doc_id
stringlengths
1
5
text
stringlengths
42
393k
31207
ሊኦፖልድ ሴዳር ሴንጎር ሊኦፖልድ ሴዳር ሴንጎር ሊኦፖልድ ሴዳር ሴንጎር 19062001 የሴኔጋል የመጀመሪያው መራሄ መንግስት በመሆን ከ1960 እስከ 1980 ድረስ ያገለገሉ፣ ኔግሪቲዩድ የሚባለው ፍልስፍና ዋነኛ አቀንቃኝ የነበሩ እና በግጥሞቹም አድናቆትን ያተረፉ አፍሪካዊ የሥነጽሁፍ ሰው ናቸው። ሴንጎር የሴኔጋል ዋና ከተማ ከሆነችው ዳካር 70 ማይልስ ያህል በምትርቅ እና ጆአል ላ ፖርቱጊዝ ጆአል ፖርቱጊዛዊቱዋ በምትባል ትንሽ የአሳ አጥማጆች መንደር በ1906 ተወለዱ። አባታችው ነጋዴ ከሆኑ ሴሬር ከሚባሉ...
31208
ፍዮዶር ዶስቶየቭስኪ ፍዮዶር ዶስቶየቭስኪ ዶስቶየቭስኪ በሩስያ ዋና ከተማ ሞስኮ መስኮብ ውስጥ እኤአ በኦክቶበር 30፣ 1821 ተወለደ። አባቱ ቀድሞ የጦር ሰራዊቱ ሃኪም የነበረ ሲሆን በጣም ጠጪ እና ጢሰኞቹም ላይ ግፍን ያበዛ እንደነበር ይወሳል። ይህም በመሆኑ ይመስላል በገዛ ጭሰኞቹ እጅ ህይወቱ ሊያልፍ የበቃው። ዶስቶየቭስኪ በ1837 ዓም በቅዱስ ፒተርስበርግ የጦር ምህንድስና አካዳሚ ተመዝግቦ ትምህርቱን በመከታተል በመኮንንነት ተመርቋል። አንድ አመት ያህል በመንግሥት ሥራ ላይ ከቆየ በኋላ ሙሉ ግዜውን...
31209
በለስ በለስ ሮማይስጥ፦ Ficus ቅጠሉ ሰፋፊ፣ ነጭ ፈሳሽ ያለው፣ ፍሬው የሚበላ የእፅዋት ዝርያ ነው። ፍሬውም ደግሞ በለስ ወይም ዕጸ በለስ ይባላል። በእስልምና፣ በሕንዱ፣ በቡድሂስትና በጃይን እምነቶች፣ በለሶች የተቀደሱ ዛፎች ሆነው ይቆጠራሉ። በክርስትናም በአይሁድም በኩል በለስ ወይም ሾላ በብሉይ ኪዳን ብዙ ጊዜ ይጠቀሳል። ለምሳሌ በአንዳንድ ሥፍራ በትንቢት፣ በእግዚአብሔር መንግሥት ሰው ሁሉ በራሱ ወይንና በለስ ሥር እንደሚቀመጥ ይላል። በተጨማሪ በኦሪት ዘፍጥረት 3፡7 ዘንድ አዳምና ሕይዋን ከበለስ ...
31210
ላይ አፈር ላይ አፈር ላይ አፈር ላያፈር፣ ላይኛ አፈር፣ ላይኛፈር ከምድሩ አፈር ላዕላይ ንብብር ሲሆን ጥልቀቱ ከ5 እስከ 20 ሴንቲሜትር ድረስ ሊሆን ይችላል። ካርቦናዊ ቁስ አካልና ደቂቅ ዘአካል ጥቅን ሕዋስ በላይአፈሩ ውስጥ በመብዛቱ፣ ስሙ ደግሞ «ሕያው አፈር» ሊባል ይችላል። የምድር ሥነሕይወታዊ ተግባር በብዛት የሚፈጸምበት በዚህ አፈር ንብብር ነው። አትክልት በተለይ ሥሮቻቸውን በእርሱ ሰድደው ንጥረ ምግቦችን ከእርሱ ሊቀበሉ ይችላሉ። ላይ አፈር ከንፋስ ወይም ከጎርፍ የተነሣ ቢጠፋ ኖሮ ብዙ አትክልት...
31211
ራያ ራያ ማለት በስሜን ወሎ እና በደቡብ ትግራይ ሰፍሮ የሚገኝ ህዝብ ነው። ይህ ህዝብ የራሱ የሆነ ባህል እና ወግ፡ ማለትም እንደ አነጋገር፡ አለባበስ፡ የሰርግ ፡ የለቅሶ ስነስራአት ያለው ኩሩ እና ጀግና ህዝብ ነው። የራያ ህዝብ ከሚደነቅበትና ከሚያስደስት ባህሉ ሁሉም የእምነት ተከታዮች በተለይምሙስሊም ክርስቲያንሳይል በመቻቻል በህብረት በአንድ ላይ ተከባበሮ የሚኖር ህዝብ ሲሆን የአለባበስ ባህሉ ሌላው የሚደነቅለት አና ባህላዊ ጭፈራው ሲያዩት የሚያስግርም አና የሚያስድስት ነው። ከባህላዊ ጭፈራዎቹ እን...
31212
ኦጋም ጽሕፈት ኦጋም ጽሕፈት ኦጋም ጽሕፈት ለጥንታዊ አይርላንድኛ ቋንቋ የተጠቀመ አጻጻፍ ነበረ። በአይርላንድና በታላቅ ብሪታንያ ምዕራብ 400 ያህል በኦጋም ፊደል የተጻፉ ቅርጾች ተገኝተዋል። እነዚህ በብዛት ከ300 ዓም እስከ 1000 ዓም ድረስ በድንጋይ ወይም በእንጨት የተቀረጹ ናቸው። እንዴት እንደ ተለማ የሚገልጹ ሀሣቦች ብዙ ናቸው። በአይርላንድ ትውፊቶች ዘንድ በፌኒየስ ፋርሳ ወይም በኦግማ በጥንት ከባቢሎን ግንብ ቀጥሎ ተፈጠረ። ፊደሉ ለመቅረጫ በጣም ተስማሚ ነው። ለእያንዳንዱ ተናባቢ ድምጽ ከ1 ...
31213
ደበበ እሸቱ ደበበ እሸቱ ደበበ እሸቱ 1936 ዓም ተወልደው ስመ ጥሩ ተዋናይ ሲሆኑ በእሁኑ ግዜ የቅንጅት ቃል አቀባይ ሆነዋል። ከፊልሞቻቸው ሚናዎች መሃል በዓለም ከሁሉ የታወቀው በ Shaft in Africa 1973 እኤአ እንደ ዋሳ ነበረ። ዘሰይለር ፍሮም ጂብራልታር፤ ዘግሬቭ ዲገር፤እና ሌሎችም ትምህርታቸውን በተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ጨርሰው ወደ ደብረ ብርሃን መምህራን ማሰልጠኛ ትቤት ገቡ። ነገር ግን በ1953 ዓም በመንግሥቱ ነዋይእና በገርማሜ ነዋይ መሪነት በተካሄደው የመንግሥት ግልበጣ ሽብር ወ...
31214
ናጊብ ማህፉዝ ናጊብ ማህፉዝ ናጊብ ማህፉዝ በ1988 እኤአ በስነጽሁፍ የኖቤል ሽልማትን የተቀዳጀ ግብጻዊ ደራሲ ነው። ማህፉዝ ካይሮ ውስጥ ገማልያ በተባለው ሰፈር ዲሴምበር 11፣ 1911 እኤአ ተወለድ። የመጠሪያ ስሙን የወረሰው ሲወለድ አዋላጅ ሃኪም ከነበሩት ከፕሮፌሰር ናጊብ ማህፉዝ ፓሻ ነው። ማህፉዝ ለረጅም ዘመን በመንግስት መስሪያቤቶች ውስጥ ያገለገል ሲሆን በስነጽሁፉም ዘርፍ 34 ወጥ ልብወለዶች፣ ከ350 የሚዘሉ አጫጭር ታሪኮች፣ ከደርዘን በላይ የሲኒማ ድርሰቶች፣ እና አምስት ተውኔቶችን አበርክቷል።...
31215
ተስፋዬ ሳህሉ ተስፋዬ ሳህሉ ተስፋዬ ሳህሉ 1924 እኤአ ተወልደው በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ላይ ስመጥርና የተወደዱ ተዋናይና በተለይም የሕፃናትና የልጆች ተረተኛ ናቸው። ፕሮግራማቸው የልጆች ግዜ ከ1965 እኤአ ጀመሮ ታይቷል። ከዚያ ጀምሮ አባባ ተስፋዬ ተብለው አዲስ ስማቸውን ተቀበሉ። በ1998 ዓም ከ42 አመታት አገልግሎት በኋላ ከሥራቸው ተለቀቁ። አባባ ተስፋዬ በኢትዮጲያ ቴሌቪዢን የልጆች ግዜ ፕሮግራም ላይ የሚያቀርቡትን ተረት ሲጀምሩ የሚናገሩአት ታዋቂ ንግግር ደህና ናችሁ ልጆች የዛሬ አበባዎች የነገ ፍ...
31216
ስንዱ ገብሩ ወይዘሮ ስንዱ ገብሩ በሸዋ ክፍለ ሀገር በመናገሻ አውራጃ በአዲስ ዓለም ከተማ ጥር ፮ ቀን ፲፱፻፰ ዓም ተወለዱ። አባታቸው ታዋቂው ዲፕሎማት፣ የመጀመሪያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል ፕሬዘደንት፤ ጣሊያኖች ከኢትዮጵያ ከወጡ በኋላ ደግሞ የምክር ቤቱ ፕሬዘደንት የነበሩት በዳግማዊ ምኒልክ ሹመትም የመጀመሪያው የጎንደር ከተማ አስተዳዳሪ የነበሩት ከንቲባ ገብሩ ደስታ ሲሆኑ ታናሽ እህታቸው ደግሞ የውብዳር ገብሩ አሁን ታዋቂዋ ሙዚቀኛ እማሆይ ጽጌ ማርያም ናቸው። “… የተፈጠሩበትን ዘመን፣...
