆየታቸው ቴዎድሮስ አውሮፓውያን ወንጌላውያንን መድፍ እና መሣሪያ እንዲሠሩላቸው ሲያግባቡ በደንብ ያስተውሉ ነበር ይላሉ ፕሮፍሰር ሪቻርድ ፓንክረስት በጽሑፋቸው፡፡ ከዓመታት በኋላ የሸዋ ንጉሥ ሲሆኑ አውሮፓውያን ባለሙያዎች ወደ ሀገራቸው እንዲመጡላቸው ጥረት ያደርጉ...
89
የአጤ ምኒልክን ስም እንዳትጠራ ይቅርብህ አጤ ምኒልክ ከ100 አመት በፊት ስለ ልዩ ሀገር የሰራ ታላቅ ሰው ነው፣ ዛሬ ከመቶ አመት በኋላ የአህጉር ከተማ ላይ አንተ ስለ ግልህ ልዩ ጥቅም ትሰራለህ አጤ ምኒልክ ተቀናቃኝ ንጉሶችን በጦርነት አሸንፎ ወዳጆቹ የሚያደርግ የድሮ ዘመን እጅግ ዘመናዊ ሰው ነው። አጤ ምኒልክ ሊገድሉት ፈልገው ቆስለው የተያዙ ተቀናቃኞቹን እንደ ልጆቹ ቁስላቸውን አጥቦ ያዳነ ሩህሩህ ሰው ነው፣ ዘመናዊ ሰው ነው። በአንተ ዘመን በቀደም ከተደረገው ጋር አታወዳድረውም። ሰሞኑን ጠቅላይ ሚ...
90
የንጉሱ ህልፈት በኩር እኒያ የጥቁር እንቁ፣ የጀግንነት መስፈሪያ፣ የስልጣኔ በር ከፋች… እምዬ ምኒልክ ያረፉት በወርሀ ታህሳስ 031906 ዓም ነው የንጉሱ አሟሟት ዛሬም ድረስ አወዛጋቢነት ያልተለየው ሆኖ ቀጥሏል ደራሲና ጋዜጠኛ ጳውሎስ ኞኞ ስለ አፄ ምኒልክ አሟሟት ሲጽፉ፣ “ንጉሱ የሞቱት መድኃኒት ተደርጐባቸው ነው” የሚል ወሬ እንደነበር አስፍረዋል ይህ ወሬም በወቅቱ ከፍተኛ ውይይቶች ክርክር አስነስቶ እንደነበር ጽፈዋል ከዚህ ሀሣብ በተለዬ ደግሞ ንጉሱን የደም ብዛት ለከፋ ችግር እንደዳረጋቸው የሚገልፁ...
91
እምየ ሚኒልክ ደጉ ንጉስ የኢትዮጵያ የብርሀን ንጉስ እምየ ሚኒልክ የአደዋን ጦርነት በድል ከደመደሙ በኃላ የተናገሩት ፦ በጥጋባቸው አድዋ ላይ ተዋግተው ድል ሆኑ እኔ ግን ከድንቁርናቸው ብዛት የእነዚያን ሁሉ ክርስትያን ደም በከንቱ መፍሰሱን እያየሁ ድል አደረኳቸው ብየ ደስ አይለኝም ብለው ነበር ። እምዬ ምንሊክ እንኳን የወገናቸው ጡት ሊቆርጡ ቀርቶ ጣልያንን እንኳን ማርከው ሳይገርፏቸው እንደ እናት አብልተው አጠጥተው እንዳይለምዳችሁ ይቅር ብለው የፈቱ የእናት ልብ ያላቸው ጀግና ሩሩህ ይቅር ባይ እና...
92
እምዬ ምኒልክን ለመሳደብ መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች። ★★★ • ደግሞ SHARE አድርጉትና አሰድቡኝ አሏችሁ። ETHIOPIA የወዳጅ ምክር ነው። ጫ ብለህ ስማኝ። ምክሬንም ተጠቀምበት። ••• አንዳንድ ሰሞንቴ የሆኑ የአክራሪው የወሐቢያ ርዝራዦችና ፀረ ምኒሊክ ኃይሎች ምንም ይባል ምንም ዘለው ምኒልክን ለመርገም መንጠራራታቸውን ባየሁ ጊዜ ምኒልክን ለመስደብ ሟሟላት ያለባቸውን ነገር ልነግራቸው በመውደዴ ይህችን ቀበርቾ የመሰለች ጦማር ጣፍኩላቸው። ተጠቀሙበት በሉልኝ። ••• ወዳጄ ምኒልክን ለመርገም፣...
93
ዳግማዊ ምኒልክ Jump to navigationJump to search ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ Menelik II 4jpg ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ግዛት ከጥቅምት ፳፭ ቀን ፲፰፻፹፪ ዓም እስከ ታኅሣሥ ፫ ቀን ፲፱፻፮ ዓም በዓለ ንግሥ ጥቅምት ፳፭ ቀን ፲፰፻፹፪ ዓም ቀዳሚ ዓፄ ዮሐንስ ፬ኛ ተከታይ ልጅ ኢያሱ ንጉሠ ሸዋ ግዛት ከነሐሴ ፳፬ ቀን ፲፰፻፶፯ ዓም እስከ ፲፰፻፹፪ ዓም ቀዳሚ ንጉሥ ኃይለ መለኮት ሣህለ ሥላሴ ተከታይ የለም ባለቤት አልጣሽ ቴዎድሮስ ባፈና ጋትቸው እቴጌ ጣይቱ ልጆች ሸዋረጋ ምኒልክ ል...
94
የቀድሞው የአሜሪካ ፕረዘዳንት ጆንኦፍ ኬኔዲ በምድር ላይ ጀግና ጥራ ብትሉኝ ቀድሜ ምጠራው የንጉስ ሚኒሊክን ነው ደርባባና ደፋር ናቸው። የነጭ ቅኝ ገዥን በአፍሪካ ምድር ያንበረከኩ ቆራጥ ሰው ። ኢትዮጵያውያን ጀግንነታቸው የመነጨው ከሌላ ሚስጥር አይደለም ከሚኒሊክ ነው። ለዚህም አገሬ አሜሪካ በክብር እዚህ ድረስ ታሪካቸውን በሙዚየም አስቀምጣለች በማለት ገልፀዋቸው ነበር። የፈረንሳዊ የቀድሞው መሪ ዣክ ሽራክየት አለ ጀግና ለዛውም በአፍሪካ ምድር ከንጉስ ሚኒሊክ በላይ በማለት ዘክረዋቸው ነበር። የሊቢ...
95
ስለ ታላቁ አጤ ምኒልክ በውጭ ሀገር ዜጎች የተሰጡ አስተያየቶች፦ የማያውቁትን ነገር ሁሉ ማየት፥ማጥናትና መስራት ይወዳሉ።ሮድ ምኒልክ የሀይለኝነት ጠባይ አላቸው። አሳባቸውም በመልካም ሁኔታ እያስተዳደሩ የአገራቸውን ዕድገት ለማፋጠን ነው። ምኒልክ የተከበሩ በጣም ትልቅ ሰው ናቸው።ግሊክን ታዋቂነታቸው በፓለቲካ ብቻ አይደለም። የሳይንስ ውጤት በሆኑ ጥበባዊ ስራዎችም እውቅ ናቸው። ግሊከን ምኒልክ ሲያጫውቱኝ ወጣቶቻችን መማር ይኖርባቸዋል።ገና ብዙ የሚሰራ ስራ አለን። በጣም ወደ ኋላ የቀረን ህዝቦች ነን።አሉኝ...
96
ዳግማዊ አጤ ምኒልክ ከጳውሎስ ኞኞ የመጀመሪያው መጽሐፍ የካቲት 1984 ዓም ምኒልክ በ1836 ዓም ነሐሴ 12 ቀን ቅዳሜ ዕለት ተወለዱ። አባታቸው ኃይለ መለኮት ሣህለሥላሴ ሲሆኑ እናታቸው ወይዘሮ እጅጋየሁ ለማ አዲያሞ ይባላሉ። የምኒልክ እናት ወይዘሮ እጅጋየሁ የንጉስ ሣህለሥላሴ ሚስት የወይዘሮ በዛብሽ ገረድና የልጆች ሞግዚት ነበሩ። እጅጋየሁ የግርድና ሥራ የጀመሩት በንጉሥ ሣህለ ሥላሴ ቤት አልነበረም። ንጉሥ ሣህለ ሥላሴ ቤት ከመቀጠራቸው በፊት የአንኮበር ቤተ ክርስቲያን አለቃ የነበሩት የመምህር ምላት ...
97
የትምክህት እና የነፍጠኝነት ጋብቻ አድዋን ወለደ፡፡ የካቲት 23 ቀን 2010 ዓም ተፃፈ፡፡ ንጉሱ ገና የ 20 ዓመት ጎረምሳ ሆኖ የገናናውን የዳግማዊ ቴዎድሮስ ልጅ ወይዘሮ አልጣሽን አገቡ፡፡ደጃዝማች የሚል ማዕረግም ተደረጎታቸው፡፡ምርኮኛ ቢሆኑም መይሳው ብልህነታቸውን አይተው በቤተመንግስታቸው አነገሷቸው፡፡ ደጃዝማች ምኒሊክ ግን ከቴዎድሮስ እልፍኝ ወጥቶ ሸፈተ፡፡ ባለቤቱን ትቶ ከቴዎድሮስ አምልጦ ራሱ ቴዎድሮስ ሆነ፡፡ ምኒሊክ ያለቃ ፊት ሲቀላ እና ሲፈካ የሚሸበር እና የሚደሰት አጎብዳጅ አልነበረም፡፡በራሱ...
