doc_id
stringlengths
1
5
text
stringlengths
42
393k
306
የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ኢኮኖሚያዊ ዓላማ ካፒታሊዝም መሆኑ በድጋሚ ተረጋገጠ ካፒታሊዝምን መገንባት የአብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ኢኮንሚያዊ ዓላማ መሆኑ በድጋሚ መረጋገጡን የኢህአዴግን የ10 ዓመት ትግል ለመገምገም አዲስ አበባ በተሰየመው ስብሰባ ላይ ተገለጸ። የስብሰባው ቃል አቀባይ ትናንት በሰጤው መግለጫ ኢትዮጵያ የምትከተለው የካፒታሊዝም ወይም የከበርቴው ሥርዓት ግንባታ መሆኑን በኢህአዴግ የ1987 ዓም የአዋሳ ጉባዔ ላይ በማያሻማ ሁኔታ መጠቀሱን አውስቶ አሁንም የኢህአዴግ ኢኮኖሚያዊ ዓላማ ካፒታሊዝምን መገ...
307
የእንግሊዙ የገንዘብ ሚኒስቴር ጐርደን ብራውን ማክሰኞ ዕለት የአሁኑን የአገሪቱ የሀይል ተቆጣጣሪ አዲሱ የገንዘብ አገልግሎት ባላስልጣን ኤፍኤስኤ መብት ተከራካሪ አድርገው ሾሟቸው። የቀድሞው አንጋፋ ባለ ባንክ ካሉም ማካርቲ በሎንዶን የገንዘብ አለም ውስጥ በጣም አስፈላጊ ከሚባሉት ስራዎች ውስጥ አንዱ የሆነውን ሥራ በመስከረም ወር ሊጀምሩ በጊዜው የነበሩት ሀዋርድ ዴቪስ ደግሞ ከስልጣናቸው ወርደዋል። ዴቪድ በለንደን ዩኒቨርሲቲ በጣም ታዋቂ ከሆኑት ክፍሎች አንዱ በሆነው የለንደን የምጣኔ ሐብት ትምህርት ቤት ...
308
የአሜሪካ መንግሥት የ30 ሚሊዮን ብር የዕርዳታ ስምምነት ተፈራረመ መቀሌ፦ የአሜሪካ መንግስት ከትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥትና በክልሉ ከሚገኙ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር ትናንት የ30 ሚሊዮን ብር የዕርዳታ ስምምነት ተፈራረመ። የተሰጠው ገንዘብ በጉሌ መኸዳና ኢሮብ ወረዳዎች በጦርነት ምክንያት የፈራረሱ መኖሪያ ቤቶችን፣ የጤና ተቋማትን፣ ትምርህት ቤቶችን፣ የውሃ ፕሮጀክቶችን እንዲሁም የፈንጂ አደጋን ለመከላከል፣ ስለኤድስ የተጠናከረ ትምህርት ለመስጠትና ለግብዓት መግዣ እንደሚውል የክልሉ መስተ...
309
ኢትዮጵያ ከ288 ሚሊዮን ዶላር በላይ ዕዳ ተሰረዘላት ኢትዮጵያ የ288 ሚሊዮን 100 ሺህ ዶላር የውጭ ዕዳ የተቀነሰላት መሆኑን በፈረንሳይ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ። ኤምባሲው ትናንት ለኢዜአ እንደገለጼው ከትናንት በስቲያ ፓሪስ ላይ በተፈረመው ስምምነት መሰረት ኢትዮጵያ የተሰረዘላት ዕዳ እኤአ እስከ መጋቢት 31 ቀን 2004 ድረስ ትከፍለው ከነበረው 430 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ 67 በመቶ ነው። ስምምነቱ ላይ ለመድረስ የተቻለው ኢትዮጵያ ድህነትን ለመቀነስ ያወጣችውን ፕሮግራም ዓለም አቀፍ የገንዘ...
310
በነዳጅ ምርቶች ዋጋ ላይ ቅናሽ ተደረገ ከዛሬ ጀምሮ ለሚቀጥሉት ሦስት ወራት በሚያገለግለው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ላይ ቅናሽ መደረጉን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ። ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ትናንት የዋጋ ማስተካከያን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው በሚኒስትሮች ምክር ቤት የፀደቀውና ከዛሬ ጀምሮ ለሚቀጥሉት ሦስት ወራት ተግባራዊ የሚሆነው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ቅናሽ በማሳየቱ በሌሎች ምርቶች ሸቀጣ ሸቀጦችና አገልግሎቶች ላይ የዋጋ ቅናሽ ይኖራል ተብሎ ይጠበቃል። በአሁኑ...
311
ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋትን የቤንዚን አቅርቦት ከሱዳን የምታገኝበት ሁኔታ መመቻቸቱ ተገለጸ ኢትዮጵያ ከሚያስፈልጋት የቤንዚን አቅርቦት ሰማንያ አምስት በመቶ ያህሉን ከሱዳን በማገኘት የሰባት ሚሊዮን ዶላር ወጪ መቀነስ የሚያስችላት ሁኔታ መመቻቸቱን የኢትዮጵያ ነዳጅ ድርጅት አስታወቀ። የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ይግዛው መኮንን ከትናንት በስቲያ እንደገለጹት ኢትዮጵያ ከሚቀጥለው የፈረንጂች አዲስ ዓመት ጀምሮ በየወሩ 10 ሺ ሜትሪክ ቶን በዓመት ደግሞ 120 ሺህ ሜትሪክ ቶን ቤንዚን ከሱዳን ታስገባለች።...
312
የተመድ የልማት ኃላፊ ኢትዮጵያን ሊጐበኙ ነው የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም ዩኤንዲፒ ኃላፊ በመጪው ወር ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው። የኃላፊው ማርክ ማሎች ብራውን ጉብኝት ዓላማ ከአፍሪካ ኅብረት ባለሥልጣናት ጋር ተገናኝተው ኅብረቱ ድጋፍ በሚያገኝበት ሁኔታ ላይ ለመወያየት ነው። በተጨማሪም ኃላፊው ለአፍሪካ ልማት አዲስ አጋርነት ኔፓድ አጀንዳ ተፈጻሚ በሚሆንበት ሁኔታ ላይ እንደሚመክሩ አክራ ሜል ዘግቧል። የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም ዩኤንዲፒ ለአፍሪካ ልማት አዲስ አጋርነት ኔፓድ ...
313
ከባህር ማዶ በተገኝ ዜና በተባበሩት መንግስታት የአንባቢ መሪዎች ጉባኤ በተካሔደበት በጆሀንስበርግ ደቡብ አፍሪካ የ 122 አገሮች ተወንዮች 12 ከፍተኛ መርዛማነት ያላቸውን ኬሚካሎች ባለመጠቀም ዕቀባ ለማድረግ ስምምነት ፈረሙ። ክእነዚህም መካከል ዳዬክሲንስ እና ሌሎች ኬሚካሎች ሲሆኑ «ስድስቱ ቆሻሻዎች» በመባል የሚታወቁ ናቸው። ከካንሰር፣ ከወሊድ ችግሮች እና ከሌሎች በራሂያዊ አለመላመዶች ጋር የተዛመዱ ናቸው።
314
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን በሕወይት ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን ገለፀ የፌዴራል ፖሊስ የወንጀል መከላከል መመሪያ በፖሊስና በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች መካከል የተፈጠረውን ግጭት አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችና በአስተዳደሩ መካከል መለስተኛ አለመግባባት ተፈጥሮ መቆየቱን አስታውሶ ለአለመግባባቱ መንስዔ የሆነው ተማሪዎቹ ላቀረቧቸው ጥያቄዎች በአስተዳደሩ በኩል በተገቢው ወቅት ምላሽ አለመስጠቱና በሌላ በኩል ደግሞ በአጠቃላይ በግቢው ውስጥ ያሉ አስተዳደራዊ ጉዳዮች መልክ...
315
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችና በትሚኒስትሯ መካከል የተካሄደው ውይይት ያለውጤት ተበተነ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች መብታችን አልተከበረም በሚል ለጀመሩት ተቃውሞ እልባት ለመስጠት በትምህርት ሚኒስትሯና በተማሪዎች መካከል የተካሄደው ውይይት ያለውጤት ተበተነ። የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች ሰሞኑን መብታችን እየታፈነ ነው በሚል ያነሷቸውን ጥያቄዎች ይመልሳል ለችግሩም መፍትሔ ያስገኛል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው ይህ ስብሰባ ያለውጤት የተበተነው በተማሪዎች ከተነሱት ነጥቦች የፖሊስ ሠራዊት አባላት ከግቢ...
316
ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ መንግሥት የተሰጠ መግለጫ ሰሞኑን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ተቀስቅሶ የሰነበተ አለመረጋጋትና የመማር ማስተማር ሂደት መቋረጥ ከተከሰተ ጀምሮ መንግሥት የተማሪዎቹን ጥያቄዎች ለመስማትና አግባብነት ያላቸውን ለመመለስ ረጅም ርቀት እንደተጓዘ በመገናኛ ብዙሃን ተገልጿል። ተማሪዎቹ ያቀረቡትን ጥያቄ በዝርዝር አዳምጦ ተገቢነት ያላቸውንና የሌላቸውን ጥያቄዎች ለመለየትና በመፍትሔው ላይ ለመግባባት የሚያስችል ውይይት በትምህርት ሚኒስቴርና በተማሪዎቹ ተወካዮች መካከል ተካ...
317
ከትምህርት ሚኒስቴር የተሰጠ መግለጫና ውሳኔ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ያቀረቧቸው አስተዳደራዊ ጥያቄዎች ተገቢው ምላሽ እየተሰጣቸው መሆኑ ይታወቃል። ጥያቄዎቹ የግቢው ጥያቄዎች ሆነው እያለ ግን በተማሪዎቹ ሰበብነት በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ሕገ ወጥ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ነው። የተማሪዎቹ ጥያቄዎች በአግባቡ እየተመለሱ ባሉበት በአሁኑ ወቅት የሰላማዊ ሕዝብ ኑሮንና የመንግሥት ሥራን ሲያስተጓጉሉ ለሽብር ለሁከትና ለዝርፊያ መነሻ ሊሆኑ የሚችሉበት አንዳችም ምክንያት የለም። ከትናንት በስቲያ በ...
318
የተማሪዎች ጉዳይ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች በጋራ እየታየ ነው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀረቡት አቤቱታ በማህበራዊና በሕግ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴዎች በጋራ እየታየ ነው። ሁለቱ ቋሚ ኮሚቴዎች ትናንት ባካሄዱት ስብሰባ በተማሪዎቹ ማመልከቻና ባቀረቡት ጥያቄዎች ላይ የተወያዩ ሲሆን ከጉዳዩ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸውን መቤቶች በዛሬው ዕለት ለማነጋገር ወስነዋል። በተወካዮች ምክር ቤት የማህበራዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ፀሐፊ አቶ ሀርቃ ሀሮዬ ለጋዜጣው ሪፖርተር...