31217
አርባ ልጆች አርባ ልጆች የተባሉት በአንደኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የቱርክ መንግስት አርመናውያን ላይ ጭፍጨፋ ባካሄደበት ወቅት ወላጆቻቸውን በማጣት እና ከጭፍጨፋው ለማምለጥ ተሰደው በእየሩሳሌም የአርመን ገዳም ውስጥ ሲኖሩ ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ያኔ አልጋወራሽ ራስ ተፈሪ አግኝተው ወደ ኢትዮጵያ አምጥተው ያሳደጉዋቸው 40 አርመናውያን ልጆች ናቸው። በልጆቹ የሙዚቃ ችሎታ የተደመሙት አፄ ኃይለሥላሴ በእየሩሳሌም የአርመን ፓትርያርክን ፍቃድ ካገኙ በኋላ ልጆቹን ወደ ኢትዮጵያ ወስደው ተጨማሪ የሙዚቃ ስልጠና እ...
31218
መኪና መኪና መኪና የሚለው ቃል macchina ከሚለው የጣሊያንኛ ቃል የተወረሰ ቃል ሲሆን፣ ወይም አውቶሞቢል ከሥፍራ ወደ ሥፍራ በመንኮራኩር ላይ በሞቶር የሚነዳ ተንቀሳቃሽ አይነት ነው። ስዎችም ሆነ ዕቃ በመንገዶች ላይ ለማዛወር ይጠቀማል። በ1999 ዓም፣ በመላ ዓለም ውስጥ የመኪናዎች ቁጥር 800 ሚሊዮን ያህል ነበር። በተለምዶ «መኪና» የሚለው ስም የሚሰጠው ከዶቅዶቄ ትልቅ፣ ከካሚዎንም ወይም ከአውቶቡስ ትንሽ ለሆነ ባለሞቶር ተሽከርካሪ ነው፤ አንዳንዴ ግን ቀላል ካሚዎኖች ከመኪናዎች ጋር መመደብ ይቻላ...
31219
ቺኑዋ አቼቤ ቺኑዋ አቼቤ በሙሉ ስሙ ሲጠራ አልበርት ቺኑዋሉሞጉ አቼቤ ይሰኛል። ምናልባትም ናይጄሪያ ካሉዋት ምርጥ ፀሃፍት ዝርዝር ውስጥ በአንደኛ ደረጃ የሚሰለፍ ሳይሆን አይቀርም። በ1930 እኤአ ኦጊዲ በተባለች የናይጄሪያ ግዛት ከአዜያህ ኦካፎ እና ከጃኔት አቼቤ ተወለድ። በ1953 እኤአ ከለንደን ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያ ዲግሪውን አግኝቷል። ለአቼቤ ድንቅ ሥራ የተባለለት Things Fall Apart 50 ወደሚሆኑ የአለም ቁዋንቁዋዎች የተተርጎመ ሲሆን ወደ 10000000 ቅጂዎች እንደተሸጡለት ይነገራል። አ...
31220
ሱሳ ሱሳ ሱሳ ፋርስኛ፦ شوش ሹሽ፤ ዕብራይስጥ፦ שושן ሹሻን፤ ጥንታዊ ግሪክ፦ Σέλεύχεια ሰለውከያ፤ ሮማይስጥ፦ Seleucia ad Eulaeum ሰለውኪያ አድ ኤውላዩም በኢራን በ የሚገኝ እጅግ ጥንታዊ ከተማ ነው። በ1997 ዓም 64960 ገደማ ሰዎች ይኖሩበት ነበር። ሱሳ በድሮ ጊዜ የኤላም መንግሥት ዋና ከተማ ነበረ። በዓለሙ ከሁሉ ጥንታዊ ከተሞች አንድ ነው። በኤላምኛ ከተማው ሹሻን ተባለ። በሱመርኛ መዝገቦች ይታወቃል። ለምሳሌ ኤንመርካርና የአራታ ንጉስ በተባለው ትውፊት ለኡሩክ አምላክ ለኢናና...
31221
ሐማዚ ሐማዚ ሐማዚ ምናልባት በ2420 ዓክልበ ገዳማ የነበረ መንግሥት ሲሆን በምዕራብ ዛግሮስ ተራሮች ከኤላምና ከአሦር መካከል እንደተገኘ ይታሥባል። ሐማዚ ለሥነቅርስ ጥናት መጀመርያ የታወቀው በዚህ ቦታ ላይ የኪሽ ንጉሥ ኡቱግ ወይም ኡሁብ ድል የሚመዝገብ በጥንታዊ ባለማዕዘን ኩኔይፎርም ጽሕፈት የተጻፈ ጽላት ሲገኝ ነበር። በሱመር ንገሥታት ዝርዝር መሠረት የሐማዚ ንጉሥ ሀዳኒሽ ኪሽን ካሸነፈ በኋላ 2243 ዓክልበ ግ በሱመር ላይ ላየኛነት ያዘ። እሱ ግን በተራው በ2215 ዓክልበ ግ በኡሩክ ንጉስ በኤን...
31222
ቡና ቡና የተክል አይነትና ከዚህ ተክል ቡን የሚወጣው መጠጥ ነው። መጀመርያ የታወቀው በኢትዮጵያ ሲሆን በዓለሙ ልሳናት ስሙ የተነሣ ለምሳሌ እንግሊዝኛ፦ coffee ኮፊ ምናልባት ከድሮው የከፋ መንግሥት ሊሆን ይችላል። በአንድ ትውፊት መሠረት በመጀመርያ ያገኘው ሰው ካልዲ የተባለ አንድ ኢትዮጵያዊ እረኛ ፍየሎቹ ፍሬውን በልተው ሲጨፍሩበት ነበረ። የቡናው የስን ፍጥረት ስሙ Coffea arabica ካፊ ኣራቢካ ሲሆን የዚህ የኢትዮጵያ ቡና ዘር በጣዕሙ ጥሩነት የተነሳ በጣም ተወዳጅ ነው። በደራሲው ዊሊያም ...
31223
አቤ ጉበኛ አቤ ጉበኛ አቤ ጉበኛ ፲፱፻፳፭ ዓም በባሕርዳር አካባቢ፣ ይስማላ ጎጃም ተወልደው ፲፱፻፸፪ ዓም አዲስ አበባ ላይ አረፉ። ባለቅኔ፤ ደራሲና ገጣሚ የነበሩት አቤ ጉበኛ በስድስት ዓመት ፊደል ቆጥረው ንባብ ከተማሩ በኋላ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርት ሲከታተሉ ቆዩ። ከዚያም ወደ ደንጎላ ሄደው በቢትወደድ መንገሻ ጀምበሬ ትምህርት ቤት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን አጠናቀው ወደ አዲስ አበባ በመምጣት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አረናቀዋል። አቤ ጉበኛ የመጀመሪያ ሥራቸው...
31224
የመንግሥት ሃይማኖት የመንግሥት ሃይማኖት በአንድ መንግሥት ዘንድ የተመሠረተ ሃይማኖት ወይም ይፋዊ እምነት ነው። ይህ ሲባል ግን የተመሠረተው ሃይማኖት መሪዎች የመንግሥቱ መሪዎች አይደሉም፤ እንደዚህ ከሆነ ግን ያው መንግስት «Theocracy» ይባል ነበር። የተመሠረተው ሃይማኖት ማለት በመንግሥት የተደገፈው እምነት ወይም ትምህርት የሚመለከት ነው። መንግሥት ሃይማኖቱን እስከ ምን ደረጃ ድረስ እንደሚደግፈው በየአገሩ ይለያያል። ከቃል ድገፋ ብቻ እስከ ገንዘባዊ እርዳታ ድረስ ሊሆን ይችላል። በአንዳንድ አገር...
31225
ግብረ ስጋ ግንኙነት ግብረ ስጋ ግንኙነት ወይም ሩካቤ ስጋ ማለት በሴትና በወንድ መካከል ለስሜት እርካታ የሚደረግ ግንኙነት ወይም ፍቅር መሥራት ነው። ይህም ለመባዛት ወይም ለመዋለድ አስፈላጊ ከመሆኑ በላይ የወሲብን እርካታዊ ፍላጎት ለማሟላት ሊሆን ይችላል። በሥነ ሕይወት ዘርፍ ሲታይ፣ ወሲብ፣ የእንስትን ሴትን እና የተባእትን ወንድን ዘር በማዋሃድ ወይንም በማዳቀል፣ የፍጡራን ዝርያ species፣ ከአሮጌ ወደ አዲስ እየታደስ፡ በቅጥልጣይ ረገድ ለረዥም ጊዜ እንዲቆይ የሚያስችል፣ ተፈጥሮ የቸረችው ተፈጥሯ...
31226
አካድ አካድ በሱመራውያን ነገሥታት ዝርዝር መሠረት አካድ አጋደ የገነባው ታላቁ ሳርጎን ነበረ። ሆኖም ከተማው ከሳርጎን ቀድሞ በኡሩክ ንጉሦች ኤንሻኩሻና እና ሉጋልዛገሢ ዘመናት እንደተገኘ ከጽሕፈቶች ይታወቃል። በመጽሐፍ ቅዱስም ዘፍ 10፡10 ዘንድ ናምሩድ ከሠሩት ከተሞች 1ዱ መሆኑ ይቆጠራል። ከዚህ በላይ ኤንመርካርና የአራታ ንጉስ በተባለው ሱመራዊ አፈ ታሪክ፣ ልሣናት የተደባለቁባቸው አገሮች ሹባር፣ ሐማዚ፣ ሱመር፣ ኡሪኪ የአካድ ዙሪያ እና የማርቱ አገር በመባላቸው፤ ይህም የአካድን ጥንታዊነት ይመሰክራል...