98
ዛሬ የጥቁሮች ዋልታና መከታ ያረፉበት ቀን ነው፤ በጨረፍታ እንዘክራቸው፡፡ ባሕር ዳር፡ ታኅሳስ 032012ዓም አብመድ ‹‹ምኒልክ መጓዙን የምትጠይቁኝ፣ ፊትም አላለፈ ኋላም አይገኝ፡፡›› ጀግኖች ያከብሯቸዋል፤ ፈሪዎች ይፈሯቸዋል፤ ይጠሏቸዋልም፤ ብልሆች በብልህነታቸው እየተደነቁ ሥራቸውን ከፍ ያደርጋሉ፡፡ ታሪክ የሚያውቅና ታሪክ ለመሥራት የሚቋምጥ ሁሉ ይኮራባቸዋል፤ እምዬ ምኒልክ፡፡ ዘራቸው ከነገሥታት፣ ከመኳንንትና ከመሳፍንት ይመዘዛል፡፡ አባታቸው ንጉሥ ናቸው፡፡ ከመወለዳቸው በፊት በእናታቸው ራዕይ ታይ...
99
ዘመን ቢለወጥ ወቅት ቢፈራረቅ ዘመን የሚሻገሩ የዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ ታሪካዊ ንግግሮች በጥቂቱ ➶ ሰው ሁሉ እኩል ስለሆነ ማንም ሰው ሰውን ባሪያ አይበል ። ➶ ሁሉም ሰው በየኃይማኖቱ ይደር ። ➶ ድኻ እወደደበት ቦታ ይቀመጥ ። በዘር ፣ በወገን ልዩነት አይከልከል ። ➶ የመሬት ጥያቄ ላቀረቡ የውጭ አገር ሰዎች ንጉሡ የሰጡት መልስ፡ ‹‹ የኛ አገር ፍትሐ ነገሥት ልዑሎች መሬት ይሽጡ አይልም ። ያገሬ መሬት ባለቤቱ ሌላ ነው ። ከአባቶቻቸው እየተቀበሉ ያቆዩት መሬት ነው ። መሬቱ የሁሉም ስለሆነ አይሸጥም ።...
125
የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ለተፈጠረው ችግር መፍትሄው ነጻነትን ማስፋትእና ሁሉን አቀፍ ውይይት መደረግ ሲችል ነው አሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቲሊርሰን እንዳሉት በኢትዮጵያ እየተደረገ ያለውን ስልጣንን የማሸጋገር ሂደት እንደግፈዋለን ያሉት ባለስልጣኑ፣ አሜሪካ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በጥብቅ መቃወሙዋንም ገልጸዋል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የዜጎችን መብት እንደሚገድብ በተለይም ሃሳብን የመግለጽ ነጻነትን እንደሚያፍን ለኢትዮጵያ ባለስልጣናት እንደገለጹላቸው ሚኒስትሩ ተናግረዋል። የጸጥታ ሃይሎች...
126
ለ6 ወር የሚተገበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በህዝብ ተወካዮች ምቤት በ23ኛ ድምፅ የፀደቀ ሲሆን የአዋጁን ድንጋጌዎች ተላልፎ የተገኘ እስከ 5 ዓመት በሚደርስ እስራት ይቀጣል ተብሏል፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በ346 ድጋፍ፣በ88 ተቃውሞና በ7 ድምጸ ተአቅቦ ጸድቋል ተብሎ ነበር፡፡ ሆኖም በኋላ ላይ በተሰጠው መግለጫ፤አዋጁ በ395 የድጋፍ ድምጽ ጸድቋል በሚል ተስተካክሏል፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የተቃወሙት በአብዛኛው የኦሮሚያ ክልል ተመራጭ የፓርላማ አባላት መሆናቸውም ታውቋል፡፡ ጠቅላይ አቃቤ ህግ...
127
ራሱን ኮማንድ ፖስት ብሎ የሚጠራው ቡድን በኦሮምያ ክልል አመራሮች ላይ እርምጃ እየወሰደ ነው ኢሳት ዜና የካቲት 29 ቀን 2010 ዓም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ሰበብ በማድረግ ራሱን ኮማንድ ፖስት ብሎ የሚጠራው ቡድን በኦሮምያ ክልል ፖሊሶችና አመራሮች ላይ የሚወስደውን እርምጃ ቀጥሎበታል። እርምጃው በኦህዴድ ላይ ከፍተኛ አደጋ ደቅኖበታል። በአዲስ አበባ ዙሪያ በሚገኙ በተለይን በለገጣፎ አካባቢ ተመድበው ይሰሩ የነበሩ የኦሮምያ ፖሊስ አባላት ምሽት ላይ በድንገት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን፣ በወረዳው ውስጥ በ...
128
ኢሳት ዲሲ–የካቲት 272010 በኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከተደነገገና ተግባራዊ ከሆነ በኋላ የሃገሪቱ ሰላምና አንድነት በአሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ኦፌኮገለጸ። ኦፌኮ በሃገሪቱ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ባወጣው መግለጫ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተደነገገበት ሁኔታና የጸደቀበት መንገድ ሕገወጥ በመሆኑ አንቀበለውም ብሏል። አዋጁ ሕገመንግስቱን በጣሰ መልኩ የተፈጸመ በመሆኑም ጉዳዩን ለሚመለከተው የሕግ አካል ለማቅረብ መዘጋጀቱንም ኦፌኮ ገልጿል። የኦፌኮ መግለጫ እንደሚያመለክተው ከ...
129
የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ለተፈጠረው ችግር መፍትሄው ነጻነትን ማስፋትእና ሁሉን አቀፍ ውይይት መደረግ ሲችል ነው አሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቲሊርሰን እንዳሉት በኢትዮጵያ እየተደረገ ያለውን ስልጣንን የማሸጋገር ሂደት እንደግፈዋለን ያሉት ባለስልጣኑ፣ አሜሪካ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በጥብቅ መቃወሙዋንም ገልጸዋል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የዜጎችን መብት እንደሚገድብ በተለይም ሃሳብን የመግለጽ ነጻነትን እንደሚያፍን ለኢትዮጵያ ባለስልጣናት እንደገለጹላቸው ሚኒስትሩ ተናግረዋል። የጸጥታ ሃይ...
130
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በአጭር ጊዜ ውስጥ መነሳት አለበት ተባለ በኢትዮጵያ ተግባራዊ የተደረገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በአጭር ጊዜ ውስጥ መነሳት እንዳለበት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቴሊርሰን አሳሰቡ። ኢትዮጵያን ጎብኝተው ወደ ጅቡቲ ያመሩት የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ያለው ችግር ሊፈታ የሚችለው ነጻነትን በማስፋት ብቻ ነው ብለዋል። የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቴሊርሰን አምስት የአፍሪካ ሃገራትን ለመጎብኘት በጀመሩት ጉዞ በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ጉብኝት አድርገ...
131
ኮማንድ ፖስቱ ባለሀብቶችን እየዘረፈ መሆኑ ተገለጸ። ለኢሳት ከአራት ከተሞች የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው ከፌደራል በጀት ያልተመደበለት ኮማንድ ፖስቱ ለቀለብና ለእንቅስቃሴው የሚያስፈልገውን ገንዘብ ከባለሀብቶች እየሰበሰበ ነው። የጸረ ሰላም ሀይሎችን እንቅስቃሴ ትደግፋላችሁ በሚል በኮማንድ ፖስቱ የሚታሰሩ ባለሀብቶች ከእስር የሚለቀቁት በገንዘብ ተደራድረው መሆኑም ተመልክቷል። የገንዘብ አቅማቸውን ከየከተሞቹ ንግድና ኢንዱስትሪ መስሪያ ቤት መረጃ የሰበሰበው ኮማንድ ፖስቱ እንደየአቅማቸው ዳጎስ ያለ ገንዘ...
132
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁን ተከትሎ ወደ ሃገር ቤት የሚገባው ሕገወጥ መሳሪያ መጨመሩን ኮማንድ ፖስቱ አስታወቀ። ፋይል የነዳጅ እቀባ ጥሪውን ተከትሎ ስጋት የገባቸው የነዳጅ ቦቴ ሾፌሮች በአንዳንድ ቦታዎች መቆማቸውንም የኮማንድ ፖስቱ ቃል አቀባይ ለመንግስትና ለፓርቲ መገናኛ ብዙሃን አምነዋል። የሞያሌ ነዋሪዎች ወደ ኬንያ የተሰደዱት ደግሞ ኦነግ በነዛው ውዥንብር ነው ሲሉ መናገራቸውም ታውቋል። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነርና የኮማንድ ፖስቱ ቃል አቀባይ አቶ አሰፋ አብዩ በሳምንቱ መጨረሻ በሰጡት መ...
133
አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2010 ኤፍቢሲ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባሳለፍነው አርብ ለስድስት ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጁ ይታወሳል። በዚህም መሰረት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዝርዝር የአፈፃፀም መመሪያ በዛሬው እለት ይፋ ያደረገ ሲሆን፥ ሙሉ መመሪያውን እንደሚከተለው አቅብረነዋል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መመሪያ ቁጥር አንድ ክፍል አንድ፡ የተከለከሉ ተግባራት ንዑስ ክፍል አንድ፡ በማንኛውም የአገሪቱ ክፍሎች የተከለከሉ ተግባራት 1 ህገ መንግስቱንና ህገ መንግ...
134
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጇል። የኢፌዴሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 93 የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚደነገግበትን ሁኔታ በዝርዝር ያስቀምጣል። ምዕራፍ አስራ አንድ ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች አንቀጽ 93 ስለ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ 1 ሀ የውጭ ወራሪ ሲያጋጥም ወይም ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን አደጋ ላይ የሚጥል ሁኔታ ሲከሰትና በተለመደው የህግ ማስከበር ስርዓት ለመቋቋም የማይቻል ሲሆን፣ ማናቸውም የተፈጥሮ አደጋ ሲያጋጥም ወይም የህዝብን ጤንነት አደጋ ላይ የሚጥል በሽታ...
135
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መራዘም በህገ መንግስቱ ዓይን Written by አለማየሁ አንበሴ font size decrease font size increase font size Print Email Rate this item1 2 3 4 5 3 votes የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መራዘም በህገ መንግስቱ ዓይን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መራዘም ከፖለቲካና ከህግ አንጻር እንዴት ይታያል የህግ ባለሙያዎች የአዋጁ መራዘም ከህገ መንግስት ውጪ ነው ሲሉ ይሞግታሉ፡፡ ፖለቲከኞች በበኩላቸው፤ህዝቡ ህገ መንግስታዊ መብቱን ተነፍጎ ወታደራ...