319
የጅማ ዩኒቨርስቲ ከመንግስት በተመደበ 274 ሚሊዮን ብር ወጪ የማስፋፋትና የተጨማሪ ሆስፒታል ግንባታ እንደሚያከናውን የዩኒቨርስቲው የውጪ ግንኙነት ኃላፊ አስታወቁ፡፡ ዘንድሮ ከ5ሺህ 500 በላይ አዲስ ተማሪዎችን ይቀበላል፡፡ ኃላፊው ፕሮፌሰር ጫሊ ጅራ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጡት ዩኒቨርስቲው የመማር ማስተማሩን ሂደት ይበልጥ ለማጠናክርና የቅበላ አቅሙን ለማሳደግ በዚህ ዓመት የአምቦ ካምፓስን ጨምሮ በ124 ሚሊዮን ብር ወጪ በጅምር ላይ የሚገኙ ሕንፃዎችን የማጠናቀቅና የማስፋፋት ስራዎችን...
320
ኢትዮጵያ ውስጥ የመጀመሪያው የግል ዩኒቨርሲቲ ሊቋቋም ነው በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የመጀመሪያውን የግል ዩኒቨርሲቲ ለማቋቋም ኢንቨስትሮችና የዩናይትድ ስቴትስ ዩኒቨርሲቲ ተወካዮች ባለፈው መስከረም 25 ቀን 1990 የመጀመሪያውን እርምጃ መውሰዳችውን በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ የላከው መረጃ አመለከት። ከኤምባሲው የተገኘው መረጃ እንደገለጸው ኢንቨስተሮቹና ተውካዮቹ ከተጋባዥ እንግዶች ጋር በመሆን በአዲስ አበባ ሰሜናዊ ክፍል የሚቋቋመውን በኢትዮጵያ የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ የግንቦታ ሥፍራ ...
321
«ዶር ፍስሃ ጊዜያችንንና ገንዘባችንን በከንቱ አባክነውብናል»የዩኒቲ ኮሌጅ ተማሪ ዪኒቲ ኮሌጅ በቅርቡ የትምህርት ክፍያውን ከ50 በላይ ያሳደገ መሆኑን በተቋሙ ውስጥ ለሚማሩት ተማሪዎችና ወላጆች ከገለፀ ጀምሮ በዶር ፍስሃና በትምህርት ቤቱ ላይ እየደረሰ ያለው ተቃውሞ በከፍተኛ ደረጃ መጋጋሉን የተለያዩ መረጃዎች ይጠቁማሉ። የኮከብ የጋዜጣ ዝግጅት ክፍል በኮሌጁ የሚማሩ ተማሪዎችንና ወላጆቻቸውን ለማነጋገር ባደረገው ጥረት ካሰባሰበው መረጃ ለመረዳት እንደተቻለው ተማሪዎቹና ወላጆቻቸው ዶር ፍስሃ የወሰዱትን ...
322
የበጎ አድራጎት ድርጅቶች የትራንስፎርሜሽን እቅዱ እንዲሳካ የበኩላቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተገለፀ 20128 0 5 አዲስ አበባ ሰኔ 12004 ዋኢማ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች መንግስት ተግባራዊ እያደረገ ያለውን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ለማሳካት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ሊወጡ እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ አሳሰቡ። አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ዛሬ የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ማህበራት ህብረት ሲሲአርዲኤ ብሔራዊ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች የስኬታማ...
323
በመላ አገሪቱ 7 ሚሊዮን ወጣቶች በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ይሰማራሉ 2012 0 270 203 5 አዲስ አበባ ሰኔ 182004ዋኢማ በመላው አገሪቱ 7 ሚሊዩን ወጣቶች በዘንድሮው ክረምት በበጎ ፍቃድ አገልግሎት እንደሚሰሩ የሴቶች ሕፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ሚኒስቴሩ የ2004 ዓም በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች አገልግሎት እቅድ ላይ የሚመክር የሁለት ቀናት አገራዊ አውደ ጥናት ከትናንት በስቲያ በአዳማ ከተማ ተጀምሯል፡፡ የሴቶች ሕፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስትር ደኤታ አቶ አልማው መንግሥት አውደ ጥና...
324
በዘንድሮው ክረምት ከ7 ሚሊየን በላይ ወጣቶች በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራ ላይ ይሳተፋሉ 2012 0 270 203 5 አዲስ አበባ ሐምሌ 42004ዋኢማ በዘንድሮው የክረምት ወራት 7 ሚሊዮን ወጣቶች በበጐ ፈቃድ አገልግሎት ስራ ላይ ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። በሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አብይ ኤፍሬም ለዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል እንደገለፁት፤ ወጣቶቹ እንደየአካባቢያቸው ተጨባጭ ሁኔታ በተለያዩ የስራ መስኮች ይ...
325
52 የሚሆኑ የሰላም ጓድ በጎ ፈቃደኞች ቃለ መሀላ ፈፀሙ 2012 0 260 197 5 አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 82005ዋኢማ ሀምሳ ሁለት የሚሆኑ የሰላም ጓድ በጎ ፈቃደኞች በአሜሪካው አምባሳደር ዶናልድ ቡዝ አማካኝት በአዲስ አበባ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በመገኘት ቃለ መሀላ መፈፀማቸውን ኤምባሲው አስታወቀ። ኤምባሲው ለዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል በላከው መግለጫ፤ በጎ ፈቃደኞቹ መካከል 36ቱ የጤና በጎ ፈቃደኞች ሲሆኑ፤ 16ቱ ደግሞ በግብርናና አካባቢ ጥበቃ መስክ የሚያገለግሉ ናቸው። በጎ ፈቃደኞቹ...
326
በጎ ፈቃደኞቹ በኢትዮጵያ በተለያዩ መስኮች ለውጥ መመልከታቸውን ገለጹ በኢትዮጵያ በተለያዩ መስኮች ለውጥ መመልከታቸውን በኢትዮጵያ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ አሜሪካዊያን የሰላም ጓድ አባላት አስታወቁ፡፡ 102 አባላት ያሉት እነዚሁ የበጎ ፈቃድ የአገልግሎት ሰጪዎች ዛሬ አዲሰ አበባ ውስጥ ከፕሬዝዳንት ግርማ ወልደጊዩርጊስ ጋር በጽሕፈት ቤታቸው ተወያይተዋል፡፡ ከነዚሁ አባላት መካካል ከ50 ዓመት በፊት በኢትዮጵያ ውስጥ የተለያዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በመስጠት ተሳትፎ ያደረጉ ነበሩ፡፡ እነ...
327
በጎ ፈቃደኞቹ በኢትዮጵያ በተለያዩ መስኮች ለውጥ መመልከታቸውን ገለጹ 201226 0 264 198 5 አዲስ አበባ፤ መስከረም 162005 ዋኢማ በኢትዮጵያ በተለያዩ መስኮች ለውጥ መመልከታቸውን በኢትዮጵያ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ አሜሪካዊያን የሰላም ጓድ አባላት አስታወቁ፡፡ 102 አባላት ያሉት እነዚሁ የበጎ ፈቃድ የአገልግሎት ሰጪዎች ዛሬ አዲሰ አበባ ውስጥ ከፕሬዝዳንት ግርማ ወልደጊዩርጊስ ጋር በጽሕፈት ቤታቸው ተወያይተዋል፡፡ ከነዚሁ አባላት መካካል ከ50 ዓመት በፊት በኢትዮጵያ ውስጥ የ...
328
ስለ በጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰጣጥ እስኪ በትንሹ።እስኪበጎ ፈቃድ ትርጉሙን እንመልከት።በጎ ፈቃድ ማለት በራስ ተነሳሽነት የማህበረሰቦችን ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ እና ፓለቲካዊ ችግሮች በመለየት መስራት ነው።ሀምሳ ሎሚ ለሀምሳ ሰው ጌጡ ነው ለአንድ ሰው ሸክሙ ነው እንዲሉ።ብዙ ያደጉ ሀገራት የእድገታቸው ሚስጥር ዘርፈብዙ ቢሆንም አንደኛው ግን ዜጎቻቸው የበጎ አድራጊነት ባህል ስላላቸው ነው።ምሳሌቻይናን እንውሰድ ።ይህን እውነታ ከሰይጣን በቀር ማን ይክዳል ጥናት እንደሚያመለክተው የሰውን ህሊናመንፈስspirit ከ...
329
በኮሎምብያ ዲስትሪክት መንግሥት የፓርክ እና የመዝናኛ መምሪያ የትብብር እና የልማት ክፍል DPR የበጎ ፈቃድ ሠራተኛዎች የዲሲ የፓርኮችና መዝናኛ መምሪያ DPR በርካታ ጨዋታ እና አስደሳች የበጎ ፈቃድ የሥራ እድል ይሰጣል። ተልዕኮአችን የተቀናጁ ፕሮግራሞች፣ እንቅስቃሴዎች እና ዝግጅቶች፣ እንዲሁም ደህንነታቸው የተጠበቀ እና ውብ ክፍት ቦታዎች እና የመዝናኛ አገልግሎቶች በገቢ መጠን እና ጥራት ያላቸው አገልግሎቶችን በእኩልነት በማቅረብ የዲሲ ነዋሪዎችን እና ጎብኚዎችን ደህንነት ማሳደግ ነው። የDPR ጠንካ...
330
የክረምት በጎ ፈቃድ ሆስፒታሎችን ማደስ ተጀመረ 5 months ago ሳምራዊት ባዬ በተያዘው የክረምት ወቅት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሃ ግብር አካል የሆነው ሆስፒታሎችን የማደስ በይፋ የጤና ሚንስትር ዶክተር አሚር አማንና ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በመገኘት አስጀምረዋል። ሀምሌ 2 ቀን የተጀመረው መርሃ ግብሩ ላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የአካባቢው ነዋሪዎችና የተለያዩ ባለሃብቶች ተገኝተዋል። በተመሳሳይ በጥቁር አንበሳ 2ኛ ደረጃ እና መሰናዶ...
331
በደቡብ ወሎ 78 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች በበጋ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት እየተሳተፉ ነው 822 Share ደሴ ጥር 152011 በደቡብ ወሎ ዞን 78 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች በተያዘው የበጋ ወቅት በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ መሰማራታቸውን የዞኑ ሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ መምሪያ አስታወቀ። በስራው ላይ የተሰማሩት ወጣቶችና ሌሎችም የህብረሰተብ ክፍሎች ናቸው፡፡ ከተሰማሩባቸው የስራ መስኮች መካከል ደም ልገሳ ፣ የከተማ ፅዳትና ውበት፣ የውሃ መፋሰሻ ቦዮች ጠረጋ፣ የአቅመ ደካማ ቤቶችን መስራትና መጠገን፣ የደረሱ የአ...
332
በበጋ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አምስት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ወጣቶች ይሳተፋሉ 565 Share አዲስ አበባ ጥቅምት 162011 ዘንድሮ በአገር አቀፍ ደረጃ አምስት መቶ ሚሊዮን ብር የሚገመት የበጋ ወቅት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እንደሚከናወን የሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስቴር አስታወቀ። በበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ አምስት ነጥን አምስት ሚሊዮን ወጣቶች ይሳተፋሉ። በየዓመቱ በክረምትና በበጋ ወቅት ወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በመስጠት የዜግነት ግዴታቸውን እየተወጡ ሲሆን፤ በአገልግሎቱም ኀብረተሰቡን ተጠቃሚ ...