31227
ሊኑክስ ሊኑክስ ሊኑክስ በነፃ ከሚገኙ ሶፍትዌሮች ግንባር ቀደም ተብሎ ሊጠቀስ የሚችል ነው። የምንጭ ኮድንም ማለትም ሊኑክስ የተጻፈበትን ኮድ ተጠቃሚው ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ሊቀይረው፣ ሊጠቀመው ብሎም እንደገና ሊያሰራጨው ይችላል። የሊኑክስ ከርነል ለመጀመሪያ ጊዜ በ17 ሴፕቴምበር 1991 እኤአ ለህዝብ ቀረበ። ይኸውም ለኢንቴል x86 ፒሲ አርክቴክቱር የተሰራው ነበር። ከዚሀም በተጨማሪ ከርነሉ ጠቃሚ ስርአተ ክወና እንዲሆን ከጂኤንዩ ፕሮጀክት በላይብራሪዎችና በሲስተም ዩቲሊቲዎች የታገዝ ነበር። ቆይቶም ጂ...
31228
እርሾ እርሾ በስነ ሕይወት የሚገኝ ጥቃቅን ነፍሳት ሲሆን የእንጉዳይ ዘመድ ነው። ለረጅም ዘመን ይህ ልዩ ሻጋታ አይነት ዳቦ ወይም አረቄ በመቡካት እጅግ ጠቅሟል። እርሾ መጀመርያ የተጠቀመበት ወቅት ባይታወቅም በጥንታዊ ግብፅ ዳቦ በመጋገር እንደ አገለገለ በሃይሮግሊፍ መዝገብ ተገኝቷል። ምናልባት በቀን ሐሩር ስንዴና ውኃ አንድላይ ሲቀመጡ በእህሉ ውስጥ የሚኖረው የተፈጥሮ ሚክሮብ መቡካት ጀመረ። ውጤቱ ከቂጣ ይልቅ ለሥላሣ የሆነ ሁኔታ ነበር። የዳቦ እርሾ ታሪክ በእንግሊዝኛ
31229
የኡርናሙ ሕግጋት የኡርናሙ ሕግጋት የኡርናሙ ሕገጋት እስከ ዛሬ ከተገኙት መንግሥታዊ ሕግ ሰነዶች መኃል ከሁሉ ጥንታዊ የሆነው ሰነድ ነው። ሰነዱ የተጻፈው ከክርስቶስ ልደት ከ1983 ዓመት በፊት ኡልትራ አጭር በሱመርኛ ቋንቋ ነበር። በመቅደሙ የኡር ንጉሥ ኡርናሙ ስም ቢጠቀስም አንዳንድ ሊቃውንት ግን ምናልባት የልጁ የሹልጊ ሥራ ይሆናል ብለው ያምናሉ። መጀመርያ የተገኘው ቅጂ በተሰበረ ጽላት በኒፑር ፍርስራሽ ሲሆን፣ በ1944 ዓም ሊቅ ሳሙኤል ክሬመር አስተረጎሙት። ሆኖም ሰባራ ክፍሎች እንደ መሆኑ ከሕጎቹ...
31230
አማ አታ አዪዶ አማ አታ አዪዶ ክሪስቲና አማ አታ አዪዶ በማርች 23፣ 1942 እኤአ ጋና ውስጥ ተወለደች። ትምህርቷን በዌስሊ የልጃገረዶች ትምህርት ቤት፣ በመቀጠልም በጋና ዩኒቨርስቲ ተከታትላ በ1964 ዓም በእንግሊዝኛ ቋንቋ የመጀመሪያ ዲግሪዋን ተቀብላለች። የመጀመሪያ የድርሰት ስራዋ የሆነውን «The Dilemma of a Ghost»ን በዚያ ዓመት ለማጠናቀቅ የበቃች ሲሆን ይሄው ድርሰቷ በሎንግማን አሳታሚ ድርጅት አማካይነት በቀጣዩ ዓመት ታትሞላታል። አዪዶ በ1982 የጋና የትምህርት ሚኒስትር ሆና ብትሾ...
31231
ጨው ጨው ማለት በጥንተ ንጥር ረገድ በተለይ NaCl ሶዲየም ክሎሪድ ነው። የተሠራው ከሶዲየም Na እና ክሎሪን Cl ንጥረ ነገሮች ነው። ይህ ማዕደን በምግብ ውስጥ ይበላል። ጣዕም ለመጨመር እንዲሁም የምግብን ኹኔታ ለማስጠበቅ በጣም ይጠቅማል። ጨው የምግብን ኹኔታ ስለሚያስቆይ፣ ሥልጣኔ በግብጽ ወዘተ እንዲጀመር የጨው ጥቅም አይነተኛ ሚና ነበረው። ከጥቅሙ የተነሣ በ1 ወራት ውስጥ የሚበላሽ ምግብ እንግዲህ ከወራቱ በኋለ እንዲቆይ ተደረገ። ከዚህም በላይ፣ እንዲህ ያለ ምግብ በረጅም ጉዞ ላይ እንደ ሥንቅ መ...
31232
ጎጃም ጎጃም በሰሜን ምራብ ኢትዮጵያ የሚገኝና በአባይ ወንዝ ተከቦ የሚገኝ ባህር ዳርን ፍኖተ ሰላምን አገው ምድርን መተከልን ፓዊ ቆላደጋዳሞትን፣ አቨፈርን ደብረ ማርቆስን ሞጣና ብቸና አውርጃዎች እና በነዚ ውስጥም ከ 35 በላይ ወረዳዎችን ይዞ የሚገኝ የራሱ ስርዎ መንግስት የነበረው ከፍለሃገር ነው። ጎጃም በጢፍ አምራችነት ከታወቁት የኢትዮጵያ ክልሎች ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል። በተለይ የአዴት ጢፍ በባህር ዳር ጎንደር ደሴ እና መቀሌ ነዋሪዎች ዘንድ በስፋት የታወቀ እና ተወዳጅም ነው። እንዲሁም በምስራቅ ...
31233
ናምሩድ ናምሩድ በመጽሐፍ ቅዱስ እንዲሁም በአፈ ታሪክ፣ ናምሩድ ዕብራይስጥ נִמְרוֹד ኒምሮድ የኩሽ ልጅ፣ የካም ልጅ ልጅ እና የኖህ ልጅልጅልጅ ሲሆን የሰናዖር ንጉሥና በእግዚአብሔር ፊት ኃያል አዳኝ ይባላል። በመጽሐፍ ቅዱስ ስሙ የሚገኘው በኦሪት ዘፍጥረት 10፣ በዜና መዋዕልና በትንቢተ ሚክያስ ብቻ ነው። እነዚህ መጻሕፍት ስለ ናምሩድ ብዙ ባይነገሩንም፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ ስለሱ ያሉት ትውፊቶች ግን በርካታ ናቸው። ከነዚህም ትውፊቶች መካከል ከሁሉ የታወቀው የባቢሎን ግንብ እንዲገነባ ያዘዘ መሆኑ ነ...
31234
ሱመር ሱመር ጽሕፈት በመፍጠሩ የታሪክ መጋረጃ ሲከፈት፣ ሱመራውያን በደቡብ መስጴጦምያ ከጤግሮስና ኤፍራጥስ ወንዞች መኃል፣ የዛሬው ኢራቅ ይገኙ ነበር። ላዕላይነቱ አሁን እንደ «ቅዱስ የሮማ መንግሥት ንጉስ» የመሰለ ማዕረግ ሆኖ ነበር። ከከተማአገሮቹ የማሪ ንጉስ ማዕረጉን ከያዘ፣ ከዚህ ወደ አክሻክ ንጉሥ ተዛወረ። የአክሻክ ንጉስ ፑዙርኒራሕ ክፉ ሆኖ፣ የሱመር ቄሳውንት መንግሥቱን ለአንዲት ሴት ባለ ጠጅ ቤት ለኩግባው ንግሥት ሆና እንዳሸለሙላት የሚል ሰነድ አለ። በዚህም ዘመን በላጋሽ፣ ከአንድ ክፉ ንጉ...
31235
ሐይክ ሐይክ አርሜንኛ፦ Հայկ በአርሜኒያ አፈ ታሪክ ውስጥ የአርሜናዊ ህዝብ መስራች ነበረ። የሱ አፈታሪክ በታሪክ ጸሐፊው ሙሴ ሖሬናዊ 5ኛ ክፍለ ዘመን መጽሐፍ የአርሜኒያ ታሪክ በተለይ የሚገኘው ነው። በሙሴ ሖሬናዊ ዘንድ ሐይክ የያፌት ልጅ ጋሜር ልጅ የቶርጎም ቴርጋማ ልጅ ነው። ሐይክ ደግሞ የሐይካዙኒ ሥርወ መንግሥት መስራች ይባላል። በታሪክ ጸሐፊው ጇንሸር ዘንድ፣ ሐይክ የሰባት ወንድማማች መስፍን ሆኖ፣ መጀመርያ ዓለሙን በሙሉ እንደ ንጉሥ ለነገሠው ለረጅሙ ሰው ለናምሩድ ያገልግል ነበር። ሐይክ ደ...
31236
ግዕዝ ግዕዝ በአፍሪካ ቀንድ በኢትዮጵያና በኤርትራ በጥንት የተመሠረተና ሲያገለግል የቆየ ቋንቋ ነው። የግዕዝ አመጣጥ በግምት የዛሬ 3 ሺህ ዓመት ከየመን እና ደቡብ አረቢያ በመነሣትና ቀይ ባሕርን በመሻገር ሰሜን ኢትዮጵያ ውስጥ ከሰፈሩ የተለያዩ የሳባውያን ነገዶች ቋንቋና በጊዜው ሰሜን ኢትዮጵያ ይነገሩ በነበሩ ቋንቋዎች ዘገምተኛ ውኅደት ነው። በአክሱም መንግሥትና በኢትዮጵያ መንግሥት መደበኛ ቋንቋ ነበር። በግዕዝ ጽሕፈት 26 ፊደላት ብቻ ይጠቀሙ ነበር፤ እነርሱም፦ በብሪቲሽ ላይብሬሪ የእንግሊዝ አገር ብ...