136
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዓላማ ምንድን ነው ዮፍታሔ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዓላማ ምንድን ነው ዮፍታሔ – ችግሩ የተፈጠረው በኦሮሚያ እና ምናልባትም በአማራ ሆኖ እያለ በመላ አገሪቱ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተግባራዊ ማድረግ ለምን አስፈለገ – ኦሮሚያና አማራ ከዚህ ተመሳሳይ በሆነ ወታደራዊ እዝ Martial law ቆይተዋል። ሕዝባዊ እምቢተኝነቱን ግን አላቆመውም። ይህ ከሆነ ይህን አዋጅ ማወጅ ለምን አስፈለገ – ላለፉት 25 ዓመታት አገዛዙ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሳያውጅ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተግባራዊ ሊደረጉ ከሚ...
137
በደቡብ ክልል የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እና አንድምታዎቹ Raphael Addisu Analysis Ethiopian Politics ሃምሌ 23 2019 0 Minutes ከቅርብ ግዜ ወዲህ በደቡብ ክልል እየታዩ የመጡ ለውጦች ክልሉን ይመራ የነበረውን ይቅርታ የሚመራውን ለማለት ነው ድርጅት ደህዴንን ግራ ያጋባው ይመስላል በተለይ በያዝነው አመት በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ ህዝቦች የተነሱ የክልል አደረጃጀት ህገመንግስታዊ ጥያቄዎችን ተከትሎ የክልሉ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጉዳዩን የያዘበት አግባብ በተለያዩ ‘የክልል ይ...
138
አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እና የፓርላማ አባላት የኢትዮጵያ የሕዝብ የተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለሁለተኛ ጊዜ የተደነገገዉን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለማፅደቅ ወይም ለመጣል የፊታችን አርብ እንደሚሰበሰቡ ታዉቋል። አውዲዮውን ያዳምጡ። 0355 የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የምክር ቤት አባላት አዋጁን ዉድቅ እንድያደርጉ ከአገር ዉስጥም ሆነ በዉጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ጫና እያደረጉ ይገኛሉ። ለዚህም አንዱ ማሳያ ሰሞኑን በማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን ላይ የምክር ቤቱ አባላት የእጅ ስልክ ቁጥሮች ናቸዉ የተባለዉ ዝርዝር በማኅ...
139
የኢፌዴሪ ህገ መንግስት ስለ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምን ይላል efdre አዲስ አበባ ፣ መስከረም 29 ፣ 2009 ኤፍ ቢ ሲ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከትናንት ጀምሮ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጇል። የኢፌዴሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 93 የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚደነገግበትን ሁኔታ በዝርዝር ያስቀምጣል። ምዕራፍ አስራ አንድ ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች አንቀጽ 93 ስለ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ 1 ሀ የውጭ ወራሪ ሲያጋጥም ወይም ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን አደጋ ላይ የሚጥል ሁኔታ ሲከሰትና በተለመደው የህግ ማስከበር ስርዓት ለ...
140
አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተጥሷል February 25 2018 Filed under News Featureየዕለቱ ዜናዎች Posted by ዘሐበሻ 126 SHARES FacebookTwitter ከመሳይ መኮንን ከስታዲየም ውስጥ ነው። ከወዲያ ማዶ ደጋፊዎች ”ይሰማል” ይላሉ በህብረት። ከወዲህ በተቃራኒው የስታዲየሙ ክፍል ያሉት ደግሞ ”አዎ” ይላሉ። ”ወያኔ” ይላሉ ከማዶ ያሉት ፡ ”ሌባ ነው” በማለት ይመልሳሉ ከወዲህ ያሉት። እንዲህ እንዲህ እያለ በስታዲየሙ ያለው ፖለቲካዊ ግለት ጨመረ። አስቸኳይ አዋጁ በጥብቅ የሚከለክ...
141
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወሰነ 5 ጁን 2018 ይህንን ለሰው አጋራ Facebook ይህንን ለሰው አጋራ Messenger ይህንን ለሰው አጋራ Twitter ይህንን ለሰው አጋራ ኢሜይል ያጋሩ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትImage copyrightHOUSE OF PEOPLES REPRESENTATIVE ከወራት በፊት በመላው ሃገሪቱ ያገጠመውን ግጭትና ፀረመንግሥት ተቃውሞ ለማስቆም በኢትዮጵያ መንግሥት ተጥሎ የነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲነሳ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወሰነ። ...
142
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተነሳ ለአስር ወራት የዘለቀው የኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተነሳ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሔደው አስቸኳይ ስብሰባ የአገሪቱ ሰላም በመረጋጋቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ በሙሉ ድምፅ ወስኗል። የምክር ቤቱን እርምጃ አንድ እምርታ ነው የሚሉት ተቃዋሚ ፖለቲከኞች በቂ እንዳልሆነ ግን ይናገራሉ። This video file cannot be played Error Code 102630 አውዲዮውን ያዳምጡ። 0423 አዋጁን በማንሳት ሰላም ይመጣል ማለት አይደለም አቶ ሙላቱ ገመ...
143
ጥቂት ስለአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የኢትዮጵያ መስፈርት ከአለምፍ ሕግ ጋር ሲቃኝ Print Email ሀገሮች የዜጎቻቸውን የንብረት፣ የህይወት በአጠቃላይ የስብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶቻቸውን ለማስጠበቅና ለማረጋገጥ የተለያየ ሕጎችን ያወጣሉ፡፡ እነዚህም ሕጎች ከሕገመንግስቱ የየሃገሩ የበላይ ህግ ጨምሮ አዋጆችን፣ ደንቦችንና መመሪያዎችን ያካትታል፡፡ በእነዚህ ሕጎች የተደነገጉት መብቶችን ማራመድ አንዳንድ ጊዜ የሌላውን ሰው መብትና ደህንነት አደጋ ላይ ሊጥል ይችላል፡፡ በእንደዚህ ሁኔታ ላይ ሲሆን ሕግ እነዚህ መብ...
144
ስለ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምንነት አለማችን በታሪክ አስከፊነታቸው ጎልቶ ከሚነገርላቸው ከሁለቱ የአለም ጦርነቶች በተጨማሪ በተለያዩ ጊዜያት በርካታ አስደንጋጭ ክስተቶችን አስተናግዳለች፡፡ በዘመናችንም ወረርሽኝ፤ የእርስ በርስ ጦርነት፤ ሽብርተኝነት፤ የጎርፍ፤ አውሎ ንፋስና መሬት መንቀጥቀጥ አደጋ በተለያዩ የአለማችን ክፍሎች ለሰው ሕይወት መጥፋትና ንብረት ውድመት ምክንያት ሲሆኑ ተመልክተናል፡፡ ሀገራት እነዚህ ክስተቶች ሲያጋጥሙ ወይም እንዳይከሰቱ ለመከላከል በተናጠልና በጋራ ብርቱ ጥረት ያደርጋሉ፡፡ በሃይ...
145
ክልሎች አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ ይችላሉPublished 6 months ago on February 18 2019 By Teshome Tadesse ክልሎች አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ ይችላሉ በሬሞንድ ኃይሉ ክልሎች አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ ይችላሉ በሬሞንድ ኃይሉ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተለያዩ አከባቢዎች በስም የመያጠቀሱ ነገር ግን በተግባር አስቸኳይ ጊዜ አዋጅን የመሰሉ ድንጋጌዎች እየወጡ ይገኛሉ፡፡ ከወራት በፊት በቤንሻንጉል ጉምዝና ኦሮሚያ አጎራባች አከባቢዎች እንዲሁም በሱማሌና ኦሮሚያ ወሰን አቅራቢያ...
146
የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ ወሰነ ዛሬ መደበኛ ስብሰባውን ያደረገው የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ ወሰነ። ምክር ቤቱ በስብሰባው የሀገሪቱን የፀጥታ ሁኔታ ገምግሟል። አሁን ላይም በሀገሪቱ ስርዓት ሰፍኖ ሰላምና መረጋጋት በመመለሱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ መወሰኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍፁም አረጋ አስታውቀዋል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ የሚጠይቅ ረቂቅ የውሳኔ ሀሳብ እንዲፀድቅ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ልኳል...
147
የእቴጌዪቱ ግዞት ዘመን በሚያዝያ 3 ቀን 1903 ራስ ቢትወደድ ተሰማ ባደረባቸው ድንገተኛ ሕመም ምክንያት ሞቱ። ልጅ ኢያሱ ያን ጊዜ ገና የዐሥራ አምስት ዓመት ወጣት ሆነው የአጼ ምኒልክ አልጋወራሽ እንደ መሆናቸው ኢትዮጵያን በግላቸው ያስተዳድሩ ዠመር። ዳሩ ግን ምንም እንኳ ለአስተዳደር ሥራ ብስለትና ልምድ እንደሚጐድላቸው በመገንዘብ እንዲረዷቸው የመረጧቸው መኳንንት መኖራቸው ቢታወቅም መኳንንቱ ተገቢውን ምክር በማካፈል ረገድ ችሎታና ብርታት እንዳልነበራቸው ይነገራል። በዘልማዳዊ የትውልድ ሐረግ መሠረት...
148
እቴጌ ጣይቱ እንዳሉት እኔ ሴት ነኝ ፡፡ ጦርነት አልወድም ፤ ነገር ግን ሀገሬን እንደዚህ ያለ ክብር የሚነካ ዘለፋ ከምትሸከም ጦርነትን እመርጣለሁ ፡፡ ሂድ መንገዱን ጨርቅ ያድርግልህ እግሩን ለጠጠር ደረቱን ለጦር አስጥቶ ደሙን ለሀገሩ ፍቅር አፍስሶ ለአፈሩ ክብር ለብሶ እሱ ወድቆ ሀገሩን የማያቆም እዚህ ያለ እንዳይመስልህ ሂድ የኢትዮጲያን ሰው ባታውቀው ነው፡፡ ለሀገሩ መሞት ማለት ለሀበሻ ጌጡ ነው ፡፡ ሂድ ባሻህ ግዜ ተመለስ ተሰናድተን እንጠብቅሃለን ፡፡ ያንተን ወንድነትና የጣይቱን ሴትነትም ያን...