333
በኤርትራ የጤና በጎ ፈቃድ አገልግሎት የሚሰጥ የኢትዮጵያ ሀኪሞች ቡድን ተሸኘ MedicalteamtoEritreaDecember 28 2018 በኤርትራ በጤና የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የሚሰጥ የኢትዮጵያ ሀኪሞች ቡድን በዛሬው ዕለት ተሸኘ። የጤና ሚንስትር ዴኤታ ዶክተር ሊያ ታደሰ እንደገለጹት፥ የሀኪሞቹ ጉዞ በኢትዮጵያና በአፍሪካ ቀንድ መካከል ያለውን የኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ትስስር ይበልጥ ለማጠናከር ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነው። የህክምና ባለሙያዎቹ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ትስስር ለማጠናከር የሚጫወ...
334
የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ወገንን የመርዳት ባህል እንድናዳብር አቅም ፈጥሮልናል ወጣቶች By wubishet seifu July 14 20190262 በዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ መርሃ ግብር በመላ ሀገሪቱ ከ10ሚሊዮን በላይ ወጣቶች የሚሳተፉ ሲሆን በድሬዳዋ አስተዳደር 60ሺ ወጣቶች ይሳተፋሉ፡፡ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ጉልበታቸውን፣ እውቀታቸውንና ሃብታቸውን በማስተባበር ወገንን የመርዳት ባህል እንዲያዳብሩ አቅም የፈጠረላቸው መሆኑን ወጣቶች ገለፁ፡፡ ባለፈው ቅዳሜ በችግኝ ተከላ ስነ ስርዓት የተጀመረው የክረም...
336
ከአሉባልታ ፖለቲካ ወደ በጎ ፈቃድ አገልግሎት ARTCLES By Admin On Aug 1 2018 0 158 Share Save ከአሉባልታ ፖለቲካ ወደ በጎ ፈቃድ አገልግሎት ስሜነህ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ሰዎች በራሳቸው መልካም ፍቃድና ተነሳሽነት የልፋታቸውን ዋጋ ሳይጠይቁ ወይም ከድርጊታቸው በስተጀርባ ሌላ አጀንዳ ሳይጠነስሱ በአብዛኛው ጊዜ በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የሚሳተፉበት ሰብአዊ ተግባር ነው፡፡ በአለማችን በተለያዩ አገራት የበጎ ፍቃድ ተግባር የሚያከናውኑ ግለሰቦች፣ ቡድኖችና ድርጅቶች በርካታ ናቸው...
337
የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ወደ ጠንካራ የመረዳዳት ባህል እየተቀየረ መሆኑ ተገለጸ July 8 201944 Share አዲስ አበባ እየተካሄደ ያለው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባር ወደ ጠንካራ የመተሳሰብ እና መረዳዳት ባህል እየተቀየረ መሆኑ ተነገረ። የኢትዮጵያ ወጣቶች ፌዴሬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሙህዲን ናስር አህመዲን ለአዲስ ዘመን እንደተናገሩት፣ ቀደም ሲል በቅስቀሳ፣ ጉትጎታና ግፊት ሲከናወን የነበረው ይህ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሁን ሙሉ ለሙሉ ተቀይሮ፤ ወጣቱ ማንንም በአስተባባሪነት ሳይፈልግ እራ...
338
ወሰን ተሻጋሪ የወጣቶች የበጐ ፈቃድ አገልግሎት በኢትዮጵያ የወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለምስጠት አንድ ሽህ ወጣቶች ወደ ተለያዩ ክልሎች ተሰማርተዋል። በሚሄዱበት ቦታ የትምህርት እገዛ እንደሚሰጡ፣ የአከባቢ ፅዳት ላይ እንደሚሳተፉ፣ የደምልገሳ እንደሚያደርጉ እና ሌሎችም እንቅስቃሴዎች ላይ እንደሚሰማሩ ይጠበቃል። This video file cannot be played Error Code 102630 አውዲዮውን ያዳምጡ። 0914 የበጐ ፈቃድ አገልግሎት በኢትዮጵያ በዚሁ የበጎ ፈቃድ ስራ ከሚሳተፉት አ...
339
የበጎ ፈቃድ አግልግሎት ለዘላቂ ልማት በአሜሳይ ከነዓን የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ሰዎች በራሳቸው መልካም ፍቃድና ተነሳሽነት የልፋታቸውን ዋጋ ሳይጠይቁ ወይም ከድርጊታቸው በስተጀርባ ሌላ አጀንዳ ሳይጠነስሱ በአብዛኛው ጊዜ በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የሚሳተፉበት ሰብአዊ ተግባር ነው፡፡ በአለማችን በተለያዩ አገራት የበጎ ፍቃድ ተግባር የሚያከናውኑ ግለሰቦች፣ ቡድኖችና ድርጅቶች በርካታ ናቸው። በኢትዮጵያም ዜጎች በመልካም ተግባር በመሳተፍ ማሕበራዊ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት የሚያስችላቸው አሳታፊ ዴሞክራሲ...
340
ይሖዋ በጎ ፈቃድ የሚያሳይበትን ዓመት አውጁ’ ‘ይሖዋ በጎ ፈቃድ የሚያሳይበት ዓመት’ ቃል በቃል የአንድ ዓመት ርዝማኔ ያለውን ጊዜ የሚያመለክት አይደለም 611 2 ይህ “ዓመት” ይሖዋ ቅን ልብ ያላቸው ሰዎች እሱ ለሚያሳውጀው የነፃነት አዋጅ አዎንታዊ ምላሽ መስጠት የሚችሉበት አጋጣሚ እንዲያገኙ ሲል የፈቀደውን ጊዜ ያመለክታል በመጀመሪያው መቶ ዘመን ይህ የበጎ ፈቃድ ዓመት የጀመረው ኢየሱስ በ29 ዓም አገልግሎቱን በጀመረበት ወቅት ሲሆን በ70 ዓም ኢየሩሳሌም በይሖዋ ‘የበቀል ቀን’ እስከጠፋችበት ጊዜ ድረ...
341
በጎ ፈቃደኛው ባለሀብት ደረጃውን የጠበቀ የአጸደ ሕጻናት ትምህርት ቤት ሊገነቡ ነው፡፡ ባሕር ዳር፡ ታኅሳስ 122012ዓም አብመድ አቶ ተመሥገን ከፍያለው የተባሉ በጎ ፍቃደኛ ባለሀብት በአማራ ክልል በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር አስተዳደር መሸንቲ ላይ ደረጃውን የጠበቀ ሞዴል የአጸደ ሕጻናት ትምህርት ቤት ሊገነቡ ዛሬ የቦታ ርክክብ ፈፅመዋል፡፡ በርክክብ ሥነ ስርዓቱ ላይ ባለሀብቱ አቶ ተመሥገን ከፍያለው በተወካያቸው ሀብታሙ በለጠ ዶክተር በኩል እንዳሉት በክልሉ የዳስ ትምህርት ቤቶችን ገጽታ ለመቀየር የሚ...
342
ብሔራዊ የበጎ ፈቃድ የማኅበረሰብ አገልግሎት መርሃ ግብር በይፋ ተጀመረ Mon Feb 24 2020በአስታርቃቸው ወልዴ የሀገር ዉስጥ ዜና “በጎነት ለአብሮነት” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው የብሔራዊ በጎ ፈቃድ የማህብረሰብ አገልግሎት ማብሰሪያ ፕሮግራም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዶር በተገኙበት ተጀመረ። ለአገልግሎቱ አምስት የበጎ ፈቃድ አምባሳደሮች የተመረጡ ሲሆን፣ ከመላ ሀገሪቷ የተውጣጡ ከ116 ሺህ በላይ ወጣቶችም ተመዝግበዋል ተብለዋል። በመርሃ ግብሩ አገራቸውን የሚወዱና የአገልጋይነት ስሜት የተላበሱ...
343
ጂጂ እና አስቴር አወቅ በጄል መንግስቱ ንዋይ ልጅ ተጣሉ በቅርቡ ታዋቂነት እያተረፈች የመጣችው ጂጂ እና አንጋፋ የሙዚቃ አቀንቃኝ አስቴር አወቀ እርስ በርስ በንዋይ መንግስቱ ንዋይ አማካኝነት መጣላታቸው ከአሜሪካ የደረሰን ዘገባ አሳወቀ። እንደዘገባው ከሆነ አስቴር አወቀ አዲስ አበባ ዝግጅት አቅርባ ወደ አሜሪካ ከተመለሰች በኋላ አፍቃሪዋ ከሆነው ከጄል መንግስቱ ንዋይ ልጅ ጋር አለመግባባት መፈጠሩን አስታውሷል። ጂጂ እና አስቴር በአንድ መድረክ እየተፈራረቁ ዝግጅታቸውን ካቀረቡ በኋላ በመሃል አስቴር ...
344
ጂጂ በአያሌ መገናኛ ብዙሃን ተደነቀች አዲሱ የጂጂ አልበም ደህና ገበያ ማግኘቱ ቢቢሲ ሲያመለክት፣ የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ በበኩሉ አልበሙ የሚገባውን ያህል አለመሸጡን በመጣው ኒውስ የጂጂን ሙዚቃ ጥሩ ዘፈኖችን ሠርተው ተገቢው ሥፍራ ካላገኙ ዘፋኞች ዝርዝር ውስጥ በአንደኛነት ማስቀመጡ ታወቀ። በጂጂ አልበም ሄርቤ ሃንኮክን ጨምሮ በመላው አለም ገናና ስም ያላቸው የትራንፔትና የሳክስ ተጫዋች ሙዚቀኞች መካፈላቸውን የገለፀው ቢቢሲ የጂጂ ዘፈን ለአመታት በኢትዮጵያውያን ከተሰሩ ዘፈኖች ሁሉ የላቀ ነው የሚሉ...
345
አርቲስት ጂጂ ኢትዮጵያውያን አትሌቶችን ለማወደስ ልዩ የሙዚቃ ዝግጅት በአቴንስ አቀረበች 28ኛውን የኦሊምፒያድ ውድድር እያስተናገደች ባለችው አቴንስ በርካታ ኢትዮጵያውያንን ያሰባሰበ ልዩ የሙዚቃ ዝግጅት ተካሄደ። ሬውተርስ ትናንት እንደዘገበው ባለፈው ቅዳሜ ምሽት በተካሄደው የሙዚቃ ዝግጅት መሪ ተዋናይ በተካሄደው የሙዚቃ ዝግጅት መሪ ተዋናይ ሆኖ ያመሸችው ታዋቂ ድምጻዊት እጅጋየሁ ሺባባው ጂጂ ናት። ጂጂ በነጭ የሀገር ልብስና በወርቅ ጌጣ ጌጦች ተንቆጥቁጧ የቀድሞና የአሁኖቹን የኦሊምፒክ ባለድል አትሌ...
346
ማህሙድ አህመድ በካናዳና አሜሪካ ሳይቀናው ተመለሰ እውቁ የኪነት ሰው አርቲስት ማህሙድ አህመድ ወደ ካናዳና አሜሪካ አዲሱን የፈረንጆች ዓመት ምክንያት በማድረግ የሥራ ጉዞ ቢያደርግም ሳይቀናው የተመለሰ መሆኑ ታውቋል። አርቲስት ማህሙድ አህመድ ለኢህአዴግ ድጋፍ በመስጠት በህወሃት በዓል ላይ በመገኘትና ከዚያም መልስ በሕዝብ መገናኛ ብዙሃን የወያኔ ኢህአዴግን ፕሮፓጋንዳ ለሕዝብ አስተላለፈ በሚል ከጊዜ ወደ ጊዜ በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያጣ ሆኗል። ማህሙድ አህመድ ከዚህ ቀደም በአውሮፓ ሲንቀሳቀስ ተቃ...