31237
ሁኖርና ማጎር ሁኖርና ማጎር ሁኖርና ማጎር በሀንጋሪ አፈ ታሪክ ዘንድ የሁኖችና የሀንጋራውያን ማውጃሮች ቅድማያቶች ናቸው። በአንዳንድ መጻሕፍት መሠረት ለምሳሌ የመካከለኛ ዘመን ላቲን ዜና መዋዕል ጌስታ ሁኖሩም ኤት ሁንጋሮሩም፤ መንታ መሳፍንት ሁኖርና ማጎር የታና ልጅ መንሮትና የሚስቱ ኤነሕ ልጆች ነበሩ። ይህ መንሮት 200 አመታት ከማየ አይህ በኋላ በባቢሎን ሥልጣን እንደያዘ ሲባል መታወቂያው ደግሞ የኩሽ ልጅ ናምሩድ መሆኑ ይተረካል። መንታዎቹም በፋርስ አገር ተወልደው በአዞቭ ባሕር አጠገብ ለ5 አመት...
31238
የጄኖቫ ቅዱስ መልክ የጄኖቫ ቅዱስ መልክ በአንድ ትውፊት ዘንድ፣ ኢየሱስ በሕይወቱ ስብከት ሳለ የኤደሣ በሶርያ ንጉሥ 5 አብጋር በበሽታ ታምመው ኢየሱስ መጥቶ እንዲፈውሳቸው አንድን መልእክተኛ ሐናን ወደ ኢየሩሳሌም ልከው ነበር። ኢየሱስ ወደ ኤደሣ ለመሔድ ግዜ ስላልነበረው፣ ባንድ ጨርቅ ላይ መልኩን በተአምር አሳተመና ሐናን ስዕሉን ይዞ ወደ ንጉሡ እንዲሔድ ላከው። እንዲህም ሆኖ አብጋር ይህን ስዕል አይተው ከበሽታቸው ተፈወሱና ወዲያው ምዕመን ሆኑ። ስዕሉ ደግሞ በተአምር በመፈጠሩ ያለ እጅ የተሠራው ተብ...
31239
ፖርቱጋል ፖርቱጋል የፖርቱጋል የጥንት ስም ሉዚታኒ ነው። በመጀመሪያም በአገሪቱ የነበሩት ሕዝቦች ሴልቶ ኢቤሪክ የሚባሉ የህንዶኤውሮፓዊ ወገን ሆነው በኋላ ወደ ላቲንነት በልማድና በኑሮ በሃይማኖትም የተለወጡ ናቸው። የፖርቱጋል ሕዝብ በጀርመንና በኖርማንዲ በሮማውያንና በዐረቦች ሞሪ ማውሪታኒ ከሚባሉ በአፍሪካ ሰሜን ሕዝብና በዕብራውያንም የተቀያየጠ ነው። ነገር ግን እነዚህ ሁሉ ባንድነት ሰፊ ዘመን በሮማ መንግሥት ስለ ተገዙ በዘርም በልማድም አብዛኛውም ወደ ላቲንነት ተለውጠዋል። የሮማ መንግሥት ከወደቀ በኋ...
31240
ወላይታ ወላይታ በቀድሞ ሲዳሞ ጠቅላይ ግዛት ባሁኑ ደቡብ ክልል የሚገኝ ና የራሱ የሆነ ቋንቋና ባህል ያለው ሕዝብ ሲሆን ከሲዳማ፡ ከከምባታ፡ ከሃዲያና ተመሳሳይ ቋንቋ ከሚናገሩ ከኩሎ ኮንታ ከጎፋና ጋሞ ሕዝብ ጋር ይዋሰናል። የወላይታ ዞን አስራ ሁለት ወረዳዎች አሉት። እነሱም፦ 1ኛ ዳሞት ጋሌ ዋና ከተማው ቦዲቲ፡ 2ኛ ዳሞት ወይዴ ዋና ከተማው፦ በደሳ፡ 3ኛ ቦሎሶ ሶሬ ዋና ከተማው አረካ፡ 4ኛ ሁምቦ ዋና ከተማው ጠበላ፡ 5ኛ ኦፋ ዋና ከተማው ገሱባ፡ 6ኛ ሶዶ ዙሪያ ዋና ከተማው ሶዶ፡ 7ኛ ኮይሻ ዋና ...
31241
ዶር ይስሓቅ ዳልኬ ዶር ይስሓቅ ዳልኬ ዶር ይስሓቅ ዳልኬ በ1949 እኤአ በወላይታ ተወለዱ። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በጄኔራል ዊንጌት ትቤት በከፍተኛ ውጤት በመጨርሳቸው ከጃንሆይ የወርቅ ሰዓት በመሸለም ተመርቀው በአዲስ አበባ ሕክምና ፋካሊቲ ትምህርታቸውን በመቀጠል የዶክተሬት ድግሪያቸውን እንዳገኙ ጥቂት ወራት በጎንደር እንዳገለገሉ ለከፍተኛ ትምህርት ወደ አሜሪካን አገር ሄደው ትምህርታቸውን በአጥጋቢ ሁኔታ ጨርሰው እካሁንም ኑሮአቸውንም በአሜሪካን አገር በፍሎሪዳ አርገዋል። ዶር ይስሃቅ ባሁኑ ጊዜ ...
31242
ሌቱም አይነጋልኝ ሌቱም አይነጋልኝ ሌቱም አይነጋልኝ በውቤ በረሃ በ ፲፱፻፶፯ ዓም ተጀምሮ በፈረንሳይ አገር ኤክስ አን ፕሮቫንስ የተፈጸመ መጽሐፍ ነው። ደራሲው ስብሐት ገብረ እግዚአብሔር መጽሐፉ እንዲታተም እሱ ደንታ ባይኖረውምበመጽሐፉ ውስጥ እንደጠቀሰው «እኔ ኮ ያደረብኝ ለዘብተኛ ልዝብ ዛር በበቂ ደሞዝና ትርፍ ስኣት በአሁኑ ሰዓት በመጀመሪያ እነዚያ ወሲባዊ ቃላቶችን «ለስለስ» ባሉ ቃላቶች በመተካት ለአንባቢያን እንዲደርስ መጽሐፉ ታትሞ ለገብያ የቀረበ ሲሆን በመቀጠልም በአገራችን አቆጣጠር በ1999...
31243
ቋንቋ ቋንቋ የድምጽ፣ የምልክት ወይም የምስል ቅንብር ሆኖ ለማሰብ ወይም የታሰበን ሃሳብ ለሌላ ለማስተላለፍ የሚረዳ መሳሪያ ነው። በአጭሩ ቋንቋ የምልክቶች ስርዓትና እኒህን ምልክቶች ለማቀናበር የሚያስፈልጉ ህጎች ጥንቅር ነው። ቋንቋዎችን ለመፈረጅ እንዲሁም ለመክፈል የሚያስችሉ መስፈርቶችን ለማስቀመጥ ባለው ችግር ምክንያት በአሁኑ ሰዓት በርግጠኝነት ስንት ቋንቋ በዓለም ላይ እንዳለ ማወቅ አስቸጋሪ ነው። እንደ ተለያየ መስፈርት ግምት ከ3000 እስክ 7000 ቋንቋዎች በአለም ላይ እንዳሉ ስምምነት አለ።
31244
ጃቫ ጃቫ ጃቫ Java ስነ ፍርገማ በቅርብ ታዋቂነትንና ተቃባይነትን እያገኘ ከመጡ ፍርገማ ቋንቋዎች አንዱ ነው። ጃቫ ተመራጭ ካደረጉት ዋና ባሀሪዎቹ አንዱ በፕላትፎርም አለመወሰኑ ነው። ይሀም ማለት በጃቫ የተጻፈ ትግበራ አፕሊኬሽን የጃቫ ቨርቹአል ማሽን ባለበት ሁሉ መሮጥ መቻሉ ነው። ስለዚህ በጃቫ ስራአት የሚጻፍ ኮድ በመጀመሪያ ኮምፓይል ከተደረገ በኋላ ኮምፓይለሩ አዲስ ዶክመንት ይፈጥራል። ይህም ማለት ኮምፓይለሩ የሚፈጥረው አዲስ ዶክመንት በጃቫ ባይት ኮድ ሲሆን የሚተገበረው ኢምፕልመንት የሚደረገው በ...
31245
አርፋክስድ አርፋክስድ አርፋክስድ ዕብራይስጥ፦ אַרְפַּכְשָׁד አርፓክሻድ፣ አረብኛ፦ أرفخشذ አርፋሕሻድ በኦሪት ዘፍጥረት ምዕ 10 ዘንድ የሴም ልጅና የቃይንም አባት ነው። በዕብራይስጥ ትርጉም ግን የቃይንም ስም የለምና በቀጥታ የሳላ አባት ነው። በመጽሐፈ ኩፋሌ 8፡15 አማርኛ ትርጉም የሴም ልጆች ኤላም፣ «አቡር»ና አርፋክስድ ከማየ አይህ ፬ኛ አመት በኋላ ተወለዱ ሲል፣ በሌሎቹ ትርጉሞች እንደ ግሪክ፣ ሶርያ ግን ኩፋሌ ከዘፍጥረት ጋር በመስማማት በ«አቡር» ፈንታ «አሹር» አሦር አለው ዘፍ 10...
31246
የአርዛፕ ድንጋዮች የአርዛፕ ድንጋዮች የአርዛፕ መልህቅ ድንጋዮች በምሥራቅ ቱርክ አገር ተራራዎች የሚገኙ 12 እጅግ ታላቅ ድንጋዮች ናቸው። እነዚህ ድንጋዮች በአንዳንድ ክርስቲያን መምህር በተለይም በአቶ ዴቪድ ፋሶልድ እምነት የኖህ መርከብ መልህቅ ድንጋዮች መሆናቸውን ያምናል። ይህ እምነት እያንዳንዱ ድንጋይ በጫፍ ላይ ትልቅ ቀዳዳ ስላለበት ነው። ለኖህ መርከብ መልህቅ እንደ ነበረው የሚል ሀሣብ በቁራን ውስጥ ተገኝቷል። በተጨማሪም በሱመራዊው አፈ ታሪክ ጊልጋመሽ፣ ስለ ማየ አይህ ሲተረክ መልህቅ ድንጋዮች...