149
ልደትን በታሪክ እናክብር እቴጌ ጣይቱ ብጡል ነሐሴ 12 ቀን 1832 ዓም በቀድሞው በጌምድር ደብረታቦር ተብላ በምትጠራ ስፍራ ነው የተወለዱት፡፡ እነሆ የፊታችን ነሀሴ 12 የልደት ቀናቸው ነው፡፡የእቴጌይቱ ልደት አጼ ምኒልክ ከተወለዱበት ቀን ጋር ይገጣጠማል ፡፡ እኛም ታሪካዊ አበርክቷቸውን በመዘከር እንኳን ተወለዱልን መልካም ልደት ልንላቸው ወደድን፡፡ እቴጌ ጣይቱ ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ በንግስትነት ዘመናቸው ለሀገራችን አኩሪ ስራ ሠርተው አልፈዋል፡፡ ለሀገሪቱ እድገት ትልቅ ሚና የሚጫወቱ ንግስት ስለመ...
150
የመላው ጥቁር ህዝብ የድል ሃውልት፤ የአሸናፊነታችን ምልክት ፤ የነፃነታችን አርማ የእምዬ ምኒልክ፤ የእቴጌ ጣይቱ እና የፊታውራሪ ገበየሁ 175ኛ የልደት በዓል። እንኳን ለታላቁ ንጉስ ወ ንጉሱ ነገስት ዘኢትዮጵያ ዳግማዊ አፄ ምኒልክ 175ኛ የልደት በዐል አደረሳቹህ ……… ምኒልክ በጥበብ ህዝቡን ሲያስተዳድር ህዝቡ በፍቅር እንዲከተለው እንጂ በፍርሀት አንዲገዛለት አይፈልግም። በዚህም ምክንያት በማስተዳደሩ በኩል የተዋጣለት ጥሩ መሪ ነው ግሊከን …… በምኒልክ ዘመን የሀገሪቱ ክብር አደገ። የዘመናዊ አስተዳ...
151
ታሪክን የኃሊት ልክ የዛሬ ፻፪ 1️⃣0️⃣2️⃣አመት 💚💛❤ ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ እቴጌ ጣይቱ ብጡል አረፉ እቴጌ ጣይቱ ሰኞ የካቲት 4 ቀን 1910 ዓም በመንፈቀ ሌሊት ህመም ፀንቶባቸው ከሚወዱትና ከሚወዳቸው ሕዝብ በሞት ተለዩ ። የእረፍታቸውን ዜና የሀዘኑንም ሥነ ስርዓት ለማወጅ የቤተ መንግሥቱ መድፍ ሃያ አምስት ጊዜ ድምፁን አሰማ ። የንግስቲቱ 102ኛ የሙት ዓመት መታሠቢያ በንግሥና ዘመናቸው ቆመው እና ሌት ተቀን ልዩ ክትትል እያደረጉ ከጀግናው ባለቤታቸው ንጉሰ ነገስት እምዬ ምኒልክ ጋር በመሆ...
152
እቴጌ ጣይቱ እቴጌ ጣይቱ በሰው ልጆች ታሪክ ውስጥ ሕያው አድርጓቸው በየትኛውም ዘመን እንዲጠሩ ካደረጓቸው ነገሮች መካከል የጥቁር ህዝቦች ሁሉ አበሳ የነበረውን የቅኝ አገዛዝ ስልትን ‹‹አሻፈረኝ››› ብለው ጦርነት ገጥመው በድል ያጠናቀቁበት ታሪክ ነው። ኢጣሊያ ኢትዮጵያን የቅኝ ግዛት አካሏ የማድረግ የረጅም ጊዜ እቅዷን ለማሳካት የጫረችው የዓድዋ ጦርነት በድል እንዲጠናቀቅ እቴጌ ጣይቱ የበኩላቸውን ሚና ተወጥተዋል፡፡ ሚያዚያ 25 ቀን 1881 ዓም አምባሰል ውስጥ በንጉሥ ምኒልክ በኋላ ዳግማዊ አፄ ምኒልክ...
153
የካቲት 4 ቀን 1910 ዓም – በዘመናዊ የኢትዮጵያ ታሪክ ጉልህ ስፍራ ካላቸው ግለሰቦች መካከል አንዷ የሆኑት እቴጌ ጣይቱ ብጡል ኃይለማርያም አረፉ፡፡ እቴጌ ጣይቱ ምኒልክን አግብተው ወደ ሸዋ ከመጡ ጊዜ ጀምሮ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ የነበራቸው ተፅዕኖ ብዙና የገዘፈ ነው፡፡ ባለቤታቸው ዳግማዊ አጤ ምኒልክ ከታመሙ በኋላ ስልጣኑን በእጃቸው አስገብተው ፖለቲካውን ለመዘወር ያላመነቱት ብርቱዋ ሴት ጣይቱ፣ ይህ ተግባራቸው ከሸዋ መኳንንት ጋር አጣላቸውና ወደ እንጦጦ ማርያም ሄደው እንዲቀመጡ አስወሰነባቸው፡...
154
የእቴጌ ጣይቱ ብጡል መታሰቢያ ሃውልት በደብረ ታቦር ከተማ ሊገነባ ነው፡፡ የንጉሠ ነገሥት ሚስት እና የንጉሥ ባለሟል፤ የሴት ባለመላ እና ባለሙያ፤ የጦር ሜዳ ፈርጥ እና ሕግ አዋቂ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ቆርቋሪና መሥራች ናቸው፡፡ በቅፅል ስማቸው ‹‹ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ›› እቴጌ ጣይቱ ብጡል፤ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ የጎላ ስም ካላቸው ሴቶች ግንባር ቀደምቷ ናቸው፡፡ የዘር ሐረጋቸው ማሩ ቀመስ ደንቢያን በደጃች ማሩ፣ በስሜን ከደጃዝማች ኃይለማሪያም፣ ከላስታና ዋግ በዋግ ሹም ክንፉ፣ ከትግራይ በደጃዝማ...
155
እቴጌ ጣይቱ ብጡል በአጭር የህይወት ዘመን የረዥም ታሪክ ባለቤት በዳንኤል ወኪዳን 16082018 እቴጌ ጣይቱ ብጡል በአጭር የህይወት ዘመን የረዥም ታሪክ ባለቤት ፀሐፊ ዳንኤል ወኪዳን ጣይቱ ብጡል ማን ናቸው «ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ» በሚል ቅፅል ስም የሚታወቁት እቴጌ ጣይቱ ከአባታቸው ደጃዝማች ብጡል ኃይለ ማርያም እና ከእናታቸው ወይዘሮ የውብዳር በነሐሴ12ቀን1832 ዓም በጌምድር ውስጥ ደብረታቦር ከተማ ተወለዱ። በየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ስርዓት መሠረት በተወለዱ በ 80 ቀናቸው ጥ...
156
ዳግማዊ አጤ ምኒልክና የእቴጌ ጣይቱን ታሪክ የያዙ 2 ሲዲዎች ሊወጡ ነው ቅዳሜ የካቲት 23 2011አም ተከብሮ የሚውለውን 123ኛ አመት የአድዋ በአልን ምክንያት በማድረግ፣ የንጉስ ምኒልክና የንግስት እቴጌ ጣይቱ ታሪክ በኦድዮ ሲዲ ሊወጣ መሆኑ ተሰማ፡፡ ይህ በ50 ደቂቃ የምሁራንን ትንታኔ ይዞ የታተመ ሲዲ የራሱ ሳውንድ ትራክ ያለውና የተንታኞችም ሙያዊ ስብጥር የተለያየ ነው ተብሏል፡፡ ተወዳጅ ሚድያና ኮሚኒኬሽን የሁለቱ ሲዲዎች ሀሳብ አመንጪና አሳታሚ ሲሆን ኤክስኪዩቲቭ ፕሮዲዩሰሩም እዝራ እጅጉ ነው፡፡...
157
የኢትዮጵያው ንጉሥ ዳግማዊ ምኒልክ ጥሩ መሪ ነበር፤ ነገር ግን አንዲት ሴት ታዝበታለች። ኮንት ፔትሮ አንቶኖሊ ባሕር ዳር፡ የካቲት 232012 ዓም አብመድ እቴጌይቱ እንደ ግብፃዊቷ ኪሊዮፓትራ፣ እንደ ፈረንሳዊቷ ዝንድርክ እና እንደ ሩሲያዊቷ ታላቋ ካትረን ሲሉ ጣሊያኖች የዓድዋ ጦርነት ገድል የወንድ አርበኞች ታሪክ ብቻ ሳይሆን የሴት አርበኞች ጭምር እንደነበር ተናግረዋል፡፡ እቴጌ ጣይቱ በመቀሌ እንዳ ኢየሱስ የጠላት ምሽግ እንደተመለከቱ በጣም ተገርመውና ተጨንቀው ነበር። የተጨነቁበት ምክንያት ደግሞ ምሽ...
158
እቴጌ ጣይቱ ብጡል የጀግንነት ማህደር አንበሲት ጣይቱ እቴጌይቱ ብርሀን ዘኢትዮጵያ እንደአንድ ራስ በሺህዎች የሚቆጠሩ ጦር መርተው ከአድዋ ድል አጠቃላይ የውጊያ ውሎ ሰፊ ምእራፍ በተለይ በመቀሌው ከበባ The Siege of Mekelle ብቻቸውን ጎልተው የሚወጡበት አንፀባራቂ ገድል ፈፅመዋል። በአፄ ምኒልክ አጠቃላይ አርበኞች የሚመሩት የፊታውራሪ ገበየሁ ጦር ፋሺስት ጣሊያንን አምባላጌ ላይ አረፋ ካስደፈቀው በኋላ ፈርጥጦ መቀሌ ላይ ምሽጉን በማጠናከር፤ ከርቀት መድፍ እየተኮሰ አላስጠጋም ማለቱን ተከትሎ ጣ...