347
«ሼራተን አዲስ» በመጪው ቅዳሜ ይመረቃል በዓለም አቀፍ መስፈርት ከፍተኛ ስፍራ የሚሰጠው ሼራተን ሆቴል በኢትዮጵያ የአዲስ አበባ ግንባታውን በመጨረስ በመጪው ቅዳሜ የካቲት 21 ቀን 1990 የሚመረቅ መሆኑ ታወቀ። ከዚሁ ጋር በተያያዘ «ዘ አዲስ ፎረም» የተሰኘውና ታላላቅ ነጋዴዎችን ወደ አፍሪካ ለመሳብ ጥረት የሚያደርገው አካል የካቲት 29 እና 30 በዚሁ ሆቴል ውይይት እንደሚያደርግ ተገልጿል። በዚሁ ውይይት መለስ ዜናዊ የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒና ዮሴፍ ዊልሰን ከኋይት ሃውስ ይገኛሉ።
348
በተጨማሪ የሁለት አሜሪካውያን መርከበኞች አስከሬን ከየመን ወደ ኤደን ከዩኤስኤስ የባሕር ኃይል መርከብ ኮሌ ውስጥ ዛሬ ተገኝቷል። የዩኤስ ባለሥልጣናት ከቦታው ላይ ተገኝተው ኮሌ መርከብ ወደብ ላይ እያለች 17 መርከበኞችን በገደለው ፍንዳታ ላይ የሚያደርጉትን ምርመራ ቀጥለዋል። የኤደን ፖሊስ የቦምብ መሥሪያ መሥሪያዎች የተገኙበትንና ነዋሪዎቹም በአጥፍቶ መጥፋት ጥቃት በጦር መርከቧ ላይ ፍንዳታ አድርሰዋል ተብለው የተጠረጠሩበትን አፖርትማ ባለቤት ይዞ ዛሬ በመመርመር ላይ ይገኛል። እንዲሁም ዛሬ ፕሬዚዳንት ...
349
ጉዳት የደረሰባት «ዩኤስ ኮል» ዛሬ አገሯ ትገባለች። ዛሬ ጠዋት በ ፓስክግዋላ ሚሲሲፒ እንደምትደርስ ይጠበቃል። አጥፊዋ ከአምስት አመት በፊት እዚያው ክርስትና ተነስቶ ነበር። ጥገናው ወደ 240 ሚልዮን ዶላር እንደሚፈጅ ይገመታል። የየመንና የአሜሪካ ባለስልጣናት የጥቅምቱን የቦምብ ፍንዳታ አሁን ድረስ በመመርመር ላይ ይገኛሉ። 17 መርከበኞች ተገድለዋል። የየመን ጠቅላይ ሚኒስቴር እንደገለፁት ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ ቢያንስ 3 የመናውያን በሚቀጥለው ወር ለፍርድ ይቀርባሉ። የአለም አቀፍ የሽብርተኛ መረብ አ...
350
የዩኤስ የጦር መርከብ ከቀይ ባሕር ወደብ ከኤደን ነዳጅ እየሞላች በነበረችበት ጊዜ፣ ከአሸባሪዎች ቦምብ ሳይሆን አይቀርም፣ ተመትታ ለዕድሳት ወደ ዩኤስ ጉዞዋን ጀምራለች። ዴቭ ጋብላክ እንደዘገበው የዩኤስ መርከብ ኮል ከኤደን ወደብ ተጐትታ ወጥታ የተጐዳችውን መርከብ ተሸክማ ወደ አገሯ የምትወስዳትን የኖርዌ የመጓጓዣ መርከብ እየተጠባበቀች ነው። አራት ጐታች ጀልባዎች የዩኤስን የጦር መርከብ ኮልን በቀስታ እየጐተቱ ከየመን ደቡባዊ ወደብ ከኤደን ሲያወጧት የአሜሪካ ብሔራዊ መዝሙር ተዘመረ። ኮል ከሁለት ሳምንት...
351
የመን ውስጥ በዩኤስ የጦር መርከብ ኮል ላይ የደረሰውን ጥቃት ይመረምሩ የነበሩ የዩኤስ መረጃ ሰብሳቢዎች ላይ የቦምብ ጥቃት ይደርሳል የሚለው ሥጋት በሚኖሩበት ሆቴል የደኀንነት ሥራቸውን እንዲያጠናክሩ አስገድዷቸዋል። የፔንታጐን ቃል አቀባይ ኬን ባኮን ለሪፖርተሮች እንደተናገረው ያለው ሁኔታ የመከላከያ ሚኒስትሩን ለመስክ አዛዦች ጥሪ አንዲያደርጉ አስገድዷቸዋል። ሚኒስትሩ የእዝ ኃላፊዎችን እንዲሁም የደኀንነት ኃላፊዎችንና የደኀንነት ፀሐፊዎችን በቪዲዮ ለሚደረግ ስብሰባ ጥሪ አድርገው ነበር፣ የውይይቱ ርዕስም...
352
የዩኤስ መከላከያ ሚኒስትር ዊሊያም ኮኸን ከአካባቢው መሪዎች ጋር ስብሰባ ለማካሄድ ወደ ዘጠኝ የመካከለኛው ምሥራቅ ባሕረ ሰላጤ አገሮች በሚቀጥለው ሳምንት ለመሄድ አቅደዋል። ሚስተር ኮኸን ሳውዲ አረቢያን፣ ኩዌትን፣ ባሕሬንን፣ ኦማንን፣ የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶችን፣ እስራኤልን፣ ዮርዳኖስንና ግብፅን ለመጐብኘት በሚቀጥለው ማክሰኞ ይነሣሉ። ሚኒስትሩ ከእነዚህ አገሮች የመከላከያ ባለሥልጣናት ጋር እንደሚወያዩና እንዲሁም በአካባቢው ያሉትን የዩኤስ ሠራዊት አባላትን እንደሚጐበኙ ፔንታጐን ገልጿል። በባሕረ ሰላጤው...
353
በዩኤስ የጦር መርከብ ላይ የተፈጸመው ግልጽ ጥቃት ቢያንስ በስድስት አሜሪካውያን መርከበኞች ላይ የሞትና በ35ቱ ላይ የመቁሰል አደጋ አስከትሏል። ፍንዳታው የተከሰተው የዩኤስ የጦር መርከብ ኮል የመን ወደብ ላይ ነዳጅ በምትቀዳበት ጊዜ ነበር። ለብሔራዊ ሕዝባዊ ሬዲዮ የቻድ ፔርግራም ዘገባ። ኋይት ሐውስና ፔንታጐን ሁለቱም እንዳሉት የደረሰው ጥቃት የአሸባሪዎች ሥራ ሳይሆን አይቀርም። ፕሬዚዳንት ክሉንተን በአካባቢው ምርመራ ሲያካሂድ ለነበረው ለኤፍቢአይ ቡድን፣ ለፔንታጐንና ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አፋጣኝ እር...
354
በዩኤስ የጦር መርከብ «ኮል» ላይ በአሸባሪዎች መጥፎ አደጋ ከደረሰ ወዲህ አሁን ሁለት ወራት ያህል መሆኑ ነው፤ ትናንት ማታ ምንጮች ለብሔራዊ ሬዲዮ ኩባንያ እንደገለጹት ጥቃቱን ካቀዱት ዋና ተጠርጣሪ የአሜሪካ ሙስሊም ነውጠኛ አሁን ዮርዳኖስ ውስጥ በማረፊያ ቤት እንዲቆይ መደረጉን ተናግረዋል። ስሙም ጃኢድ ሂጃዚ ይባላል፤ የብሔራዊ ሬዲዮ ኩባንያ ዜና አገልግሎት ይህ ሰው ከአሸባሪው ኦሳማ ቢን ላደን ጋር በቀጥታ ከፍተኛ ግንኙነተ እንዳለው ደርሶበታል። በዩኤስ ወታደራዊ አውሮፕላኖች ላይ በፔርሻ ባሕረ ሰላጤና...
355
ቲቤት ውስጥ በረዶ የገገረበት የራራ ጫፍ መሬት በአደገኛ ሁኔታ እየሞቀች ለመሄዷ ጠቃሚ ፍንጭ ይሰጣል። ኦሂዬ ስቴት ዩኒቨርስቲና ላንዝሁ የግላሲኦሎጂ ኢንስቲትዩትና የቻይናው ጂኦክራይኦሎጂ ተመራማሪዎች የቲቤትን ግግር በረዶ በናሙናነት በመውሰድ ከመረመሩ በኋላ እንደተናገሩት ከዚያ ያለው የሙቀት መጠን ባለፉት 10000 ዓመታት ውስጥ በተመሳሳይ የጊዜ ወቅት ከታየው በበለጠ ባለፈው ምዕተዓመት አጋማሽ ላይ በአማካይ ከፍተኛ ሆኖ ተገኝቷል። የግግር በረዶው ናሙና መሬት በአብዛኛው አየር ውስጥ ከሚገኙ ብክለትን ከ...
356
በዚህ ምዕተ ዓመት መጀመሪያ ናሚብ በረሃ ከአትላንቲክ ውቅያኖስ ጋር በሚገናኝበት አካባቢ በሚገኘው ድንቅ የአሸዋ ክምር የባሕር ዳርቻ አልማዝ የማውጫ ጊዜ ነበር። ወንዶች የሚያንፀባርቀውን ማዕድን በመፈለግ በአሸዋው ላይ ይድሃሉ። ማሊቡ ላይ ዛጐል የመሰብሰብ ያህል ቀላል ሥራ ነበር። ወንዶቹ አሁንም አካፋና የእጅ ብሩሽ ይዘው የባሕሩን ዳርቻ እያሰሱ ናቸው። ግን የደ ቢርስ የተዋሃደ የማዕድን የግል ኩባንያ ንብረት በሆነው 336 ግዙፍ መኪና ከተጓዙ በኋላ ነበር ለሥራው አስፈላጊ የሆኑት ሰዎች ሥራቸውን የሚጀ...
357
የዘንድሮው የበልግ ዝናብ በ52 ዓመታት ውስጥ ከተመዘገበው ይበልጣል የዘንድሮው የበልግ ዝናብ መጠን ባለፉት 52 ዓመታት ከተመዘገበው ከፍተኛው መሆኑን ብሔራዊ ሜቲዎሮሎጂ አገልግሎት ድርጅት አስታወቀ። በድርጅቱ የአየር ትንበያና ቅድሚያ ማስጠንቀቂያ ቡድን መሪ አቶ ድርባ ቆርቻ ሰሞኑን ለጋዜጣው ሪፖርተር በሰጡት መግለጫ በአዲስ አበባ፣ በኮምቦልቻ፣ በሲሪንቃ፣ በኮፌሌ፣ በሶክሩና በእነዋሪ አካባቢ በ96 ነጥብ 3 እስከ 48 ነጥብ 8 ሚሊ ሜትር ዝናብ መመዝገቡን ገልጸዋል። ባለፈው የክረምት ወቅት ይህንን ...