31247
የኅሊና ነፃነት የኅሊና ነፃነት የኅሊና ነፃነት ማለት ማንኛውም ግለሠብ ምንምን ሀሣብ፣ እምነት ወይም አስተያየት በጽናት ለመያዝ የሚረጋገጥበት ነጻነት ነው። የሌላ ሰዎች እምነት ምንም ቢሆንም፣ ይህ ነጻነት ለየግለሠቡ ጽኑእ ሆኖ ይቆጠራል። መግለጫ የኅሊና ነጻነት ፍሬ ነገር እያንዳንዱ ግለሠብ ለራሱ የቱን እምነት ለመምረጥ ስለሚሰጥ፣ የሃይማኖት ነጻነት ጽንሰ ሐሳብ ከዚህ ጋር ተያይዟል። በአንዳንድ ህብረተሠብ ወይም መንግሥት በተግባር የሃይማኖት ነጻነት ወይም የእምነት ነጻነት ባይከበርም፣ በሌሎች ህብረተ...
31248
ፐርል በክ ፐርል በክ ፐርል በክ በስነጽሁፍ የኖቤል ተሸላሚ 1938 ለመሆን የበቃች አሜሪካዊት ደራሲ ናት። በክ ጁን 26 ቀን 1982 ዓም በምእራብ ቨርጂኒያ ሂልዝቦሮ በተባለ ቦታ ተወለደች። ወላጆቿ ፕሬስብቴርያዊ ሚሲዮኖች የነበሩ ሲሆን ብዙውን የሚሲዮን ስራቸውን በቻይና ነው ያሳለፉት። በዚሁ የተነሳ በክ ከልጅነቷ ጀምሮ እንግሊዝኛን ብቻ ሳይሆን ቻይንኛንም አቀላጥፋ ትናገር ነበር። ትምህርቷን በ1914 እንዳጠናቀቀች ወደ ቻይና ነው ያቀናችው። በ1915 የወደፊት ባሏ ከሚሆነውን ከጆን ሎሲንግ በክ ጋር ተ...
31249
ልድያ ልድያ አሦርኛ፦ ሉዱ፤ ዕብራይስጥ፦ לוד ሉድ፣ ግሪክ፦ Λυδία ሉዲያ በምዕራብ ትንሹ እስያ የተገኘ ታሪካዊ አውራጃና መንግሥት ነበር። በታወቀበት ዘመን ዋና ከተማው ሰርዴስ ሆነ። በአንድ ወቅት የትንሹ እስያ ምዕራብ ክፍል በሙሉ የሉድያ ግዛት ነበረ። በኋለ ዘመን ደግሞ ልድያ የሮማ መንግሥት ጠቅላይ ግዛት ነበረ። መሐለቅ መጀመርያ የተፈጠረው በልድያ ክበ 660 አመት ያሕል እንደ ነበረ ይታመናል። ቋንቋቸው ሉድኛ በሕንዳዊአውሮፓዊ ቋንቋዎች ቤተሠብ ሲሆን በዚሁም ቤተሠብ ውስጥ የአናቶላዊ ቅርንጫፍ...
31250
አሞራውያን አሞራውያን አሞራውያን ሱመርኛ፦ ማርቱ፤ አካድኛ፦ አሙሩ፤ ግብጽኛ፦ አማር፣ ዕብራይስጥ፦ אמורי አሞሪ በጥንት ከኤፍራጥስ ወንዝ ወደ ምዕራብ የኖረ ሕዝብ ነበረ። «የማርቱ አገር» ከሁሉ ጥንታዊ በሆኑት ሱመራዊ ምንጮች ለምሳሌ በኤንመርካርና የአራታ ንጉሥ ወይም በኤብላ ጽላቶች ይጠቀሳል። ለአካድ ነገሥታት ደግሞ ማርቱ በአካድ ዙሪያ ከነበሩት አራት ሩቦች አንዱ ሲሆን ሌሎቹ 3 ሱባርቱ፣ ሱመርና ኤላም ነበሩ። ይህ ስያሜ ወደ ምዕራብ የሆኑት አገራት ሶርያና ከነዓን ይጠቀልል ነበር። የአካድ ንጉሥ...
31251
መጽሐፈ ሄኖክ መጽሐፈ ሄኖክ መጽሐፈ ሄኖክ በግዕዝ ቋንቋ የተጻፈ የመጽሐፍ ቅዱስ ዲዩትሮካኖኒካል መጽሓፍ ነው። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ዘንድ ይህም መጽሓፍ ከሁሉ በፊት በሰዎች ቃላት በግዕዝ በያሮድ ልጅ በሄኖክ ከማየ አይህ አስቀድሞ ተጽፎ ነበር። በመጽሓፉ ሄኖክ ከእግዚአብሔር ብዙ ራዕዮች ሲያይ ይናገራል። ደቂቀ ሴት ትጉሃን በአመጻቸው ጽናት ከቃየል ልጆች ጋራ አብረው እንዲዋሀዱ ከደብረ ቅዱስ በወረዱበት ጊዜ ሄኖክ እንደ ገሠጻቸው ይላል። የከለሱት ልጆቻቸውም በቁመት አብልጠው...
31252
የኖህ ልጆች የኖህ ልጆች የኖህ ልጆች በመጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 10 ይዘርዘራሉ። በአዚህ መጽሐፍ ዘንድ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ ከኖህ 3 ልጆች ከሴም ካምና ያፌትና ከሚስቶቻቸው ተወልደዋል ይባላል። ይህም በአውሮፓ ውስጥ በብዙዎቹ እስከ 19ኛ ክፍለ ዘመን ድረስ እንደ ታሪካዊ ዕውነት ይቆጠር ነበር። እስከ ዛሬም ድረስ በብዙ አይሁድ፣ እስላምና ክርስቲያን አማኞች ዘንድ ዕውነተኛ ታሪክ ሆኖ ይታመናል። አፍሪካውያን እንግዲህ በጥንት የካም ልጆች ተባሉ። እስከ ዛሬ ኩሻውያን ወይም ኩሺቲ...
31253
ኣበራ ሞላ ኣበራ ሞላ ግዕዝ በኮምፕዩተር ዶር አበራ በኮምፕዩተር ግዕዝ ፊደልን ለመጀመሪያ ጊዜ መጠቀም እንዲቻል ያደረጉ ምሑር ናቸው። ይሀንንም ያደረጉት የዓማርኛውን የጽሕፈት መሣሪያ ታይፕራይተር ለሚያውቁት ቀላል እንዲሆን በ“a”፣ “b”፣ “c”፣ “d” ምትክ “ሀ”፣ “ጠ”፣ “ሸ”፣ “ዘ” እና እንግሊዝኛ ለሚያውቁ በ“A”፣ “B”፣ “C”፣ “D” ምትክ “አ”፣ “በ”፣ “ቸ”፣ “ደ” ቀለሞችን በመመደብ ዓይነት ሰላሳ ሰባቱን የግዕዝ ቤት ሆህያት ለ፴፯ የኮምፕዩተር መርገጫዎች ስሞችም በማድረግ ነበር። ስምን...
31254
ምጽራይም ም ጽራይም ዕብራይስጥ፦ מִצְרָיִם ሚጽራዪም በኦሪት ዘፍጥረት ምዕ 10 መሠረት ከኖህ ልጆች መካከል የካም ሁለተኛ ልጅ ነበረ። የምጽራይምም ልጆች ሉዲም፣ ዐናሚም፣ ላህቢም፣ ነፍታሌም፣ ፈትሩሲም፣ ከስሉሂምና ቀፍቶሪም ናቸው። የ«ሚጽራዪም» ትርጉም በዕብራይስጥ ደግሞ ግብጽ ምሥር አገር ነው። እንዲሁም በአረብኛ የአገሩ ስም مصر ምጽር ይባላል። ስሙ ዕጅግ የቆየ መሆኑ እርግጠኛ ነው። በአካድኛ መዝገቦች የግብጽ ስም «ሙሱር»፣ «ሙስሪ»፣ በኡጋሪትም ጽላቶች «ምስርም» ተብሏል። አባ አውሳብዮ...
31255
ዓለማየሁ አልቤ አጊሮ ዓለማየሁ አልቤ አጊሮ ዓለማየሁ አልቤ አጊሮ በደቡብ ኢትዮጵያ የተወለዱ ታዋቂ ሰው ናቸው። አቶ ዓለማየሁ ሳሊኒ ኮስትራቶሪ በተባለው በአንድ የጣሊያን የስራ ካምፓኒ ባለስልጣን ሆነው በተለያዩ አገሮች በኃላፊነት ሰርተዋል። አቶ ዓለማየሁ በበጎ አድራጊነትና ብዙ ድሃ ኢትዮጵያዊያን በመርዳት የሚታወቁ ሲሆን የመጀመሪያ ድግሪያቸውን በአሜሪካን አገር ተቀብለው ኑሮአቸውንም እዚያው አርገዋል። አቶ ዓለማየሁ ባለትዳርና የሁለት ወንድ ልጆች አባት ናቸው።
31256
ወላይትኛ ወላይትኛ በኢትዮጵያ በተጠቃሚ ብዛት በ4ኛነት የሚመደብና በደቡብ ኢትዮጵያ ውስጥ በሰፊው የሚነገር ቋንቋ ነው። ይህም ብቻ ሳይሆን የሌሎቹ ተቀራራቢ ቋንቋዎች ምንጭ ነው። ወላይትኛ ከሁሉም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች በፊት የመጀመሪያው የላቲን ፊደል መጽኃፍ ቅዱስ ታትሞበታል። ከወላይትኛ ጋር ዝምድና ያላቸው ሌሎች ቋንቋዎች ጋሞጎፋዳውሮ እና ኩሎና ኮንታ ናቸው። ባሁኑ ጊዜ በሥልጣን ላይ ያለው የኢሕአዴግ መንግሥት እነኚህን ተቀራራቢ ቋንቋዎች ነገር ግን 25 ትርጓሜዎቻቸው እርስ በርሳቸው በፍጹም የማይገናና...