159
ባልና ሚስት ከአንድ ወንዝ ይቀዳሉን እንጂ በተመሳሳይ ቀን ይወለዳሉንስ አልሰማንም ነበር የመድኃኒት ጥቂት ይበቃል እያለች፤ የምኒልክ እናት አንድ ወልዳ መከነች፡፡ ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 112011 ዓም አብመድ ንጉሠ ነገሥት ከንግሥት፤ እምዬ ምኒልክ ከእቴጌ ጣይቱ፤ ርሀቤ ምኒሊክ ከብርሃን ዘ ኢትዮጵያ ጣይቱ፤ በአራት ዓመታት ልዩነት ነሐሴ 12 ቀን 1836 እና ነሐሴ 12 ቀን 1832 ዓም ሚስት እና ባል በቅደም ተከተል ከኢትዮጵያ ምድር ፈለቁ፡፡ በኢትዮጵያውያን ወግና ባሕል ብዙም ባልተለመደ መልኩ ሚስት ባል...
160
በጣና ሐይቅ የጎርጎራ ወደብና መናፈሻ ለሚሌኒየሙ በዓል የሚመጡ እንግዶችን ለማዝናናትና ለማስተናገድ በሚያስችል መልኩ እየተዘጋጀ መሆኑን የወደቡ አስተዳደር አስታወቀ፡፡ የወደቡ የአስተዳደርና ፋይናንስ ክፍል ኃላፊ አቶ እምሩ ሻረው ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በዓሉን ለማክበር ከውጪ የሚመጡ በርካታ ኢትዮጵያውያንና የውጪ ጎብኚዎች በሐይቁ የሚገኙ ገዳማትንና ታሪካዊ ሥፍራዎችን በጀልባ ለመጎብኘት የሚያስችላቸዉ ዝግጅት በመጠናቀቅ ላይ ነው፡፡ በተለይም በሐይቁ ላይ በጀልባ ለሚደረገው የመዝና...
161
በባህር ዳር ከተማ የአዲሱን ሚሌኒየም ዋዜማ ምክንያት በማድረግ በጣና ኃይቅ ላይ ከ30 በላይ ጀልባዎች የተሳተፉበት የባህር ላይ ትርኢት ትላንት ምሽት ተካሄደ፡፡ ትርኢቱን ከ10 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰዎች ተከታትለውታል፡፡ በጣና ኃይቅ ትራንስፖርት ድርጅትና በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ሚሌኒየም በዓል አከባበር ጽህፈት ቤት አስተባባሪነት የክልሉ ርእሰ መስተዳድር አቶ አያሌው ጐበዜና የሱዳን ገዳሪፍ ግዛት አስተዳዳሪ ኢንጂነር ሙባረክ ሙኒር ሐጂ በተገኙበት በጣና ኃይቅ ላይ ትላንት ምሽት የተካሄደው የባህር...
162
በጣና ሀይቅና አካባቢ ተፋሰስ ላይ እየደረሰ ያለውን የተፈጥሮ አየር መዛባትና የብዝሀ ህይወት መመናመን ለመካለከል ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት የተቀናጀ የአካባቢ ልማትና ጥበቃ ስራ መስራት ወሳኝ መሆኑን የአማራ ክልል ርአሰ መስተዳድር አስገነዘቡ፡፡ በጣና ሀይቅ ላይ እየደረሰ ያለውን ጉዳት ለመከላከል በባህርዳር ከተማ የተዘጋጀ አውድ ጥናት መክፈቻ ላይ ርአሰ መስተዳድሩ አቶ አያሌው ጎበዜ እንዳስታወቁት መንግስት ፣መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ለጋሾችና ሲቪክ ማህበራት በተፋሰሱ አካባቢ ለሚያካሂዱት የአካባቢ...
163
በጣና ሀይቅ የሚካሄዱትን የተፈጥሮ ሃብት፣ የብዝሃ ሕይወትና የተፋሰስ ልማቶች በበላይነት የሚያስፈጽም ተቋም እንዲቋቋም ተመራማሪዎችና ባለሙያዎች የውሳኔ ሃሳብ አቀረቡ፡፡ ሃይቁን በሚመለከት በባህር ዳር ከተማ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው ዓውደ ጥናት ትናንት ማምሻውን ሲጠናቀቅ ተመራማሪዎቹና ባለሙያዎቹ እንደተናገሩት የውሳኔ ሃሳቡን ማቅረብ ያስፈለገው የሃይቁን የተፋሰስ አካባቢና ተፈጥሯዊ ይዘት በጠበቀ መልኩ ለዘላቂ ልማት ለማዋል ታስቦ ነው፡፡ በሃይቁ አካባቢ የሚታዩትን የተበታተኑ አሰራሮች ለማቀናጀት፣...
164
ኩባንያው በጣና ሃይቅ ላይ የተከሰተውን የእምቦጭ አረም ለመከላከል የ15 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ኩባንያው በጣና ሃይቅ ላይ የተከሰተውን የእምቦጭ አረም ለመከላከል የ15 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ ባህር ዳር መጋቢት 262010 ኬኬ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ በጣና ሃይቅ ላይ የተከሰተውን የእምቦጭ አረም ለመከላከል ስራ የሚውል የ15 ሚሊዮን ብርና አንድ እስካቫተር ድጋፍ አደረገ። የእንቦጭ አረምን በመከላከል የግል ባለሃብቱና ህብረተሰቡ ድጋፍ እያደረገ መሆኑም ተገልጿል። የኩባንያው ምክትል ዋና ስራ ...
165
በጣና የእንቦጭ አረምን ለማስወገድ የሚያስችል ዘመናዊ ማሽን አገር ውስጥ መግባቱ ተገለጸ በጣና ላይ የተዛመተውን የእንቦጭ አረም ለማስወገድ የሚያስችል ዘመናዊ ማሽን ወደ ሀገር ውስጥ መግባቱ ተገለጸ ፡፡ የአረም ማስወገጃ ማሽኑን ገዝቶ ለክልሉ መንግስት ያስረከበው በባህር ዳር የተቋቋመው አማጋ የስፖንጅ ውጤቶች ማምረቻ ድርጅት ነው፡፡ የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ገብሩ ምትኩ እንዳሉት ማሽኑ በሰዓት 5 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታን ከአረም የማስወገድ አቅም አለው፡፡ በቅርቡም ከውጭ ሀገር በሚመጡ ባለሙያዎች ተገጣጥ...
166
የእምቦጭ አረምን በዘመናዊ መንገድ ሰብስቦ የሚያስወግድ ማሽን ዛሬ ስራ ጀመረ በጣና ሃይቅ ላይ የተከሰተውን የእምቦጭ አረም በዘመናዊ መንገድ ሰብስቦ ማስወገድ የሚችል ማሽን በትናንትና ዕለት በይፋ ተመርቆ ስራ ጀመረ። በአማጋ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የተገዛው ይኸው ማሽን አንድ ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት ሲሆን በሰዓት 5 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ የሚገኝ የእምቦጭ አረም የማስወገድ አቅም አለው፡፡ በጎንደር ዙሪያ ወረዳ ጎመንጌ በተባለው የሃይቁ ዳርቻ ትናንት በተካሄደው ስነስርአት የአማ...
167
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የእንቦጭ ማስወገጃ ማሽኖች ምርምር ምን ላይ ደረሰ ባሕር ዳር፡ የካቲት 252011 ዓምአብመድ በጣና ኃይቅ ላይ የተከሰተውን የእንቦጭ አረም ለማስወገድ አራት ማስወገጃ መንገዶች በአማራጭነት አገልግሎት ላይ እንዲውሉ ምክረሐሳብ ይቀርባል፡፡ ከእነዚህ ማስወገጃ መንገዶች እስካሁን ሁለቱ የሕዝብ ጉልበት እና ማሽነሪዎች ጣና ሐይቅ ዙሪያ አገልግሎት ላይ እየዋሉ ነው፡፡ ለመሆኑ እንቦጭን ለማስወገድ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምርምር ሥራዎች የሚሰሩ የአረም ማስወገጃ ማሽነሪዎች ምን አገ...
168
በቴክሳስ ኤኤም ዩኒቨርሲቲ በተመራማሪ ሳይንቲስትነት እየሰሩ ያሉት ዶር አብዩ የሃይድሮሎጂ እና የሳተላይት እውቀታቸውን በመጠቀም ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በየጊዜው የሳተላይት መረጃን በመጠቀም የጣናን የእምቦጭ ስርአጭት በቅንነት ሲያሳዩ የቆዩ ሃቀኛ ባለሙያ ነቸው ዶር አብዩ አንደሚሉት ከሆነ የእምቦጩ ስርጨት ከመቸውም በላይ ስለጨመረ የጣናን አደጋ መሸፋፈኑ እዚህ ላይ ሊቆም ይገባል ይላሉ። የጣናን የእምቦጭ ስርጭት መግታት ካልተቻለ ጉዳቱ መጠነ ሰፊ አንደሚሆን እየገለፁ የተቀናጀ እምቦጭን የማስወገድ መንገድ ...
169
በእንቦጭ አረም የጣና ቂርቆስ አንድነት ገዳም ህልውና ስጋት ውስጥ ነው… የገዳሙ መነኮሳት 95 Share ባህርዳር የካቲት 112011 በጣና ሐይቅ ላይ የተከሰተውን የእንቦጭ አረም በህዝብ ተሳትፎ የማስወገድ ሥራ ውስን በመሆኑ የገዳሙ ህልውና ስጋት ውስጥ መሆኑን የጣና ቂርቆስ አንድነት ገዳም መነኮሳት ገለጹ። የገዳሙ መነኮሳት እንቦጭን ለማስወገድ ለሚያከናውኑት ተግባር “ከጣና ትረስት ፈንድ” የ825 ሺህ 125 ብር ድጋፍ የተደረገ ሲሆን ገንዘቡም እንቦጭን ለማስወገድ የሚያስችል ጀልባ ለመግዛት ይውላል ተብ...