358
የክረምት ማዕበል ያላችሁበትን ቦታ አየር ሁኔታ ያውክ ይሆን እስቲ«በአርእተ ዜና» ላይ የተካተተውን ሰፋ ያለ የአየር ትንበያ እንመልከት። በዛሬው ዕለት ሌላኛው ዙር የክረምት አየር እንደሚጀምር ይጠበቃል ይህም ዋነኛ የክረምት ማዕበል በደቡብ ረባዳማ ስፍራዎች በኦሀዮ ወንዝ ሸለቆ አድርጐ ቀስ በቀስ ወደ ሰሜናዊ ምስራቅ እየተስፋፋ ይሔዳል። እንደ ስፕሪንግ ፊልድ፣ ሚዙሪ ተመልሶ በሴይንት ሉዊስ እና በኢንዲያና ፓሊስ የመሳሰሉት ከተሞች ከፍተኛውን የበረዶ ዝናብ ያገኛሉ። በነገው ዕለት ጠዋት በ7 ኢንች በላይ ...
359
የቀድሞው የዩኤስ ጦር ሠራዊት ሃምሳ አለቃ በ1998 በምሥራቅ አፍሪካ በአሜሪካ ኢምባሲዎች ላይ በደረሰው የቦምብ ፍንዳታ ሤራ ውስጥ እንደነበረበት ኒው ዮርክ በሰጠው ቃል ጥፋተኛነቱን አምኗል። የግብፅ ተወላጅ የሆነው አሊ ሞሐመድ በመካከለኛው ምሥራቅ ውስጥ የዩኤስን ታርጌቶች ለማጥቃት ሳውዲ ተወልዶ ተቃዋሚ ከሆነው ከኦሳማ ቢን ላደን ጋር ያሤርባቸው በነበሩት አምስት ክሶች አምኗል። በቦምብ ፍንዳታው ከ220 ሰዎች በላይ ሞተዋል።
360
ከአሶስየት ፕሬስ፦ አንድ ብቸኛ ባለጠመንጃ ወንበዴ በሰሜን ኒው ዮርክ በሕዝበ በተጨናነቀ የእግር መንገድ እሁድ ዕለት ጥይት መተኮስ ጀምሮ ጥይት ከመጨረሱ በፊት አንድ ሰው አቁስሎ በሠራተኞች መሸነፉን ባለሥልጣኖች ተናግረዋል። ባለ ጠብመንጃው ወንበዴ ከኒው ዮርክ ከተማ በስተሰሜን 90 ማይል ርቆ በሚገኘው ኪንግስተን ውስጥ በሃድሰን የእግረኞች መንገድ ከ9 ሰዓት ትንሽ አለፍ ብሎ መተኮስ ጀመረ። የ24 ዓመቱ ባለ ጠብመንጃ ወንበዴ ወደ ቤስት ባይ መደብር ገብቶ መተኮስ ጀመረ። ጥቃቱን ሲጨርስ በሜል ሠራተኞች ...
361
ኤርትራ ብዛት ያለው ኃይል በቀጣናው ማሰማራቷ እንዳሳሰበው የፀጥታው ምቤት አስታወቀ ኤርትራ በጊዜያዊ የፀጥታ ቀጣናው ውስጥ ብዛት ያለው የሚሊሺያና የፖሊስ ኃይል ማሰማራቷ እንዳሳሰበው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምቤት አስታወቀ። የፀጥታው ምቤት የመንግሥታቱ ድርጅት ዋና ፀሐፊ በኢትዮ ኤርትራ ጉዳይ ላይ ለምክር ቤቱ ሰኔ 12 ቀን 1993 ባቀረቡት ወቅታዊ ሪፖርት ላይ ከመከረ በኋላ ከትናንት በስቲያ ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ ኤርትራ በአካባቢው የሚሰፍረው ኃይል ደረጃ በተመለከተ ከተመድ ጋር እ...
362
የጦር መሳሪያ ማዕቀቡ መነሳቱን ኢትዮጵያ ተቀበለች የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምቤት በኢትዮጵያና በኤርትራ ላይ ጥሎት የነበረው የጦር መሳሪያ ማዕቀብ እንደማይቀጥል ከትናንት በስቲያ የደረሰበትን ውሳኔ ኢትዮጵያ መቀበሏን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትናንት ባወጣው መግለጫ የፀጥታው ምቤት በሁሉ አገሮች ላይ ግንቦት ዘጠኝ ቀን 1992 ዓም የጣለው የጦር መሳሪያ ማዕቀብ እንደማይቀጥል መግለጹ ማዕቀቡ መነሳቱን ያመለክታል ብሏል። የፀጥታው ምቤት ላለፈው አንድ ዓመት ጥሎት የቆየ...
363
ኤርትራ ሰሞኑን ሠራዊቷን ከሚመሰረተው የፀጥታ ቀጣና እንደምታስወጣ ተገለጸ በኢትዮጵያና በኤርትራ ሠራዊት መካከል ጊዜያዊ የደህንነት ቀጣና ምሥረታ ሂደትን ለመቀጠል እንዲቻል የኤርትራ ሠራዊት ከመጋቢት 27 ቀን 1993 ጀምሮ አሁን ካለበት ሥፍራ ወደኋላ መንቀሳቀስ እንደሚጀምር በሁለቱ አገሮች የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተልዕኮ ማስታወቁን ኢዜአ ዘግቧል። ተልዕኮው ትናንት ባወጣው መግለጫ ኤርትራ ባለፈው የካቲት 24 ቀን 1993 ዓም ሠራዊቱን ከአካባቢው አስወጥታ የማጠናቀቅ ግዴታዋን የሚመመሰርተውን ጊ...
364
የጊዜያዊ ደህንነት ቀጣና ምስረታ የኤርትራ መንግሥትና ልዑክ በወሰዱት አቋም እልባት ሳያገኝ ቀረ የኢትዮ ኤርትራ ሚሽን ወታደራዊ ቅንጅት ኮሚሽን ስብሰባ የጊዜያዊ ደህነንት ቀጣና ምስረታን በሚመለከት የኤርትራ መንግሥትና ልዑክ በወሰዱት አቋም እልባት ሳያገኝ መቅረቱን የተባበሩት መንግሥታት የኢትዮ ኤርትራ ተልዕኮ የኢትዮጵያ ማስተባበሪያ ቢሮ አስታውቋል። የማስተባበሪያ ቢሮው እንደገለጸው ትናንት በናይሮቢ በተካሄደውና በተመድ የኢትዮ ኤርትራ ሚሽን ወታደራዊ አዛዥ በሜጀር ጄኔራል ፓትሪክ ካማራት በተመራው ...
365
የጦርነቱ መጋረጃ ተከፍቷል በእልልታ የተሸኘው የሻዕቢያ ሠራዊት ጠመንጃውን እንደ ጭራሮ ሰቅሎ አልጌና ላይ ተማረከ ግንቦት 4 ቀን በድንገት የፈነዳው የኤርትራና የኢትዮጵያ ግጭት ከዲፕሎማሲያዊው ጥረት አፈንግጦ ግልፅ ወደሆነ ጦርነት አምርቷል። ቅዳሜ፣ ግንቦት 22 ከለሊቱ 10፡00 ሰዓት በተጀመረው የሻዕቢያ ወታደሮች አዲስ የጥቃት እርምጃ ሁለት የኢትዮጵያ ወረዳዎች ዳልጌዳ እና አልጌና በቁጥጥር ስር መዋላቸው የሚታወስ ሲሆን፣ በዚህ አዲስ ወረራ ሻዕቢያ የአካባቢው ሚሊሺያ እና ሰላማዊ ህዝብ ላይ ጥቃት ...
366
የጦር ጉዳተኞች ሻዕቢያን ለመውጋት ቃል መግባታቸው ተገለጠ ባለፈው ግንቦት መጀመሪያ በድንገት በኢትዮጵያና በኤርትራ ድንበር ላይ በሶስት ግንባር የተከሰተው ጦርነት በመቶዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች መሞት ምክንያት ሲሆን ሁለቱም አገሮች ለግጭቱ መፈጠር አንዳቸው አንዳቸውን ተጠያቂ ካደረጉ ወዲህ የድንበሩ ውጥረት የተባባሰ መሆኑንና በዩኤስአሜሪካ አስማሚነት ሁለቱ አገሮች የአየር ድብደባ ላለማድረግ ቢስማሙም የምድሩ ውጊያ ይቀጥል ይሆናል የሚል ስጋት መኖሩን የሲኤንኤን ዜና ገልጦ በኢትዮጵያ የቀድሞ የጦር ጉዳተኞች...
367
የኢትዮጵያ ወታደሮች «ባኮል»ን ተቆጣጠሩ የተባለው ወሬ ሀሰት መሆኑ ተገለጸ ከባድ መሳሪያ የታጠቁ የኢትዮጵያ ወታደሮች ከትናንት በስቲያ ወደ ሶማሊያ መሬት ዘልቀው «ባኮል» የተባለውን አካባቢ ተቆጣጠሩ ሲል ቢቢሲ ያሰራጨው ዜና ሀሰት መሆኑን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሬስ ዋና ዳይሬክቶሬት አስታወቀ። የሶማሊያ ምክትል መከላከያ ሚኒስተር ናቸው ያላቸውንና መሐሙድ መሐመድ የሚባሉትን በመጥቀው ሬዲዮው ትናንት በአስር ሰዓት በአረብኛ ባስተላለፈው ዘገባ ሶማሊያ ተያዘ ወደተባለው አካባቢ ወታደሮቿን ...
368
በጋምቤላ ሽብርና የእርስ በርስ ግጭት ያነሳሱ አምስት ግለሰቦች በጽኑ እስራት እንዲቀጡ ተወሰነ በጋምቤላ ክልል ሽብርና የእርስ በርስ ግጭት ባነሳሱ አምስት ግለሰቦች ላይ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተዘዋዋሪ ችሎት ከአንድ እስከ 14 ዓመት የሚደርስ ጽኑ እስራት ወሰነ። ፍርድ ቤቱ በጋምቤላ ከተማ ከትናንት በስቲያ ባስቻለው ተዘዋዋሪ ችሎት አሞድ ኡቦንግ፣ ኡኪክ አቡላ፣ ኡቦን አዋለ፣ከበደ ኡኬሎና ኡመድ ኡቶው ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔውን የሰጠው በክልሉ ሽብር ፣ ብጥብጥና የእርስ በርስ ግጭት ማነሳሳታቸው ...
369
የኩርድ ሚሊሺያ ጦርና የአሜሪካን ልዩ የጦር ኃይል ከ1000 የሚበልጡ የአሜሪካን አየር ወለድ ወታደሮች ጋር በጣምራ ሆነው ሐሙስ ዕለት ስትራቴጂያዊ ጠቀሜታ ያለውን የአየር ማረፊያ ለመያዝ መንቀሳቀሳቸው፤ በሰሜን ኢራቅ ያለው የመጀመሪያው ትልቁ የኀብረቱ እግረኛ ጦር በሳዳም ሁሴን ላይ ሌላ የጥቃት ግንባር መክፈቱን ያሳያል። የጦሩ 173ኛ አየር ወለድ ብርጌድ የቁንጮ ወታደራዊ ሃይልን ጨምሮ ዝቅ ብለው ከሚበሩ ሲ17 ከሚባሉ የመጓጓዣ አውሮኘላኖች የሌሊት ጨለማን ተገን በማድረግና በመዝለል በወታደራዊና የሰው ...