31257
ኃይለማሪያም ደሳለኝ ኃይለማሪያም ደሳለኝ አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ በወላይታ አውራጃ በቦሎሶ ወረዳ ዱቦ በተባለ የገጠር መንደር ተወለዱ። የ1ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአከባቢያቸው የአየርላንድ ካቶሊክ ሚሺን ባቋቋመው ትቤት እንደፈጸሙ የ2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በወላይታ ሶዶ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትቤት ፈጽመው በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በኢንጂነሪንግ ከተመረቁ በኋላ በአርባምንጭ ውኃ ተቋም አስተማሪ ሆነው እያገለገሉ ሳሉ የማስትሬት ዲግሪያቸውን በፊንላንድ ተምፔ ዩኒቨርስቲ አጠናቀው አገር ቤት በመመለስ በአር...
31259
ተሾመ ቶጋ ተሾመ ቶጋ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ፡ በ1954 በደቡብ ኢትዮጵያ በወላይታ ተወለዱ። እ ኤ አ በ2009 የ46 ዓመቱ ጎልማሳ ኢሕአዴግ አዲስ አበባን እንደ ተቆጣጠረ ተቀማጭነታቸው በግብጽ ሆኖ ለ 3 የአረብ አገሮች አምባሰደር ሆኑ ከዚያም በስፖርት ሚንስትርነት ካገለገሉ በኋላ በ1997 ውዝግብ ያስነሳው የጠቅላላ ምርጫ ሲደረግ ለፓርላማው አፈ ጉባኤነት ኢሕአዴግ በበላይነት በተቆጣጠረበት ፓርላማ ተመረጡ። ጥሩ የመናገር ችሎታ አላቸው የሚባልላቸው አቶ ተሾመ በተለይ በኢትዮኤርትራ ጦርነት ጊዜ ከኬኒያ ...
31260
ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ በ1917 ዓም በአዲስ አበባ ከተማ ተወለዱ፤ በልጅነታቸውም የቤተክህነት ትምህርት ከተማሩ በኋላ፣ በ1926 ዓም በተፈሪ መኮንን ትምሕርት ቤት ገብተው እስከ ጣልያን ወረራ ድረስ ዘመናዊ ትምህርት ተከታትለዋል፡፡ በ193033 ዓም ባሉት ጊዜያትም በአዲስ አበባ “ዘ ስኮላ ፕሪንሲፔ ፒዮሞንቴ” በተባለው የጣሊያኖች ትምሕርትቤት ገብተው ጣልያንኛ ቋንቋ አጥንዋል፡፡ በ1942 እና 1944 ዓም መካከለል ባሉት ጊዜያት ደግሞ በዓለም ዓቀፍ የሲቪል ማኅበር ድጋፍ በሚሰው የማ...
31261
ኮካ ኮላ ኮካ ኮላ ኮካኮላ መጀመርያ የተፈጠረ በ1878 ዓም በአትላንታ አሜሪካ በዶር ጆን ፔምበርቶን ነበረ። መጀመርያ ሀሣቡ ማነቃቂያ መድኃኒት እንዲሆን ነበር። ኮካኮላ የሚለው ስም የተወሰደበት ምክንያት በመጀመርያ የኮካ ቅጠልና የኮላ ፍሬ በውስጡ ስለነበረ ሲሆን፣ ዛሬ ግን እነዚህ አትክልት አይገኙበትም። ከ1886 ዓም ጀምሮ በብርሌ ይሸጥ ጀመር። በ1947 ዓም ደግሞ በቆርቆሮ ይሸጥ ጀመር። ዛሬ የኮካኮላ ድርጅት ብዙ ሌሎች አይነት ለሥላሣዎች ይሠራል። በአለም ዙሪያ በ1 ሴኮንድ ውስጥ፣ ከኮካኮላ ድር...
31262
እግዚአብሔር እግዚአብሔር የግዕዝ ቋንቋ ቃል ሲሆን ትርጓሜውም እግዚዕ ማለት ገዢ ሲሆን፤ ብሔር ማለት ደግሞ የሰው ስብስብ ወይም አገር ማለት ነው። የተሟላ ትርጉም ፡ የሁሉ ገዢ ከሁሉ በላይ የሆነ ፡ ዓለምን የፈጠረ ፡ ብቸኛ አለቃ ማለት ነው። የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች የተጻፉት በሶስት ቋንቋዎች ሲሆን የመጀመሪያው ክፍል በዕብራይስጥና በአረማይክ እንዲሁም የኋለኛው በግሪክ መሆኑ ይታወቃል። እግዚአብሔር በሚለው የግዕዝ ቃል የተተካው ስም በዋነኞቹ እና በመጀመሪያዎቹ ቅጅዎች የፈጣሪን ስም የሚወክሉት አራት ...
31263
ሰይጣን ሰይጣን ሠይጣን በመጽሐፍ ቅዱስና በልዩ ልዩ ሃይማኖት ትምህርት እርኩስ መንፈስ የተጠናወተው ክፉ ኃይል ነው። በተዋሕዶ ሃይማኖት ዘንድ፣ የሰይጣኖች አለቃ ዲያብሎስ አመጸኛ ሆኖ እስከ ዕለተ ደይን ድረስ ይታስራል። በዕለተ ደይንም በእግዚአብሔር ምሕረት ያልዳኑ ሰዎች ሁሉ ከዲያብሎስ ጋር በገሐነመ እሳት ሊቀጡ ነው የሚል እምነት ነው። በአብያተ ክርስትያናት ውስጥ ባሉት ስዕሎች ላይ የዲያብሎስ ቅርጽ ቢታይ፣ ሁልጊዜ እጅና እግሩን ታሥሮ በእሳትም ሐይቅ ተቀምጦ በስቃዩ ጮኾ ይሆናል።
31264
የአንጎላ ፕሬዝዳንት የአንጎላ ፕሬዝዳንት የሀገሩና የአንጎላ መንግሥት መሪ ነው። ፕሬዝዳንቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሾምም፣ አብዛኛው የሕግ ማስፈጸሚያ ሥልጣን በራሱ በፕሬዝዳንቱ ላይ ነው የተወከለው። ኮኝስኮቮላ ኮኝስኮቮላ ፖሎኝኛ ፡ Końskowola IPA kɔɲskɔvɔla በደቡባዊ ምስራቅ ፖላንድ የሚገኝ ሰፈር ነው። ከፑዋቪ እና ከኩሩቭ ከተሞች መካከል በኩሩፍካ ወንዝ ላይ ትገኛለች። ከተማው ላይ ተቀምጦ ይገኛል። በ1996 ዓም የሕዝቡ ብዛት 2188 ነበር። ሰፈሩ በ14ኛ ክፍለ ዘመን ዊቶውስካ ዎላ በሚ...
31265
መላኩ ተፈራ መላኩ ተፈራ ደርግ የኃይለስላሴን አገዛዝ ገርስሦ ስልጣን በያዘ ጊዜ በጎንደር አከባቢ ለአብዮቱ አልታዘዛችሁም በማለት ብዙ ሺ ወጣቶችን በመረሸንና በማስረሸኑ በጭካኔው ይታወቃል። በመሆኑም የጎንደር እናቶች እንዲህ ሲሉ አዚመውለታል። «መላኩ ተፈራ የእግዜር ታናሽ ወንድም የዛሬውን ማረኝ እንጂ ሌላ ልጅ አልወልድም» መቶ አለቃ መላኩ ተፈራ ለሰራው እጅግ አሰቃቂ የግድያ ወንጀሎች አሁን በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ፍርድ ቤት በሞት እንዲቀጣ ፈርዶበታል።
31266
አው ባድር አው ባድር ኣውባዲር፣ አውባድር፣ አባዲር፦ ዑመር አርሪዳ በግምት ወደ ፲፫ ኛው ክዘ፦ በ ፲፫ ኛው ክዘመን ውስጥ የተፃፈውና ስለ ሐረር ጥንታዊ አፈታሪካዊ ታሪክ የሚዘክረው ፋዝ መዲናት ሐረር የተባለው ያልታተመ መጽሐፍ እንደሚገልጸው አባድር ዑመር አርሪዳ እጅግ ከተከበሩት የሐረር ሼኽዎች ውስጥ አንዱና ዋንኛው ናቸው። በዚሁ መጽሓፍ አገላለጽ መሠረት፡ አባድር ከሌሎች በርካታ ሼኾች ጋር በመሆን ከሂጃዝ በ፮፻፩፪ ሂጅሪያ 1216 እኤአ ተነስተው ሐረር ከገቡ በኋላ በአካባቢው የጎሣ እና ኃይማኖት መሪ...
31267
ስብሐት ገብረ እግዚአብሔር ስብሐት ገብረ እግዚአብሔር ስብሐት ስብሐት ለአብ ገብረ እግዚአብሔር ሚያዝያ 27 ቀን 1928 ዓም ሰኞ፣ የካቲት 12 ቀን 2004 በትግራይ ጠቅላይ ግዛት፣ አድዋ አውራጃ፣ እርባ ገረድ በተባለች መንደር ከአባቱ ከቄስ ገብረ እግዚአብሔር ዮሐንስ እና ከወይዘሮ መአዛ ወልደ መድኅን ተወለደ። ትምህርቱን በስዊድን ሚሲዮን፣ እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተከታትሎ በትምህርት አስተዳደር የመጀመሪያ ዲግሪውን ተቀብሏል። በአስፋ ወሰን ትምህርት ቤት በእንግሊዝኛ መምህርነት ለ2 ዓመት ...
31268
በርጫ በርጫ በአጠቃላይ የጫት መቃምን ስነሥርዓት ያጠቃልላል። በርጫ በተለምዶው ሲጀመር በፈጣሪ ምስጋና ይከፈትና፡ ወደ ጫት የመቃሙ ሂደት ይግገባል። የዘወትር ቃሚዎች ለመቃም ትንሽ ሲቀራቸው ጀምሮ እስከ መጀመሪያው የጫት ጉርሻ ባሉት ሰዓታት ውስጥ ድምፃቸውን የማጉላት፣ እርስበእርስ የመተራረብ፣ አልፎ አልፎም የመሳደብና የመጣላት ባሕሪ ይታይባቸዋል። የሙዚቃ ምርጫቸውም ሞቅ ያለ ነው በዚህ ስዓት። ሁለተኛው የበርጫ ክፍለ ጊዘ ቁምነገርም ሆን አልሆነ፡ በተጀመረው አርዕስት ላይ ጥልቀት ያለው ውይይትና ክርክ...