170
እምቦጭ አረምን ለማስወገድ የ20 ሚሊዮን ብር ዕርዳታ ተሰጠ በእስር ላይ የሚገኙት የኬኬ ድርጅት ባለቤት አቶ ከተማ ከበደ በጣና ሐይቅ ላይ የተንሰራፋውን እምቦጭ አረም ለማስወገድ የ20 ሚሊዮን ብር ዕርዳታ ሰጡ። አቶ ከተማ ከበደ፣ ዕርዳታውን ያደረጉት በወኪላቸውና በድርጅታቸው ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ በአቶ ቦጋለ ማሞ አማካይነት ነው፡፡ የኬኬ ድርጅት ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጁ እንዳሉት አቶ ከተማ ከበደ ዕርዳታውን ያደረጉት በሁለት መንገዶች ነው፡፡ — በጥሬ ገንዘብና ማሽን በመግዛት፡፡ ስጦታው የተበረ...
171
በእንቦጭ አረም የጣና ቂርቆስ አንድነት ገዳም ህልውና ስጋት ውስጥ ነው… የገዳሙ መነኮሳት 204 Share ባህርዳር የካቲት 112011 በጣና ሐይቅ ላይ የተከሰተውን የእንቦጭ አረም በህዝብ ተሳትፎ የማስወገድ ሥራ ውስን በመሆኑ የገዳሙ ህልውና ስጋት ውስጥ መሆኑን የጣና ቂርቆስ አንድነት ገዳም መነኮሳት ገለጹ። የገዳሙ መነኮሳት እንቦጭን ለማስወገድ ለሚያከናውኑት ተግባር “ከጣና ትረስት ፈንድ” የ825 ሺህ 125 ብር ድጋፍ የተደረገ ሲሆን ገንዘቡም እንቦጭን ለማስወገድ የሚያስችል ጀልባ ለመግዛት ይውላል ተ...
172
ጣና ሐይቅ ጣና ሐይቅ የአባይ ብሉ ናይል ወንዝ ምንጭ ሲሆን ከኢትዮጵያ አንደኛ ትልቁ ሐይቅ ነው። 84 ከሜ ረጅም እና 66 ኪሜ ሰፊ ነው። ባጠቃላይ 3500 ካሬ ኪሜ ይሸፍናል። በቁጥር እርግጠኛ መሆን ባይቻልም ብዙ ደሴቶች በሐይቁ ላይ ይገኛሉ። ባንዳንዶቹ ላይም ለምሳሌ በደጋ ደሴት የድሮ የኢትዮጵያ መሪዎች መቃብሮች ሲገኙ ኢትዮጵያ ውስጥ ክርስትናን ለመጀመሪያ ያስተዋወቀው አቡነ ሰላማ መቃብርም በዚሁ ሃይቅ ይገኛሉ። የጣና ሃይቅን የሚመግቡ 3ቱ ዋና ወንዞች ርብ፣ ጉማሬ ወንዝ ና ትንሹ አባይ በመባል ይታ...
173
ዜና ጣና በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ‹‹ዓለማቀፉ የጣና መልሶ ማቋቋም ማህበር ››እንቦጭን ለማስወገድ የሚውል ከ1 መቶ ሺህ ዶላር በላይ ገቢ ማሰባሰቡን ገለጸ፡፡ ባህር ዳር፡ መጋቢት 92010 ዓምአብመድበዛሬው ዕለት ‹‹ጤና ለጣና 2018 ወይም ያለምንም ልዩነት ለጣና ጤንነት›› በሚል መሪ ሀሳብ በዋሽንግተን ዲሲ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ተካሂዷል፡፡ የፕሮጀክቱ መስራችና አስተባበሪ ዶክተር ሶሎሞን ክብረት ከዋሽንግተን ዲሲ ለአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት እንደገለጹት በዕለቱ ለጣና ጤንነት ወይም ደህንነት ...
174
ጤና ለጣና በሚል እምቦጭ አረምን ለመከላከል በዋሽንግተን ዲሲ በተካሄደው የገቢ ማሰባሰቢያ በአንድ ቀን ብቻ 140ሺ የአሜሪካን ዶላር ተሰበሰበ። በዝግጅቱ ከ1 ሺ በላይ የሚሆኑ የአካባቢው ተቆርቋሪ ኢትዮጵያውያን ተገኝተዋል። በመድረኩ በርካታ ታዋቂ ድምጻውያንና ኮመዲያን ተገኝተው ለዝግጅቱ ድምቀት ሰጥተውታል። የዝግጅቱ አስተባባሪ አለም አቀፍ ትብብር የጣና መልሶ ማልማት ድርጅት ሰብሳቢ ዶክተር ሰለሞን ክብረት ጣናን ከጥፋት ለመታደግ የባለሙያዎች ቡድን የጥናትና የቴክኒክ እገዛ ማድረጉንና እምቦጭ አረሙን ...
175
የጣና ሐይቅን የወረረ ከአራት ሺህ 700 ሄክታር በላይ የእምቦጭ አረም ተወገደ ባህርዳር ጥር 232010 የጣና ሀይቅን ከእምቦጭ አረም ለመከላከል በተደረገው ጥረት ከአራት ሺህ 700 ሄክታር በላይ የሚሸፍነውን ቦታ ማፅዳት መቻሉን የአማራ ክልል አካባቢ ጥበቃ ደንና ዱር እንስሳት ባለስልጣን አስታወቀ። በባለስልጣኑ የእምቦጭ ማስወገድ አስተባባሪ ወይዘሮ በፍትሃ ጤናው እንደገለፁት አረሙን ማስወገድ የተቻለው ባለፉት ስድስት ወራት የአካባቢውንና ከሌሎች አካባቢዎች የሚመጡ በጎ ፈቃደኛን በማሳተፍ ነው። የተወገደ...
176
ጣና ሐይቅ ላይ ለ2013 ዓም የሚተርፍ አረም በማይኖርበት ደረጃ ለማፅዳት የቅደም ዝግጅት ሥራ መጠናቀቁን ኤጀንሲው አስታወቀ፡፡ ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 172012 ዓም አብመድ ጣና ሐይቅን ለመታደግ ሀብት እና ሐሳብን በማቀናጀት ለመጠቀም የሚያስችል ዝግጅት ማድረጉን የጣና ሐይቅ እና ሌሎች ውኃማ አካላት ጥበቃና ልማት ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡ ጣና ሐይቅ በእንቦጭ አረም ከተወረረ እና አደጋ ከተጋረጠበት ስምንት ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ አረሙ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ ይገኛል፤ ዘንድሮም ተጨማሪ ቦታዎችን አካልሎ ተስፋ...
177
ተከታታይነት የሚጠይቀው ጣናን የመታደጉ ጥረት እምቦጭ የሚል ስያሜ የተሰጠውን የዉኃ ላይ አረም ከጣና ሐይቅ ላይ ለማስወገድ የዘመቻ የመሰሉ እንቅስቃሴዎች በክረምቱ እና ክረምቱ ከወጣ በኋላም ታይተዋል። ይህ የዉኃ ቀበኛ ተክል ግን እንደውም ከዚህ ቀደም ወዳልታየባቸው አካባቢዎች ሁሉ እየተዛመተ መሆኑን ለመረዳት ችለናል። አረሙን የማጥፋት የሚደረጉ ጥረቶች እንዴት ይቀጥሉ This video file cannot be played Error Code 102630 አውዲዮውን ያዳምጡ። 1109 ከሰው ኃይል ጋር በርከት ያ...
178
‹‹ጣና ላይ የተከሰተው የእንቦጭ አረም የእኛም ችግር ስለሆነ የበኩላችንን እናደርጋለን፡፡›› የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ‹‹ኢትዮጵያዊነት ለሌላው ችግር ሁሉም በአንድነት በመገኘት ነፃ ማውጣት ነው፡፡›› የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ባሕር ዳር፡ መጋቢት 012011ዓም አብመድ ጣና ሐይቅ ላይ የተከሰተውን የእንቦጭ አረም ለማጥፋት በኅብረተሰቡ፣ በባለሀብቱ እና በጎ አድራጊ ግለሰቦች እና ድርጅቶች ርብርብ እየተደረገ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ችግሩን በዘላቂነት ከማስወገድ አንፃር የሚቀሩ ሥራዎች በመኖሩ ጣናን ከእንቦጭ ...
179
ጣናን ከእምቦጭ ለመታደግ የተሠማሩት የኦሮምያ ወጣቶች ከተለያዩ የኦሮምያ ልዩ ዞኖች የተውጣጡ ቁጥራቸው ከ 200 የሚበልጡ ወጣቶች የጣና ሐይቅን ከእንቦጭ አረም ለመታደግ ባህር ዳር ከተማ ይገኛሉ። መሪ ቃላቸው «ጣና የኛ ነዉ» የሚል ነው። This video file cannot be played Error Code 102630 አውዲዮውን ያዳምጡ። 1000 የኦሮምያ ወጣቶች ከሰባት የተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች ተውጣጥተው የጣናን ሐይቅ ከእንቦጭ ለመታደግ ሐሙስ ዕለት ጉዞ የጀመሩትን ወጣቶች በስልክ ያነጋገርኳቸው ፍ...
180
ጣና ሐይቅን የማዳኑ ዘመቻ ምሁራን እዉቀታቸዉን እያስተባበሩ ነዉ፤ ኅብረተሰቡ ደግሞ ጣናን እናድን ብሎ ተነስቷል። የጎጃምና ጎንደር ወጣቶች ከሌላ አካባቢ ያሉ ወገኖቻቸዉን አስተባብረዉ ጣናን ከወረረዉ አረም ለማላቀቅ ዘመቻቸዉን አንድ ብለዋል። ባለፈዉ ሳምንት ባህር ዳርና ጎርጎራ አካባቢ በአባይ ወንዝ እና በጣና ሐይቅ ላይ የተንሰራፋዉን የዉኃ ጠር አረም ሲነቅሉ ዉለዋል። This video file cannot be played Error Code 102630 አውዲዮውን ያዳምጡ። 1135 ባለፈዉ ሳምንት የጀመረዉ ...