370
አንድ የፍልስጤም የደህንነት ምንጭ እንዳለው እስራኤል ዋናዎቹን የባህር ጠረፍ ግዛት የፍተሻ ቦታዎች እንደለቀቀች ሰኞ ዕለት የፍልስጤም ኃይሎች ፍልስጤሞች ከ33 ወራት የፍልስጤሞች አመፅ በፊት ይዘውት ወደ ነበረበት ተመልሷል። ምንጩ እንደጠቀሰው የፖሊስ መኮንኖች በጋዛ ሠርጥ ዙሪያ ቦታውን በመያዝ ኢስቲፋዳ እስከፈነዳበት 1992 ድረስ አይተውት የማያውቁትን ነፃ እንቅስቃሴ እየተጠቀሙበት ነው። «የፍልስጤም ፖሊስ ከመስከረም 17 ቀን 1993 በፊት ይዞት የነበረውን የሥራ ቦታና ሐላፊነቶች በሙሉ ወስዷል። ምን...
371
የመሪዎቹ ጉባኤ በአያሌ የምዕራባዊው የባህር ዳርቻ ዌስት ባንክ እና ጋዛ ሰርጥ ከተከሰቱት ግጭቶች ጋር ተገጣጥሟል። በመቶዎች የሚቆጠሩ ድንጋይወርዋሪ ፍልስጤማውያን በእስራኤል ቁጥጥር ስር ባለችው የሔብሮን ከተማን በመውረር፣ ባለፈው ወር ተቀስቅሶ በነበረው ብጥብጥ ሳቢያ የተደነገገውን የሰዓትዕላፊ ዕገዳ ጥሰዋል። የእስራኤል ወታደሮች የእውነት ጥይትና በኘላስቲክ የተሸፈኑ የብረት ጥይቶችን በመተኮስ ቢያንስ ሰባት ሰዎችን አቁስለዋል ሲል ምስክሮች ገልፀዋል። በሺህ የሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰልፍ ያደረጉ ፍልስጤማውያን...
372
ዩኤስ አሜሪካ ሌላ የሚዛይል ጥቃት ለመሰንዘር መዛቷን ሱዳን ገለጠች ፕሬዚዳንት ኡመር አልበሽር ባለፈው እሁድ በብዙ ሺህ የሚቆጠር ሕዝብ በካርቱም የተቃውሞ ሰልፍ ባሳየበት ቦታ በዩኤስ ኤምባሲዎች ላይ የትም ቦታ ጥቃት ቢደርስ ሱዳንን እንደገና በሚዛይል የምታጠቃ መሆኑን ዋሽንግተን የማስፈራሪያ መልዕክት ለሱዳን ልካለች ሲሉ ገለጡ። የዩኤስ አሜሪካ ውጪ ጉዳይ መቤት ይህ አልባሌ ወሬ ነው ቢለውም አልበሽር መልዕክቱ የተላከላቸው በአንድ የቀድሞ የሱዳን ባለሥልጣን እጅ እንደሆነ አመልክተዋል። የመልዕክቱ ዝር...
373
የኮሚኒስቷ አገር ሰሜን ኮሪያ ከኒውክሌር ጦር መሣሪያ እራሷን ነፃ እንድታደርግ የገባችውን የመጨረሻ ሕጋዊ ግዴታ መሬት ቆፍራ ከቀበረች በኋላ ወታደሮቿ በማርች ውስጥ በዩኤስ ሄሊኮኘተር ላይ የጨረር ሞገድ የሚረጭ መሣሪያ ሳትተኩስ እንዳልቀረች የዩኤስ ባለሥልጣን ማክሰኞ ዕለት ገልጿል። ሄሊኮኘተሯ ከባድ ምሽግ ባለበት በሁለቱ ኮሪያዎች ወሰን አጠገብ በመብረር ላይ እንዳለች ተቆጣጣሪዎቹ ያልታወቀ ዓይነት ጨረር የሚረጭ መሣሪያ መኖሩን የሚያመለክት መረጃ መኖሩን እንዳገኙ ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የዩኤስ ወታ...
374
ጥቂት የአሜሪካ ከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣናት ብዙ ወራትን እንደሚወስዱ ባስጠነቀቁት ሳዳም ሁሴንን ከስልጣን በማስወገዱ ላይ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቶኒ ብሌርና የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ከጆርጅ ደብልዩ ቡሽ ጋር የተወያዩ ሲሆን ሐሙስ ዕለት አዳዲስ የአሜሪካ ወታደሮች ወደ ኢራቅ አቅንተዋል። ወደ 1000 የሚገመቱ የአሜሪካ ወታደሮች ከ173ኛ አየር ወለድ ብርጌድ በኮርዶች ዕዝ ወደሚገኘው ሰሜናዊ የኢራቅ አካባቢ በፓራሹት ወርደው ተጨማሪ ወታደርና ታንክ በማስገባት የጦር ሠፈር ማቋቋማቸውን የፔንታጐን ባለስልጣ...
375
የመከላከያ ሚኒስትር ዶናልድ ራምስፊልድ ዛሬ በቀረበው የጥያቄን መልስ ዝግጅት ከወታደሮች ጋር ተሳታፊ ነበሩ፤ ይህም የሚያስደስት እንጂ ምንም ነገር አልነበረም። ደስተኛ ያልሆኑ ወታደሮች በረጅም እርቀት እርምጃ ተደርጐ ብረት ለበስ መኪናዎች ባለመኖራቸው ቅሬታቸውን ለራምስፊልድ ገልጸዋል። ከአሶስየትድ ፕሬስ የቀረበ ጥያቄ ነበር፦ «ወደ ጦርነት የምትገባው ያሉህን ወታደሮች ይዘህ ነው» አሉ ራምስፊልድ ሲመልሱ፤ «እንዲኖርህ የምትፈልገውን ወይም ተስፋ የምታደርገውን ወታደር ይዘህ አይደለም።» ቶማስ ዊልሰን መከ...
376
በታችኛው ጁባ የሶማሊያዎች ውጊያ አንድ መንደር ወደመ በደቡብ ሶማሊያ በተቀናቃኝ የሶማሊያ አንጃዎች መካከል ከባድ ውጊያ ተካሂዶ ከፍተኛ ጉዱት መድረሱን የቢቢሲ ሬዲዮ ዘገበ። በዚህ የተቀናቃኝ አንጃዎች ተከታታይ ውጊያ በታችኛው የጁባ አካባቢ ሆሲንጆ የተባለች መንደር ሙሉ በሙሉ የወደመ መሆኑን የቢቢሲ ዘገባ አመልክቷል። የተረፈው አንድ የመንደሩ መስጊድ ብቻ እንደሆነም ተጠቅሷል። በዚህ ውጊያ ቁጥራቸው ወደ 50 የሚሆኑ ሰዎች የተገደሉ ሲሆን ውጊያው የተካሄደው በኦጋዴንና በሺክሃል ጐሳዎች መካከል በግ...
377
የአሜሪካና የእንግሊዝ ጦር ንጋት ላይ የባግዳድን ከተማ በከፍተኛ ሁኔት ከደበደበ በኋላ ቅዳሜ ዕለት ከፍተኛ እስትራቴጂያዊ ጠቀሜታ ወዳላት የወደብ ከተማ ባዝራ እየገሰገሰ ሔዷል። በሺህ የሚቆጠሩ በደቡብ የአገሪቱ ክፍል ተከበው የሚገኙ ወታደሮች በደረሰባቸው ከፍተኛ ጥቃት ሳቢያ እጃቸውን ሰጡ። የነዳጅ ማጣሪያ እምብርት የሆነችውና 13 ሚሊዮን ነዋሪ ያላትን የባዝራ ከተማን በመያዝ የሚደረገው ውጊያ እኩለ ቀን ላይ የጀመረ ሲሆን የተባበሩት ሃይሎች የኢራቅ ወታደሮችን ይዞታ ለመክበብ እና እጅ እንዲሰጡ ለማስገደ...
378
የአሜሪካን ሠራዊት ባግዳድ የሚገኘው የሣዳም ሁሴንን ዓለምአቀፍ የአይሮኘላን ማረፊያ ለማቆጣጠር ዓርብ ማለዳ ተንቀሳቅሶ ከኢራቅ መከላከያ ሠራዊት ጋር ከመዲናዋ በስተደቡብ በኩል ያለማቋረጥ ውጊያ ሲያደርግ ማርፈዱ ተገለፀ። ጆርጅ ደብሊዩ ቡሽ «ሥርዓቱ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል» አሉ። ምንም እንኳን ሙቀቱ 9ዐ ዲግሪ የሚደርስ ቢሆንም በግንባር የተሠለፈው ሠራዊት ከኬሚካል መሣሪያ ራሱን እንዲከላከል ይችል ዘንድ ቦት ጫማ እና ሙሉ የደንብ ልብስ እንዲለብስ ጥብቅ ማሣሠቢያ ተሰጣቸው። ከባግዳድ በስተደቡብ በሚገኘው...
379
የአሜሪካ ኃይሎች ለመጀመሪያ ጊዜ በሰሜን በኩል ወደ ከተማው በመግባት ወታደራዊ አይሮፕላን ጣቢያ፣ የደፈጣ ተዋጊዎችንና የሪፐብሊካኑን የጥበቃ ሃይል በመያዝ በመላው ባግዳድ ቁጥጥሩን አጥብቀዋል። ይህ በዚህ እንዳለ ሶስት የውጭ ጋዜጠኞችን በገደለው ጥቃት ምክንያት የአሜሪካ የጦር ሃይል ከፍተኛ ወቀሳ ገጥሞታል። የፔንታጐን ባለስልጣኖች ማክሰኞ ዕለት እንዳስታወቁት የኢራቁ መሪ ሳዳም ሁሴን በባግዳድ አጐራባች ቦታዎች ላይ ከትላንት በፊት በተደረገው በዩኤስ የአየር ጥቃት መሞት አለመሞታቸውን አያውቁም። ጥቃቱ በ...
380
በኮንሶ የረዥም ዘመን አጽም ተገኘ ኢዜአ፦ በኮንሶ በሚገኘው የፓሊዎ አንትሮፖሎጂ መካነ ቅርስ ጥናቱን በማካሔድ ላይ የሚገኘው ቡድንያገኘው ከ1 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዓመት በፊት የነበረ የጥንት ሰው ዝርያ የራስቅል ግኝት ለሳይንሳዊ ኅትመት መብቃቱን የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ድርጅት አስታወቀ። ድርጅቱ ትናንት ለኢዜአ እንደገለጸው በኮንሶ የፓሊዎ አንትሮፖሎጂ መካነ ቅርስ ጥናት በተጀመረበት በ1985 ዓም የተገኘውና በሳይንሳዊ አጠራሩ ዓውስትራሎፒቲክስ ቦዛይ በመባል የሚታወቀው የጥንት ሰው ዝርያ የራስ ቅል ጥናት...
381
«አዋጁ የኤርትራ ዜግነት የመረጡትን አይመለከትም» «የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆኑ የውጭ ዜጐችን በትውልድ አገራቸው የተለይዩ መብቶች ተጠቃሚ ለማድረግ» በሚል ርዕስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረቀቀው አዋጅ በሚኒስትሮች ምቤት ፀደቋል፤ ሐሙስ ጥር 9 ቀን 1994 ዓም ለሕዝብ ተዋካዮች ምቤት ቀርቦ ወደ ሕግ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ተመርቷል። ይህ በ3 ክፍል በ18 አንቀጾች የተከፋፈለው አዋጅ የሌላ ሐገር ዜግነትን የወሰዱ በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሆኑ ዜጐች፤ በትውልድ ኢትዮጵያዊ ባይሆኑም ወላጆቻቸው ወይንም አያቶቻቸው...