31269
ሳይሌሲያን የሳይሌሲያን ቋንቋ ሳይሌሲያን፦ ślůnsko godka ślůnski አንዳንዴ ደግሞ pů našymu በፖላንድ የላይኛው ሳይሌሲያ ክፍለ ሀገር፣ በቼክ ሪፑብሊክ እና በጀርመን ሀገር የሚነገር ቋንቋ ነው። በ2011 እኤአ በፖላንድ በተካሄደው ብሔራዊ የሕዝብ ቆጠራ 509 000 ሺ ሰዎች ሳይሌሲያን የመጀመሪያ ቋንቋቸው እንደሆነ አስመዝግበዋል። የሳይሌሲያ ቋንቋ ተናጋሪዎች የራሳቸው ፊደላት ስላልነበራቸው ለጽሑፍ የፖልኛን ፊደላት ይጠቀሙ ነበር። በ1998 በ10 የሳይሌሲያን ፊደላት እና ዲግራፎች digr...
31270
ታላቅ የአናባቢ መፈራረቅ ታላቅ የአናባቢ መፈራረቅ ታላቅ የአናባቢ መፈራረቅ በ15ኛው ክፍለ ዘመን አካባቢ በእንግሊዝኛ አጠራር ላይ የደረሰ የድምጽ ለውጥ ነበር። በዚህ ለውጥ ሳቢያ የእንግሊዝኛ ረጅም አናባቢዎች አጠራር ከሌሎች ልሳናት እንደ እጣልኛ፣ ፈረንሳይኛ ወዘተ እጅግ ይለያል። ከዚህ ዋና ለውጦች ጭምር አንዳንድ ሌሎች ትንንሽ የድምጽ ለውጦች ደረሱ። እንዲሁም ዘመናዊ እንግሊዝኛ more ሞር «ተጨማሪ» ከ6 መቶ አመታት በፊት māra ማረ እንደ ነበር እርግጥኛ ነው። ከለውጡ በፊት የላቲን ፊደል ዋና ...
31271
በዳዊ በዳዊ በዳዊ በአዲስ አበባ ቅድስት ማርያም ሰፈር የነበረ ዝነኛ የበርጫ አቅራቢና አስቃሚ ነው። በደዊ ኮሬ ስፍር ቁጥር የሌላቸውን የ5ና 4 ኪሎ ተማሪዎች ለአመታት በሚገባ ሁናቴ አመርቅኖአል። ግሪንላንድ ግሪንላንድ ግሪንላንድ ወይም ካላሊት ኑናት በስሜን አትላንቲክ ውቅያኖስ ያለ ታላቅ ደሴት ነው። አሁን በዴንማርክ ግዛት ውስጥ ራስገዥ ክፍላገር ነው።
31272
የሺጥላ ኮከብ የሺጥላ ኮከብ ኢትዮጵያዊው ደራሲ፤ ጋዜጠኛ አና መምሀር የሺጥላ ኮከብ መስከረም 21 ቀን 1958 በሃረርጌ ክፍለ ሃገር ተወልዶ የአንደኛ አና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በባቢሌ፤ ወተር አና ሃረር እንዲሁም የከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ትምህርቱን ደግሞ በሆሳእና ልጅ አበበ ወ ሰማያት ትቤት ተከታትሏ። ቀጥሎም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በባዮሎጂ በቢ ኤስ ሲ ዲግሪ ተመርቆ በኢሉባቦር ክፍለሃገር ሞቻ አዉራጃ እና መቱ ፤ እንዲሁም በአዲስ አበባ የከፍተኛ 12 እና በቀድሞው ተፈሪ መኮንን እንጦጦ አ...
31273
ፊልጶስ አረባዊ ፊልጶስ አረባዊ ከ236 እስከ 241 ዓም ድረስ የሮማ መንግሥት ንጉሠ ነገስት ነበረ። «አረባዊ» የተባለው ቤተሠቦቹ ከአረቢያ ስለመጡ ነበር። እሱ በ196 ዓም አካባቢ በሶርያ አውራጃ ተወለደ። በሮሜ ንጉሥ አሌክሳንድር ሴቬሩስ ዘመን ፊልጶስ የፕራይቶርያን ጠባቂዎች የንጉሡ ልዩ ዘበኞች ክፍል አባል ሆነ። በኋለኛውም ንጉሥ በ3ኛ ጎርዲያኖስ ዘመን በ235 ዓም ፊልጶስ የዘበኞች አለቃ ሆነ። ይኸው ንጉሥ ግን ልጅ ስለ ሆነ፣ ፊልጶስ እንደራሴ የሚመስል ሚና አጫወተ። ከዚህ ትንሽ በኋላ ጎርድያኖስ...
31274
ፉጥ ፉጥ ደግሞ ፉድ በኩፋሌ፤ ዕብራይስጥ፦ פוט ፉጥ ግሪክ፦ Φουδ ፉድ በኦሪት ዘፍጥረት ምዕ 10 መሠረት የካም ልጅ ነው። የጥንት ሊቃውንት «ፉጥ» ጥንታዊ ሊብያውያን «ለቡ» እና «ፒቱ» እንደ ነበሩ በማለት ይስማማሉ። እነዚህ ነገዶች የግብጽ ጎረቤቶች በስተ ምዕራብ ተገኙ። ዮሴፉስ እንደ ጻፈው፦ «ፉጥ ደግሞ የሊቢያ መስራች ነበረ፣ ከራሱም ኗሪዎቹን፦ «ፉጣውያን» አላቸው፤ ደግሞ በሞሮች አገር በዚያው ስም የሚሰየም ወንዝ አለ፤ ስለዚህ ነው አብዛኞቹ ግሪክ የታሪክ ጸሐፍት ያንን ወንዝና ዙሪያውን «ፉ...
31275
ሉድ ሉድ ዕብራይስጥ፦ לוּד በኦሪት ዘፍጥረት ምዕ 10 መሠረት የሴም ልጅ የኖህም ልጅ ልጅ ነበረ። ይህ ሉድ የሴም ልጅ እና ምጽራይም የወለደው ሉዲም ግን ሁለት የተለያዩ ዘሮች ሆነው ይቆጥራል። የሉድ ተወላጆች በዮሴፉስና በሌሎች ጸሐፍት ዘንድ የትንሹ እስያ ሀገር ልድያ አካድኛ፦ ሉዱ ሆኑ። ከልድያም አስቀድሞ በዚያ ዙሪያ ሉዊያ የተባለ አገር ነበር። በመጽሐፈ ኩፋሌ ድግሞ የሉድ ርስት የሉድ ተራሮች ከአራራት ወደ ምዕራብ፣ በትንሹ እስያ ናቸው። ከዚህ በላይ የግሪክ ታሪክ ጸሐፊ ሄሮዶቶስ እንዳለ፣ ልድ...
31276
የአካዳውያን ታላቅ መፈንቀል የአካዳውያን ታላቅ መፈንቀል የአካዳውያን ታላቅ መፈንቀል ከ1747 እስከ 1755 ዓም ድረስ የእንግሊዝ መንግሥት በአካዲያ ፈረንሳዊ ሕዝብ ላይ ብግድ የጣለው ስደት ነበር። ፈረንሳውያን ከ1596 ዓም ጀምሮ «አካዲ» አካዲያ ወይም የዛሬው ኖቫ ስኮሺያ፣ ካናዳ በተባለ አውራጃ ከኗሪ ሚግማቅ ሕዝብ ጋራ አንድላይ ይኖሩ ነበር። አገሩ ለረጅም ዘመናት የሚግማቅ መኖሪያ ምንም ቢሆንም በ1705 ዓም የፈረንሳይ ንጉሥ በአንድ የአውሮፓ ጦርነት ድል ሆኖ በኢውትረኽት ውል ስምምነት ሥር ቅኝ...
31277
ታምራት ላይኔ ታምራት ላይኔ ታምራት ላይኔ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሰው ነበሩ። የኢሕአዴግ መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ሲሠሩ ከቆዩ በኋላ በሙስና ተከስሰው የ18 ዓመት ጽኑ እስራት ተፈረደባቸው። ከ18ቱ ዓመት 12ቱን ከጨረሱ በኋላ በታኅሣስ ወር አጋማሽ 2001 ዓመተ ምሕረት በአመክሮ ተፈቱ። በእስር ቤት በቆዩበት ጊዜ ከከሃዲነት ወይም አምላክ የለሽነት ወደ አማኝነት የተለወጡ ሲሆን ሲፈቱ የመሰከሩትም ይህንኑ ነበር። አንዳንድ ወሬዎች እንደሚናፈሱት ሆነ ግን 12 ጻመት ወሀኒ ያወረዳቸው ሙሰና ብቻ ሳይሆ...
31278
አዲስ ዘመን ጋዜጣ አዲስ ዘመን ጋዜጣ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ሥር፣ በየዕለቱ የሚታተም ብሔራዊ ጋዜጣ ነው። አዲስ ዘመን በአሁኑ ጊዜ ከ ፵ በላይ ጋዜጠኞች ያሉት ሲሆን የጋዜጣው መጠን ‘መካከለኛ’ በርሊነር 315 cm × 47 cm 124 in × 185 in ሆኖ የፊትና ጀርባ ገፆችን በሙሉ ቀለም ያቀርባል። ይህ ጋዜጣ የአገሪቱ ብቸኛው ዕለታዊ ጋዜጣ ሲሆን የመንግሥትን አቋም የሚያንፀባርቅ እና በየዕለቱ የተለያዩ ልማታዊ ዜናዎችን ይዞ ይወጣል። ታሪካዊ ሂደት የጋዜጣው ድረገጽ ስለጋዜጣው ታሪክ ሲዘግብ፤«...