181
ዜና ጣና ማህበሩ ጣናን ከእንቦጭ ለመታደግ ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ አሰባሰበ፡፡ ባህር ዳር፡ መጋቢት 142010 ዓምአብመድዓለምአቀፉ ጣናን መልሶ የማቋቋም ማህበር ከ4 ሚሊዮን ብር በላይከ140 ሺህ በላይ ዶላር ገቢ መሰብሰቡን ከዋሽንግተን በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡ በዓለማቀፉ ጣናን መልሶ የማቋቋም ማህበር ከጣይቱ የባህልና የትምህርት ማዕከል እና ዒሻራ መልቲሚዲያ ጋር በመተባበር በዋሺንግተን ዲሲ ባለፈው ቅዳሜ የተካሄደው ‹‹ጤና ለጣና 2018›› የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በተሳካ ሁኔታ አካሂዷ...
182
ጣናን በባለቤትነት ይዞ የሚሠራ አካል አለመኖሩ ሐይቁ ለገጠመው ችግር መፍትሔ ለመስጠት እንቅፋት መሆኑ ተገለጸ፡፡ ባሕር ዳር፡ ግንቦት 282011ዓም አብመድ የዓለም አካባቢ ቀን በጎንደር ዩኒቨርሲቲ እየተከበረ ነው፤ በአከባበሩ የጣና ሐይቅና የስሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክን የተመለከቱ ጽሑፎች ለውይይት እየቀረቡ ነው። በዩኒቨርሲቲው ማኅበራዊ ሳይንስና ሥነሰብዕ ‹ኮሌጅ› ልማትና አካባቢ ትምህርት ክፍል ‹‹የአየር ብክለትን እናስወግድ›› በሚል መሪ ሐሳብ የዓለም የአካባቢ ቀን እየተከበረ ነው። ቀኑ በዓለም ...
183
አማን ነህ ወይ ዓባይ ጣናስ አማን ነው ወይ – በላይነህ አባተ አማን ነህ ወይ ዓባይ ጣናስ አማን ነወይ ይኸ ከይሲ ዘመን በናንተም መጣ ወይ ጨለማው ሳይነጋ የሰፈር መንደርህ፣ ለሱዳኖች ሸጡህ ፉል ሊያስቀቅሉብህ፡፡ ግርማ ሞገስ እያልን ቅኔ ብንዘርፍልህ፣ ቅናት ፈጥፍጧቸው ሸረቡ ሊያደርቁህ፣ ሰርቀው ተመስኖ ውስጥ ሸንኮራ አስመጠጡህ፣ እምቦጭን ቻዝ ብለው በውሻ አስነከሱህ፡፡ ግንድ ይዞ ይዞራል እያልን ብንስቅብህ፣ የቤት ጨዋታ እንጅ እውነት እንዳይመስልህ፣ እሙት ዓባይዋ ተሲሳይ በላይነህ፣ ታጥንታችን ፈልቀህ...
184
የጣና ሐይቅን የተመለከቱ ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃዎችን የሚሰጥ በራሪ ካሜራ ባሕር ዳር መግባቱ ተሰማ፡፡ ባሕር ዳር፡ ሰኔ 132011ዓም አብመድ በጣና ሐይቅ ላይ የእምቦጭ አረም ከ2004ዓም ጀምሮ መከሰቱና የአረም መከላከል ሥራ ውጤታማነት በየጊዜው ሲያወዛግብ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ በተለይ ከአረም የጸዳውና አረሙ የወረረው የሐይቁ አካል መጠን በየጊዜው ሲያወዛግብ ነበር፤ ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ግምታዊ አሀዞች መሰጠታቸው ነበር፡፡ የዓለማቀፍ ጣናን መልሶ ማቋቋም ማኅበር ሊቀ መንበር ዶክተር ሰሎሞን ክብረት ለ...
185
ጣና ወደ መሬትነት እየተቀየ ነው የታሪካዊ ገዳማት ባለቤት ፤ የብርቅዮ አእዋፋት እና አሳዎች መገኛ ፤ የሺዎች መተዳደሪያ ጣና እንዲህ እንዳልነበረ ሲሆን ምን ይሰማናል ጣና ከወረረው የእምቦጭ አረም ሳያገገም ይህው ክረምቱ ዳግም ሊገባ ነው፡፡ ለጣና መፍትሄ ይሰጣሉ ተብለው የተገዙ የእምቦጭ ማጨጃ ማሽኖች እዚህ ግባ የሚባል ስራ ሳይሰሩ እንዲሁም ከህብረተስቡ የተሰበሰብው ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ የት እንደገባ ሳይታወክ ይህው ክረምት አለፎ ክረምት መጣ ፡፡ ጣናም እንደምታዩት በእምቦጭ እንደተወደረ አለ፡፡ ...
186
በጣና ላይ የተንሰራፋውን እንቦጭ ሙሉ ለሙሉ ለማጥፋት እቅድ መያዙ ተገለፀ የስትራቴጅክ ፕላን በማዘጋጀት በጣና ሀይቅ ላይ የተንሰራፋውን የእንቦጭ አረምን ሙሉ ለሙሉ ለማስወገድ እቅድ መያዙን የጣና ሀይቅና ሌሎች የውሃ አካላት ጥበቃና ልማት ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡ የኤጀንሲው ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር አያሌው ወንዴ እንደገለፁት፤ እምቦጭን ለማስወገድ ብዙ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጥረትና ድጋፍ ሲያደርጉ ቢቆዩም ስትራቴጅክ ፕላን ባለመኖሩ በሚፈለገው ልክ ውጤት ማምጣት አልተቻለም፡፡ ችግሩን ከመቅረፍም በላይ በፍጥ...
187
በጣና ሃይቅ ላይ የተስፋፋውን የእምቦጭ አረም ለማስወገድ የሚያስችል ገንዘብ ለማሰባሰብ የተዘጋጀው የእግር ኳስ ውድድር በባህርዳር ስታዲየም እንዳይካሄድ ታገደ ውድድሩ በጠባብ ስታዲየም እንዲካሄድ የተወሰነ ሲሆን ወሳኔውም በኳስ ሜዳው ሕዝባዊ ተቃውሞ ሊቀሰቀስ ይችላል በሚል ስጋት መሆኑም ተመልክቷል። የእምቦጭ አረም በጣና ሃይቅ ላይ ያደረሰውን ጉዳትና የደቀነውን አደጋ ለማስገንዘብና ገንዘብ ለማሰባሰብ በተዘጋጀው የእግር ኳስ ውድድር ለመሳተፍ የቅዱስ ጊዮርጊስ የእግር ኳስ ቡድን ከአዲስ አበባ ወደ ባህርዳር...
188
ሰሚ ጆሮ ያጣው የጣና ጩኸትና ዝምታን የመረጠው የክልል መንግስት አያለው መንበር ጣናን በተመለከተ ህዝባዊ አጀንዳ ከሆነ ወዲህ ህዝቡ ራሱ ስለሚጠይቅና መንግስትም ትኩረት ስለሚሰጠው እኛ ሌሎች ተግባራት ላይ እናተኩር በሚል ትኩረት ነፍገነው ነበር። ይሁንና ከጊዜ ወደጊዜ መሻሻሎች ይመጣሉ ስንል እንዲያውም እየተባባሰ ነው።የገንዘብ ችግር ስለነበር እርሱ ከበቂ በላይ ተሰብብሷል፣የባለሙያ ችግርም ስለነበር ምሁራን ለማገዝ ተስማምተው እያገዙ ነው። ምንም እንኳን በጣና ላይ ቢዝነስ መስራት የሚፈልግና በርካታ ግል...
189
የምንኩስና ህይወት🔸 🍂፬ቱ ስርወ ቅድስና🍂 🍃ምንኩስና፣ ድንግልና፣ ምናኔና ብሕትው🍃 🌷በዚህ ርእስ ዙሪያ አራት መሠረታዊ ቁም ነገሮች ተጠቅሰዋል፤ እነርሱም፡ ምንኩስና፣ ድንግልና፣ ምናኔና ብሕትውና የሚሉ ናቸው፤ የአራቱም ዓላማና ግብ ወይም መድረሻቸው አንድ እንደሆነ የታወቀ ቢሆንም፣ የጉዞ መነሻቸውና የአካሔድ አቅጣጫቸው ግን በአብዛኛው ጊዜ ልዩነት ያለው መስሎ ይታያል፡፡እዚህ ላይ ለመግለጽ የተፈለገው ምንኩስና ከድንግልና፣ ከምናኔና ከብሕትውና ሕይወት ጋር ያለው አንድነትና ልዩነት ነው፤ 🌾፩ ...
190
የብሕትውናየምንኩስና ኑሮ ክፍል 2 2 የሥርዓተ ምንኩስና ታሪክ 21 አባ ጳውሊ እና አባ እንጦንስ 211 አባ ጳውሊ አባ ጳውሊ እና አባ እንጦንስ በተባሕትዎ መኖር ከጥንት ዘመን የመጣ ይሁን እንጂ የብሕትውናን ኑሮ ሥርዓት በወጣለት መልኩ የጀመረው አባ ጳውሊ የተባለው ግብፃዊ አባት ነው፡፡ በንጉሥ ዳክዮስ ዘመነ መንግሥት በክርስቲያኖች ላይ በተነሣው ስደት ምክንያት አባ ጳውሊና ቆይቶም ደግሞ ሌሎች የአካባቢው ክርስቲያኖች በግብፅ በረሃዎች ውስጥ በምናኔ ይኖሩ ነበር፡፡ ይህንን አባ ጳውሊ የጀመረውን ...
191
የምንኩስና ህይወትክፍል ሁለት🍂🍂 🍃ሀ አባ እንጦንስ🍃 🌾የምንኩስና ምስራች ኮከበ ገዳም፣ አበ መነኮሳት፣ ትሩፈ ምግባር የሚል የክብር ቅጽል መገለጫ የተሰጠው ግብጻዊው አባት ቅዱስ እንጦንስ ነው፣ ቅዱስ እንጦንስ የተወለደው አቅማን በመባል ትጠራ በነበረች የግብጽ አውራጃ ነው፡፡ እናትና አባቱ ደጋግ ክርስቲያኖች ስለነበሩ እንጦንስን በመልካም አስተዳደግና በጥሩ ስነ ምግባር አንጸው ኮትኩተው አሳድገውታል፡፡ በእንጦንስ የወጣትነት ዘመን ምንኩስና የሚል ስም ከነአካቴው ያልተሰማ ያልታወቀ ነገር ነበር፡፡...