382
ሲህዴድ አቶ አባተ ኪሾን ጨምሮ አምስት ከፍተኛ የአመራር አባላቱን ከማዕከላዊ ኮሚቴ አስወገደ የሲዳማ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት አቶ አባተ ኪሾን ጨምሮ የአመራር ብቃት ማነስና የሥነ ምግባር ችግሮች ታይቶባቸዋል ያላቸውን አምስት ከፍተኛ የአመራር አባላቱን አስወገደ። ድርጅቱ ሊቀመንበሩን አቶ አባተ ኪሾንና ምክትል ሊቀመንበሩን አቶ ብሩ ባሌን ጨምሮ አምስቱን የአመራር አባላት ያስወገደው ከፍተኛ የአመራር አባላቱና ካድሬዎቹ ድርጅቱን ከመበስበስ አደጋ በማዳን ወደፈጣን ጎዳና ለመውሰድ በሚያስችሉ ነጥቦች...
383
«የብአዴን ጄኔራሎች መለስን አድነዋል» በእስር ላይ ካሉት ታምራት ላይኔ ጋር ሆነው ኢህዴንን በመመሥረት ቁልፍ ሚና የተጫወቱት ያሬድ ጥበቡ ከወደ አሜሪካ ሆነው ባወጡት ፅሁፍ «የአዲሱ ለገሠ ዕጣ ያሰጋኛል» አሉ። አቶ ያሬድ በዜጋ ላይ ባወጡት ፅሁፍ ከአቶ አዲስ ሌላ ኤርትራዊው በረከት ስምዖን በሕወኃት ውስጥ ያሉ «ጠባቦች» የጥቃት ዒላም ስለሆኑ የእሳቸውም ዕጣ ያሰጋኛል ብለዋል። እንዲሁም «ነገሩን ግን ይበልጥ ውስብስብ የሚያደርገው፣ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ፣ የምክትል ጠሚኒስትር አዲሱ ለገሠንና የማስ...
384
«በሉአላዊነት ላይ ከመለስ የተለየ አቋም ነበረን» ብአዴኖች በሕወሐት ማዕከላዊ ኮሚቴ ውስጥ መከፋፈል በተፈጠረበት ወቅት ከአቶ መለስ ቡድን ጋር የቆሙት ብአዴኖች በሉአላዊነት ጉዳይ ከአቶ መለስ ዜናዊ የተለየ አቋም እንደነበራቸውና ከእነ አቶ ተወልደ ጋር ተመሳሳይ ዕምነት ያራምዱ እንደነበር ገለጡ። ከሕወሐት ማዕከላዊ ኮሚቴ የተወገዱት እነ አቶ ተወልደ ወማርያም «የመለስና የብአዴን ፖሊት ቢሮ የድብብቆሽ ድራማ» በሚል ርዕስ በ«ሪፖርተር»መፅሔት ላይ ላቀረቡት ፅሁፍ ብአዴኖች በዚያው በሪፖርተር መፅሄት ላ...
385
የዩኤስ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ደብልዩ ቡሽ ለካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ለጂን ችሬቲየን በኢንዱስትሪ የበለጸጉት አገሮችና ሩሲያ በሚቀጥለው ጊዜ በሚያደርጉት የመሪዎች ስብሰባ ላይ ሊያገኙዋቸው መጓጓታቸውን ሰኞ ዕለት በስልክ የገለጹላቸው መሆኑን ኋይት ሐውስ ማክሰኞ ዕለት ተናግሯል። «ሁለቱ መሪዎች ስለሚቀጥለው የቡድን 8 ስብሰባ፣ ስለዩኤስ ካናዳ ግንኙነት እና ስለሌሎች ዓለም አቀፋዊ አሳሳቢ ጉዳዮች መወያየታቸውን «የቡሽ ቃል አቀባይ አሪ ፍሌሸር ፖሪስ ውስጥ ከጁን 13 ከሚካሄደው የመሪዎች ስብሰባ በፊት ትንሽ ቀ...
386
የኔዘርላንድና የካናዳ ወታደሮች ግዳጃቸውን ፈፀሙ የሕንድ ወታደሮች ሥራቸውን ጀመሩ በተባበሩት መንግሥታት የኢትዮጵያና ኤርትራ ተልዕኮ ውስጥ ተሰማርተው የነበሩት የኔዘርላንድና የካናዳ የሰላም አስከባሪ ኃይሎች ግዳጃቸውን አጠናቀው ለሚተኳቸው የሕንድ ወታደሮች ስራቸውን ማስረከባቸውን በኢትዮጵያ የኔዘርላንድ ኤምባሲ አስታወቀ። ኤምባሲው ትናንት እንደገለጸው የኔዘርላንድና የካናዳ ባታሊዮን አዛዥ ኔዘርላንዳዊው ሌተና ኮሎኔል ቶን ቫን ኤዴ የተልዕኮውን ማዕከላዊ ዘርፍ እዝ አዲግራት ላይ ባለፈው ሰኞ ለህንዳዊው...
387
የኢህአዴግ ልሣኖች በሳምንት 2ጊዜ እንዲወጡ ተወሰነ ጋዜጠኞች ወደ ጦር ግንባር ተሸኙ የኢህአዴግ ልሣኖች የሆኑ ጋዜጦች ከመጪው ጥር 30 1991ዓም ጀምሮ በሳምንት ሁለት ጊዜ እንዲወጡ የበላይ አካላት ትዕዛዝ መስጠታቸው ታወቀ። የኢህአዴግ ልሣኖች ከሆኑት መሃል በፋና ዲሞክራሲ ፣ የሚታተመው እፎይታ ጋዜጣ፣ አብዩታዊ ዲሞክራሲ፣ ማህቶት እና መሰል ጋዜጦች ይኸው መመሪያ ተፈጻሚ እንደሚሆንባቸው ታውቋል። እነዚህ ጋዜጦች በሣምንት ሁለት ጊዜ እንዲታተሙ ከመወሰኑ በፊት ብዙ ውዝግቦች ተነስተው እንደነበር ታው...
388
አፍሪካን ይለውጣሉ ተብለው ተስፋ የተጣለባቸው አዲሶቹ መሪዎች መስመር እየለቀቁ መሆኑ ተገለጠ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የነበረው ንፋስ ይገባበታል ተብሎ የማይታሰበው የሰመረ ግንኙነት የመበላሸቱ ሁኔታ በናፍቆት ሲጠበቅ የነበረው የዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ መምጣት የዓለምን ትኩረት ስልቦት ሽፍኖት ቆይቶ ነበር። ጨዋታው ከቀጠለ በኋላ ግን ሁላችንም ቁጭ ብለን በአዲስ አበባና በአስመራ መካከል ምን ሰይጣን ገባ የተፈጠረው ስህተት በትክክል ምንድን ነው በማለት እንድንመረምር አስገድዶናል። ባለፉት ቅርብ ዓ...
389
ኤርትራ ከባድ ጥቃት ለማድረስ እየዋዛች ነው ሪፖርታዥ የግንባሩ ሁኔታ የኤርትራው አመራር የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን የማስማሚያ ሃሳብና የማስፈፀሚያ ስልቶች ተቀብያለሁ፣ ግን ኢትዮጵያ ቀደም ሲል ተቀብያለሁ ስትል ቆይታ አሁን አልቀበለውም ያለች በመሆኗ ጦርነቷ አይቀሬ ነው በማለት በአንድ በኩል ለወቅቱ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ሊቀመንበርና ለአልጀሪያው ፕሬዝዱንት ለአብዱል አዚዝ ቡተፍ ሊካ አንድ አቋራጭ መንገድ ይፈልግለት ሲሉ አሳስበው በሌላውና እውነተኛው በሆነው ገጽታቻው ህዝባቸው ለጦርነት እንዲ...
391
በዮኤስ አሜሪካ ደጋፊነት ተዘጋጅቶ የኢራቅ ተቃዋሚ ድርጅት መሪዎችን ያገናኘና የድህረጦርነት መንግስት በምን መልክ መቋቋም እንዳለበት የሚያነጋግር መድረክ ትላንትና ማክሰኞ ዕለት የተከፈተው አሜሪካ ኢራቅን ላታስተዳድር ቃል በመግባት ሲሆን ከ 10 ቀናት በኋላ እንደገና ለመገናኘት በመስማማት ተጠናቋል። የመፅሐፍ ቅዱሱ ነቢዩ አብርሃም በተወለደባት ስፍራ በመገናኘት ከኢራቅ የተለያዩ ወገኖች የተወከለ መሪዎች በመጪው መንግስት የሀይማኖት ሚና ላይና አገሪቱን መልሶ በማቋቋም ረገድ ላይ ተወያዩ። ነገር ግን አን...
392
የእስራኤል የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ሲልቫን ሻሎም ሮብ ዕለት ከአቻቸው ከካታሪው ሼህ ሀመድ ቢን ጃሲም ጃባር አልታኒ ጋር በፖሪስ ሲነጋገሩ ካታር በመካከለኛው ምስራቅ የሠላም ሂደት ላይ ያላትን ሚና አስምረውበታል። ሻሎም በሰጡት የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደተመለከተው ትናንሾቹ የባህረሰላጤው መንግስታት በቅርቡ ከተሾሙት የፍልስጤም ጠቅላይ ሚኒስቴር መሀመድ አባስ ጋር ያላቸው ጥብቅ ግንኙነት የሰላሙ ሒደትን ያጐለምሳል። «እኛ የመካከለኛው ምስራቅ ሠላም ሂደትን ተወያይተንበታል» «አንድ ሠዓት ያለፈ ንግግር ካደረ...
393
የእስራኤልና የፍልስጤም መሪዎች በመካከለኛው ምሥራቅ የሰላም ዕቅድ ላይ ለመነጋገር በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ ዌስት ባንክ ውስጥ ማክሰኞ ዕለት በተቀሰቀሰው ግጭት የእስራኤል ወታደሮች 16 ዓመት የሆነውን አንድ ወጣት ገድለው ዕድሜአቸው 7 እና 9 የሆኑ ሁለት ሴቶች ልጆችን በከባድ ሁኔታ አቁስለዋል። ተኩሱ የተጀመረው የእስራኤል ጦር ሠራዊት እንደተናገረው ፍልስጤማውያን ድንጋይና እንዲፈነዳ ሆኖ የተዘጋጀ ጠርሙስ በመወርወራቸው የተነሣ አጸፋዊ እርምጃ ለመውሰድ ነውየተጀመረው የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ኤሪኤል ሻ...
394
«እርምጃው ትክክለኛ፣ ተገቢና ወቅታዊ ነው» ጠሚ መለስ የኢህአዴግን አስረኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ትናንት ታትሞ ከወጣዊ አብዮታዊ ዴሞክራሲ ልዩ ዕትም መጽሔት ጋር ጠሚ መለስ ዜናዊ ባደረጉት ቃለ ምልልስ እየተወሰደ ያለው እርምጃ የአገሪቱን ሕግና ሥርዓት ተከትሎ የተወሰደ በመሆኑ ትክክለኛ፣ ተገቢና ወቅታዊ መሆኑን ገልፀዋል። በቅርቡ የተከሰተው ክፍፍል፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ተቃውሞ፣ ከዱርዬዎች ዘረፋና ረብሻ ጋር በተያያዘ የታሰሩ ሰዎችና በአቶ ክንፈ መሰዋት ሳቢያ ያጋጠሙ ተደራራቢ ች...
395
ፕሬዝዳንት ነጋሶ ጊዳዳ ከኢህአዴግ ማዕከላዊ ምክር ቤት ስብሰባ መድረክ ለቀው ወጡ የኢህአዴግ ማዕከላዊ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ በኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ያካሄደውን ውይይት እያጠናቀቀ ባለበት ሂደት ፕሬዝዳንት ነጋሶ ጊዳዳ መድረኩን ለቀው መውጣታቸውን የኢህአዴግ ምክር ቤት አስታወቀ። የኦህዴድ ማዕከላዊና ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እንዲሁም የኢህአዴግ ምክር ቤትና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴእ አባል የሆኑት ዶር ነጋሶ ጊዳዳ ከመድረኩ ጫና ደርሶብኛል በሚል ምክንያት ራሴን ከምክር ቤቱ አባልነት አግልያለሁ በማለት ...
396
ፕሬዝዳንት ነጋሶ ጊዳዳ የሞዛምቢክን አምባሳደር አሰናበቱ ፕሬዝዳንት ነጋሶ ጊዳዳ የሥራ ጊዜያቸውን የፈጸሙትን በኢትዮጵያ የሞዛምቢክ አምባሳደር አሌክሳንድሬ ዛንዳሜላን ትናንት አሰናበቱ። በብሔራዊ ቤተመንግሥት በተከናወነው ሥነ ሥርዓት ላይ ለአምስት ዓመታት በኢትዮጵያ የቆዩት አምባሳደር ዛንዳሜላ የሁለቱን አገሮች ግንኙነት ለማጠናከር የተጫወቱትን ሚና ፕሬዝዳንት ነጋሶ ማድነቃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አስታውቋል። ሞዛምቢክ ባለፉት ጊዜያት በደረሰባት የጎርፍ አደጋ ኢኮኖሚዋ ቢጎዳም ከችግሩ...
397
የኦነግ ተጠርጣሪዎች 7 ዓመት ታስረው በነፃ ተለቀቁ የኦነግ አባልና ደጋፊ ናችሁ በሚል ጥርጣሬ ከአምስት እስከ ሰባት ዓመት ክስ ሳይመሰርትባቸው ታስረው ከሚገኙ የኦሮሞ ተወላጆች መሃል 550ዎቹ በነፃ መለቀቃቸውን በኦሮሚያ ክልል ከሚገኙ ታማኝ የዜና ምንጮች የተገኘው ዜና ያስረዳል። በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ውስጥ የኦሮሞ ነፃንት ግንባር ኦነግ አባልና ደጋፊ ናችሁ በሚል ጥርጣሬ ከመኖሪያ አካባቢያቸው በኦሕዴድ ካድሬዎችና የኮር አባላት እየታፈሱ በየእስር ቤቱ በማጐር ከአምስት እስከ ሰባት ዓመት ለሚደርስ ጊ...
398
ለኦነግ መጠናከር የሃይማኖት ሰዎች እጅ መኖሩ ተገለፀ በሀገራችን ኢትዮጵያ ተጨማሪ ጠላትና የሻዕቢያ ረዱት በመሆን አጋርነቱን እያረጋገጠ ለሚገኘው ኦነግ መጠናከርና ማደግ የሃይማኖት ሰዎች እጅ በድጋፍ ሰጪነት መኖሩ ተገለፀ። አንድ ዘገባ እንዱመለከተው፣ «እስከ ቅርብ ወራት ድረስ በሲዊዘርላንድ ለሻዕቢያ ድጋፍ ሰጪ ቢሮን የአደራጀውና የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እንቅስቃሴን የሚያደናቅፈው፣ በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን «እንግዱ ቤት» ይጠለል የነበረው በኤርትራ ኦርቶዶክስ ወጣት ቢሮ ኃላፊነት ሽፋን የነበረው ጴጥ...
399
የፓርላማው ውሎ ጥር 21 ቀን 1994 ዓም ጠሚር መለስ በሕዝብ ተወካዮች ምቤት ያቀረቡትን ሪፖርት፣ እንዲሁም ይህንን ሪፖርት መነሻ በማድረግ የመላው አማራ ህዝብ ድርጅት አመራር አባል ሻለቃ አድማሱ መላኩ ያነሱትን ጥይቄና አስተያየት ባለፈው ሣምንት ዘገባችን ማስነበባችን ይታወሣል። ከሻለቃ አድማሱ ቀጥሎ በምቤቱ አስተያየትና ጥያቄዎችን ያስከተሉት የአማራጭ ኃይሎችና የደቡብ ሕብረት ሊቀ መንበር የሆኑት ዶር በየነ ጴጥሮስ ናቸው። ዶር በየነ 32ቱን ገፅ ሪፖርት በአብዛኛው ገፅ በገፅ እየሄዱ ተችተውበታል።...
400
በእነ ፕሮፌሰር መስፍን ላይ ዓቃቤ ሕግ አስተያየት እንዲሰጥ ትዕዛዝ ተሰጠ ተማሪዎችን ለአመጽ ቀስቅሰዋል በሚል ክስ በተመሰረተባቸው ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያምና ዶር ብርሃኑ ነጋ ላይ በተጠየቀው ተጨማሪ ቀነ ቀጠሮና የዋስትና ጥያቄ አቃቤ ህግ አስተያየት እንዲሰጥበት የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ያዘ። የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ሰብስበው ተቃውሞ እንዲያስነሱ ቅስቀሳ አድርገዋል በተባሉት በሁለቱ ተከሳሾች አምስተኛ ወንጀል ችሎት ተለዋጭ ቀጠሮውን የሰጠው የኢፌዴሪ...
401
የእነ ፕሮፌሰር መስፍን ወማርያም ክስ ጉዳይ በዳኞች አለመሟላት ለሌላ ጊዜ ተላለፈ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት በፕር መስፍን ወልደማርያምና በዶር ብርሃኑ ነጋ የክስ መዝገብ ለትናንት ይዞት የነበረው ቀጠሮ የመሀል ዳኛው በመታመማቸው ምክንያት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ። ችሎቱ በሁለቱም ተከሳሾች በቀረበው የዋስትና ጥያቄ ትዕዛዝ ለመስጠትና በቀረበባቸው ክስ መቃወሚያ ለመቀበል ለትናንት ይዞት የነበረውን ቀጠሮ ለግንቦት ሃያ ስምንት ቀን 1993 ዓም እንዲተላለፍ አድርጓል። ችሎቱ ባለመሟላቱ ...
402
ቅንጅትና ኢህአዴግ በሞባይል የጽሑፍ መልዕክት እየቀሰቀሱ ነው በግንቦቱ ምርጫ ከፍተኛ ፉክክር በማድረግ ላይ ከሚገኙ የፖለቲካ ድርጅቶች መካከል የኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ግንባርና ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ የምረጡኝ ቅስቀሳቸውን በሞባይል መልዕክት ጭምር እያካሄዱ መሆናቸውን አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ገለጹ። ነዋሪዎቹ ትናንት እንዳስታወቁት ኢህአዴግና ቅንጅቱ የምረጡኝ ቅስቀሳቸውን ለደጋፊዎቻቸው በሞባይል የጽሑፍ መልዕክት በማስተላለፍ ላይ ሲሆኑ፣ መልዕክቱ የደረሳቸው ደግሞ ለሌሎች እንዲ...
403
ቅንጅት በጠሚኒስትር መለስ ላይ የመሰረተው ክስ በፌዴሬሽን ምቤት ተጣርቶ እንዲወሰን ብይን ሰጠ ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ላይ የመሰረተው ክስ በፌዴሬሽን ምክር ቤት የህግ መንግሥታዊ አጣሪ ጉባኤ ተጣርቶ እንዲወሰን ፍርድ ቤት ብይን ሰጠ። የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሁለተኛ ፍትሃብሄር ችሎት ትናንት ብይኑን የሰጠው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ግንቦት 7 ቀን 1997 ዓም ያወጡት መመሪያ ህገ መንግሥቱን የሚቃረን ነው። አዋጅ ቁጥር 383 የሰጠው...
404
የፊያሜታ መልዕክት የሻዕቢያን ሠርጐ ገቦች ጥቃት ለመግታት የመላው ሕዝብ ቁጥጥር ወሳኝ ይሆናል ከወታደራዊ ሳይንስ ትንታኔ አንፃር ሰርጐ ገቦች የአንዱን አገር ብሔራዊ ድንበር ተሻግረው ወደ ሌላ አገር የሚገቡ ዓላማቸው ባለው መንግሥት ላይ ሽብርና አለመተማመንን ለማስነሳት፣ ወታደራዊ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና የሕብረተሰብን መረጃዎች ለመሰብሰብ፣ የሕዝቡን ብሶትና ጥያቄዎች በመሰብሰብ ፕሮፓጋንዳ ለማሰራጨት በወታደራዊና በሲቪል ሰፈሮች በመገናኛዎችና በልዩ ልዩ የኢኮኖሚ ተቋማት ላይ አደጋ ለመጣልና እንዲሁም የ...
405
ሻዕቢያ የነፃነት በዓሉን ምክንያት በማድረግ በሺ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን አሰረ የሻዕቢያ መንግሥት 10ኛ የነፃነት በዓሉን ምክንያት በማድረግ በሺ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን አፍሶ በማጎሪያ ካምፖቹ ማሰሩን በአስመራ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ። ኤምባሲው ትናንት እንደገለጸው የሻዕቢያ መንግሥት አራት የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሰራተኞችን ጨምሮ በርካታ ኢትዮጵያውያንን ከመንገድና ከመኖሪያ ቤታቸው እያፈሰ በተለያዩ ፖሊስ ጣቢያዎች የቀበሌ ጽቤቶችና ማጎሪያ ካምፖች ውስጥ አስሯል። ሻዕቢያ የሚያካሂደውን ...
406
ሻዕቢያ በኢትዮጵያ ላይ ያሰራጨው ዘገባ መሰረተ ቢስና ከእውነት የራቀ ነው የኢትዮጵያ ሠራዊት በአሰብ ቡሬ መንገድ በጊዜያዊ የደህንነት ቀጣና ውስጥ በመግባት በኤርትራ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ጥቃት ሰንዝሯል ሲል ያሰራጨው ዘገባ መሰረተ ቢስና ከእውነት የራቀ መሆኑን አንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለሥልጣን ገለጹ። ባለሥልጣኑ ትናንት እንደገለጹት ጥቃቱን የፈፀመው የኤርትራ ተቃዋሚ ድርጅት የሆነው የቀይ ባሕር አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት መሆኑን ድርጅቱ ካወጣው መግለጫ ለማወቅ ተችሏል ብለዋል። ጥቃቱን ያ...
407
የኢትዮጵያ አንድነት ግንባር በአመስተርዳም ተወያየ የኢትዮጵያ አንድነት ግንባር ኢአግ ዋና ፀሃፊ አቶ መርሻ ዮሴፍ የወቅቱ የፖለቲካ ሃይሎች ተግባር የወያኔ መንግስት ለኢትዮጵያ ሕዝብ መሰረታዊ ጥያቄዎች ተገቢ መልስ እንዲሰጥ መወጠር ነው በማለት አስገነዘቡ። አቶ መርሻ ይህንን የገለጹት የኢትዮጵያ አንድነት ግንባር ኢአግ ድጋፍ ኮሚቴ በቅርቡ በአገራችን የተፈጠረውን ልዩ የጦርነት ሁኔታ አስመልክቶ በሆላንድ አገር ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በአምስተርዱም ከተማ ባዘጋጀው ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ንግግር ...