192
ምንኩስና ክፍል ፪ on January 23 2011 ለመሆኑ የመነኮሳቱ አመጋገብ እንዴት ነው መነኮሳቱ የሚመገቡት፦ ቋርፍ ወይም ስራስር ተቆፍሮ የሚገኝ ንፍሮ፣ዳቤ ወይም መኮሬታ፣ ቅጠላ ቅጠል፣ ቆሎ የመሳሰሉትን እንደ ገዳሙ ስርዓት መሰረት በቀን አንድ ጊዜ ብቻ ዘጠኝ ወይም ሶስት ሰዓት ላይ ብቻ ይመገባሉ። አለባበስ፦መነኮሳት በምድር መላእክት በሰማይ ሰዎች ናቸው ስለዚህ በዚህ አስተሳሰብ ከዓለማዊያን እንደተለዩ ሁሉ በአለባበስም እንዲሁ ይለያሉ ። አለባበሳቸው መነኮሳት ቢጫ ወይም ወይባ መልክ ያለው፣ ጥቁር...
193
የምንኩስና እምነትና የምንኩስና ባህል ልዩነት አላቸው Written by ብሩህ ዓለምነህ በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የፍልስፍና መምህር font size decrease font size increase font size Print Email Rate this item1 2 3 4 5 0 votes ባለፈው ሳምንት ጥቅምት 25 ቀን 2010 ዓም በወጣችው አዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ “ለኢትዮጵያ ኋላ ቀርነት ተጠያቂው ላሊበላ” በሚል ርዕስ አቶ ዓለሙ ኃይሌ አንድ ፅሁፍ አስነብበውናል። የፅሁፋቸው መነሻ “የኢትዮጵያ ፍልስፍና” የሚለው መፅ...
194
8 ክርስቲያናዊ ምንኩስና ክርስቲያናዊ የምንኩስና ሕይወት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚዘወተር ራሱን የቻለ ዓይነት የአናኗር ዘይቤ ነው። ይህን ሕይወት የሚመርጡ ክርስቲያን ወንዶችም ሆኑ ሴቶች ክርስቲያኖች ሁሉ ሊኖሩት የሚገባቸውን የጥምቀት ጸጋ ራሳቸውን ለእግዚአብሔር በመለየትና በመስጠት በተለየ ሁኔታ እርሱን በማኅበራዊ ሕይወት ለመከተል የሚሹ ናቸው። በርግጠኝነት ገዳማዊ ሕይወት መቼና የት እንደተጀመረ መናገሩ አዳጋች ነው። ምክንያቱም ገዳማዊ ሕይወት ሌላ ሳይሆን የክርስትናን ሕይወት ለመኖር ሲባል የ...
195
ክርስቲያናዊ ምነና Category የምንኩስና ሕይወት Published Friday 20 April 2012 1326 Written by Super User Hits 2639 Print Email 7 ክርስቲያናዊ ምነና ከላይ በመግቢያችን ላይ እንዳልነው ምናኔና ብሕትውና የሚሉት ቃላት ከምንኩስና ሕይወት ጋር ተቀራራቢነት ያለው ትርጉም ቢያስተላልፉም ቅሉ በጊዜ ሂደትም ሆነ በአናኗር ዘይቤ ይለያያሉ። ስለዚህም የክርስቲያናዊ ምንኩስናን አጀማመርና ታሪክ ለመረዳት የክርስቲያናዊ ምነናን ቀዳሚነትና አመጣጡን ማየቱ ጠቃሚ ነ...
196
ምንኩስና እና የአይሁድ ማኅበረሰብ 6 ምንኩስና እና የአይሁድ ማኅበረሰብ በአይሁዳዊ ታሪክ ውስጥ የምንኩስና ሕይወት ይዘወተር እንደነበር አስረጂ የሚሆን ጽሑፍ የለንም። ነገር ግን እንደፍንጭ የሚጠቆመው የናዝራውያን ሕይወት ብቻ ነው። ከዚህ ውጭ ግን መሰል የምንኩስና ሕይወት የነበራቸው አሴናውያን፣ ቴራፐውት እና የቁምራን ማኅበረሰብ የሚባሉ ነበሩ። ከአይሁዳውያን ወገን አሴናውያን የሚባሉ በአዲስ ኪዳን እንዴት ሳይጠቀሱ እንደቀሩ የሚገርም ነው። ምክንያቱም የነበሩበት ጊዜ ከ2ኛ ክዘ ከክርስቶስ ልደት በፊት...
197
የምንኩስና ሕይወት በጄይኒዝምና በእስልምና Category የምንኩስና ሕይወት Published Friday 20 April 2012 1325 Written by Super User Hits 2226 Print Email 5 የምንኩስና ሕይወት በጄይኒዝምና በእስልምና ጄይኒዝም በጄይኒዝም ሁለት ዓይነት የምንኩስና ቅርንጫፎች አሉ። የመጀመሪያዎቹ ዲጋምባራ የሚባል ሲሆን ምንም ልብስ የማይለብሱ ናቸው። ሆኖም ግን ራሳቸውን እርቃናቸውን እንደሆኑ አድርገው አያስቡም። ምክንያቱም አካባቢን ተፈጥሮን ለብሰናል ይላሉ። ይህንንም በ...
198
ሸማኒዝም ቅድመ ታሪክ ምንኩስና Category የምንኩስና ሕይወት Published Friday 20 April 2012 1324 Written by Super User Hits 2965 Print Email 3 ሸማኒዝም ቅድመ ታሪክ ምንኩስና በዓለም ታሪክ ከሚታወቁ ዓበይት ሃይማኖቶች በተሟላ መልኩ ሃይማኖት ተብለው ሊጠሩ ከሚችሉት ጥንታዊና ቀዳማዊ የሚባለው ሂንዱዊዝም ነው። በምንኩስና ሕይወት ታሪክም ጥንታዊ የምንኩስና ሕይወት የሂንዱዊዝም ምንኩስና እንደሆነ ታሪክ ይመሰክራል። ነገር ግን የተዋቀረና መልክ ያለው ...
199
አብይ ኖቤሉ ይገባዋል። አልማዝ በዳኔ ጥቅምት 2012 ከፍንፍኔ ለምን ይሆን ብዙ ኢትዮጵያውያን የጠቅላይ ሚኒስተር የአብይ አህመድ ዓሊን የሰላም ኖቤል ሽልማት የሚቃወሙት ኤርትራውያን ወንድሞቻችን ሳይቀሩ ለምን አጥብቀው ይቃወሙታል ቅናት ወይስ ስላልገባቸው ነው ከመቃወማቸው በፊትስ የተሸለሙበት ዋና ምክንያት ምን እንደሆነ አውቀው ነው ወይስ ሳያዉቁ ነው እየተቃወሙ ያሉት ብለን ብንጠይቅ የተቃውሞው ምክንያት ሊገባን ይችላል። እንደኔ አብይ አህመድ ዓሊ የሰላም ኖቤል ሽልማቱ ይገባዋል የሚል የግል እምነት አለ...
200
ከአልጀዚራ እስከ ዘኢኮኖሚስት የአብይ አህመድ ዶር ተስፋ ተጋሪዎች ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ዶር መጋቢት 24 በትረ ስልጣናቸውን በህዝብ እንደራሴዎች ፊት ከተቀበሉ ወዲህ የዓለም መገናኛ ብዙሃን ትኩረታቸውን በአዲሱ መሪ ላይ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለያዩ ወቅቶች ባደረጓቸው ንግግሮች ውስጥ ያቀረቧቸው የወደፊት ዕቅዶች እና አቅጣጫዎች እንዲሁም ተጨባጭ እርምጃዎች የተለያዩ መገናኛ ብዙሃን የማይጠበቅ ነገር ግን እየሆነ ያለ ታላቅ ለውጥ ሲሉ ዘግበውታል፡፡ የአሜሪካው የዜና አውታር ...
201
ትንሽ ስለ ኖቤል ሽልማት ያሬድ ሀይለማርያም 0191012 ትንሽ ስለ ኖቤል ሽልማት ያሬድ ሀይለማርያም Le Duc Tho Phan Dinh Khai ተብሎ የሚጠራው ቬትናማዊ የ1974 ኖቤል አሸናፊ የተናገረው፤ “peace has not yet been established” ዶር አብይ እንግዲህ በውስጥ ሰላማችን ላይ ደግሞ ወገብዎትን ታጥቀው እና ቆፍጠን ብለው ይሥሩና የኢትዮጵያ ሕዝብም ደግሞ ደጋግሞ ይሸልምዎት። እኔን ጨምሮ ብዙዎች ዛሬ ያገኙትን ሽልማት በደስታ ተቀብለነዋል። የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክታችንንም...
202
የዐቢይ አሕመድ የኖቤል ሽልማትና የኤርትራ ሁኔታ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዶር ሥም እንዲህ እንደትላንቱ በደስታ እና በሙገሳ ተነስቶ አያውቅም። ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያዊ ዜጋን ደጃፍ ያንኳኳው እና በዓለም በትልቅነቱ ወደር የማይገኝለት የኖቤል የሰላም ሽልማት ብዙዎች ዳግም በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ተስፋ እንዲያጭሩ አድርጓቸዋል። 180621 Kolumne BefeQadu Z Hailu በፍቃዱ ኃይሉ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዶር ሥም እንዲህ እንደትላንቱ...
203
የኖቤል ሽልማት ለዐቢይ አህመድ የኖርዌይ የኖቤል ተቋም ጠቅላይሚኒስር ዐቢይ አህመድን የዘንድሮው የሰላም ኖቤል ተሸላሚ አድርጓል። ተቋሙ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን ለዚህ ሽልማት ያበቃበት ዋናው ለ20 ዓመታት በድንበር ጉዳይ ሲወዛገቡ የኖሩት ኢትዮጵያ እና የኤርትራ መካከል ሰላም ለማውረድ ባደረጉት ጥረት መሆኑን አመልክቷል። This video file cannot be played Error Code 102630 አውዲዮውን ያዳምጡ። 0309 አቶ ክቡር ገና በሀገር ውስጥ በማካሄድ ላይ የሚገኙ ጠቃሚ ባላቸው ማሻሻያ...