31279
ኢሳያስ አፈወርቂ ኢሳያስ አፈወርቂ የኢሳያስ አፈወርቂ አባት አቶ አፈወርቂ አባት አቶ አፈወርቅ አብርሃ ይባላሉ፤ እናቱ ወይዘሮ አዳነች በርሄ ይባላሉ። የአቶ ኢሳያስ አጎት ደጃዝማች ሰለሞን አብራሃ በጊዜዉ ሲጠርዋቸዉ በነበሩ ጋዜጦች አጠራር «ሰለሞን አብሃም» በዓጼ ሃይለ ስላሴ ዘመነ መንግሥት ማለት በ1946 ዓም የወሎ እንደራሴ ሆነዉ ያገለገሉ ናቸዉ። በዚያ ጊዜ መቀሌ ከተማ ዉስጥ ተደራጅቶ የነበረዉ የባህል ቡድን አስመራን ከጎበኘ በሗላ ወደ ደሴ መጣ። እንደራሴዉ ደጃዝማች ሰለሞን ለክብር እንግዶቹ በተዘ...
31280
የተከሠተው ዕድል «የተከሠተው ዕድል» ማለት የአሜሪካ መንግሥት ግዛት ከአትላንቲክ ውቅያኖስ ጀምሮ እስከ ሰላማዊው ውቅያኖስ ድረስ መስፋፋቱ ልዩ ዕድል እንደ ነበር የሚል እምነት ነው። አንዳንዴም የተከሠተው እድል ደግሞ ስሜን አሜሪካ በሙሉ ከነካናዳ፣ ሜክሲኮ፣ ኩባና መካከለኛው አሜሪካ ጋራ ሁሉ እስከሚመጠት ድረስ የሚል ሰፊ ትርጉም ተሰጠው። ከዚህ በላይ ይኸው ፅንሰ ሀሣብ ሌሎችን ግዛቶች መግዛቱን ለማጽደቅ ተጠቅሞ ያውቃል። በተከሠተው ዕድል አራማጆች አስተያየት ዘንድ መስፋፋቱ ጥሩ ነገር ከመሆኑ በላይ ...
31281
ማስሩቕ መስሩቕ፣ መስሩቅ፡ 595 አም ገደማ በየመን የመጨረሻው የኢትዮጵያ ንጉሥ፣ በየመን የኢትዮጵያ ንጉሥ ኣብረሃ የመጨረሻው ልጁ ሆኖ ከታላቅ ወንድሙ ከአክሱም ቀጥሎ በየመንና አካባቢው ግዛቶች በዙፋን የተቀመጠ። እናቱ ንግስት ሪይሃና ትባላለች። ከወንድሙ ከያክሱም ጋር የአንድ አባትና እናት ልጆች ናቸው። ሪይሃና ከየመን ልዑላን ቤተሰብ የምትወለድ ስትሆን ሥሙ ዙልያዛን ዱያዛን ከተባለ፣ ከሂምሪያ ንጉሣዊ ቤተሰብ አንዱ ክፍል ከሚወለድ የመጀመሪያ ባልዋ ላይ በግድ ጠልፎ ነው ንጉሥ ኣብረሃ ያገባት። የወን...
31282
መምበርቱ መምበርቱ መስከረም 10 ቀን 1604 ዓም የሞቱ ፈረንሳያውያን በአካዲያ የዛሬው ኖቫ ስኮሺያ፣ ካናዳ መጀመርያ በሠፈሩበት ወቅት የሚግማቅ ብሔር ሳግሞው አለቃ ነበሩ። መጀመርያ የገስፑጒትክ ክፍላገር ሳግሞው ሆነው፣ በኋላ የሌሎቹ 6 ሚግማቅ ክፍላገሮች ሳግሞዎች ዋና ሳግሞው እንዲሆኑ መረጡዋቸው። መምበርቱ ከስሜን አሜሪካ ኗሪዎች መጀመርያ የተጠመቁት በመሆናቸው በተለይ ይታወቃሉ። በሰኔ 20 ቀን 1602 ዓም ቄሱ አቤ ዠሴ ፍሌሼ ለመተባበር ምልክት እሳቸውን ስለ ፈረንሳይ ንጉሥ 4ኛ አንሪ ስም «አን...
31283
ኦሊቨር ክሮምዌል ኦሊቨር ክሮምዌል ኦሊቨር ክሮምዌል ሚያዝያ 30 ቀን 1591 ዓምመስከረም 6 ቀን 1651 ዓም የኖሩ በንጉሥ ፋንታ የእንግሊዝ አገር ጠባቂና መሪ ነበሩ። የእንግሊዝ ብሔራዊ ጦርነት በጀመረበት ጊዜ 1634 ዓም ዖሊቨር ክሮምዌል የፒዩሪታን ወገን መሪ ሆነው ነበር። በተደረገው አብዮት በንጉሡ 1 ቻርልስ ይሙት በቃ ከተፈረደባቸው ቀጥሎ 1641 ዓም አገሩ ያለ ንጉሥ መንግስት ሆኖ የእንግሊዝ ኅብረተሠብ Commonwealth ወይም የጋራ ደኅንነት ይባል ነበር። በ1645 ዓም የክሮምዌል ማዕረግ ...
31284
ኡሩካጊና ኡሩካጊና ወይም ኡሩኢኒምጊና 21022095 ዓክልበ ገደማ የነገሠ በሱመር ውስጥ የላጋሽ ከተማ ገዢ ንጉስ ነበረ። የሉጋላንዳ መረን ግዛት በወደቀ ጊዜ፣ ኡሩካጊና በላጋሽ ንጉስ ሆነ። ኡሩካጊና ያዋጀው ሕገ ፍትሕ 2098 ዓክልበ ግ በታሪካዊ መዝገብ እስከምናውቀው ድረስ መጀመርያው የሕገ መንግሥት ሰነድ ነው። ሰነዱ እራሱ ገና አልተገኘም፤ ነገር ግን ለዜጎቹ አንዳንድ መብት እንደ ፈቀደላቸው ይታወቃል። ለምሳሌ ለመበለትና ለደሀ አደጎች ቀረጥ እንዳስቀረላቸው ድሆችንም ከሃብታሞች አራጣ እንደጠበቃቸው ይ...
31285
ሴይንት ህሊና ደሴት ሴይንት ህሊና ደሴት ሴይንት ህሊና እንግሊዝኛ፦ Saint Helena ወይም ቅድስት ሄሌና በአትላንቲክ ውቅያኖስ የሚገኝ ደሴትና የእንግሊዝ ቅኝ ጥገኛ አገር ነው። ስሙ ስለ ቄሣሩ ቆስጠንጢኖስ ክርስቲያን እናት ሄሌና ተሰየመ። አሁን 4255 ያህል ሰዎች ይኖሩበታል። ከ 2001 ዓም በፊት፣ አሰንሸን ደሴት እና ትሪስተን ደ ኩና በሴይንት ህሊና ጥገኝነት ሥር ኖረው ነበር፤ በዚያ ቀን ግን ሦስቱ ግዛቶች በሕግ እኩል ተደርገው የጠቅላላ ግዛቱ ይፋዊ ስም ከ«ሴይንት ህሊናና ጥገኞቿ» ወደ «...
31286
ገደረ ገደረ ወይም ገደራት በግምት ከ3ኛው ክፍለ ዘመን በፊት በአክሱም የነገሰ የኢትዮጵያ ንጉሥ ነበር። የንጉሥ ገደረ ሠራዊት በደቡብ አረብ ስለመዝመቱ የሚናገሩ መረጃዎች ተገኝተዋል። ሆኖም የመንን በቁጥጥሩ ሥር አድርጎ መግዛቱን ለማረጋገጥ አያስችሉም። በሳባ ቋንቋ ተጽፎ በየመን የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ንጉስ ገደረ ገደራት ከሂምያር ቤተሰቦች ተቀናቃኝ ከሆነው ሓምዳ አኒድ ባላባት አልሃን፣ ናህፋን እና ከልጆቹ ሳይሩውም፣ አውታር፣ እና ያሪም አይመን ጋር ወግኖ እንደነበርና ሆኖም ቆይቶ ወገንተኝነ...
31287
አብርሀም ሊንከን አብርሀም ሊንከን የአብርሀም አባት ማሀይም ገበሬ ቢሆንም፣ አብርሀም ከልጅነት ጀምሮ እራሱን በትጋት ያስተምር ነበር። በ፲፰፻፳፮ ዓም ለኢሊኖይ ክፍለ ሀገር ምክር ቤት መቀመጫ ተመረጡ። የሕግ ትምህርት በጠንካራ ትጉነት አጥንቶ የሕግ ባለሙያ ሆነ። ከ፲፰፻፳፱ ዓም ጀምሮ የባርነት ተቃዋሚ ሆነ። ከአፍሪካ የተወሰዱት ጥቁር ሕዝቦች በግብርና መሥራት እንዲገደዱ ትክክለኛ ወይም ጥሩ ሀሣብ አይደለም ብለው አመኑ። ዳሩ ግን በ1834 ብዙ ባርያዎች ባገለገሉበት ቤተሠብ ውስጥ ያደገችውን ሚስታቸውን ሜ...
31288
ጥቅማዊነት ጥቅማዊነት ጥቅማዊነት እንግሊዝኛ፦ Utilitarianism ዩቲሊቴሪየኒዝም በፍልስፍና ስለ ድርጊት ትክክለኛነት የሚሰፍን ግብረገባዊ ኅልዮ ነው። ከሁሉ የሚሻለው ድርጊት ለአብዛኛዎቹ ደስታ ወይም ጥቅም የሚያመጣው ያው ነው የሚለው ፍልስፍና ነው። ጽንሰ ሃሣቡ በግሪኩ ፈላስፋ በኤጲቁሮስ ጽሑፍ ይገኛል። መርኁ ከጥንት ጀምሮ ቢታወቅም፣ በቅርቡ ዘመን ስለ ጥቅማዊነት በተለይ የጻፉት ፈላስፎች እንግሊዞች ጄርሚ ቤንታም እና ጆን ስቱዋርት ሚል ነበሩ። ቤንታም እንደ ጻፈው የተሻለው ሥራ ለብዛቱ በጎ የሚ...
31289
አባሲዶች አባሲዶች አባሲዶች የሚባሉት የአረቡን ክፍለ ዓለም ከ7421250 ዓም የገዙት የነገሥታት ቤተሰቦች ናቸው። እነዚሁም ባግዳድ የአሁኗ ኢራቅ ዋና ከተማ ላይ ተቀምጠው ይገዙ የነበሩት የሱኒ እምነት ክፍል አራማጆች ሲሆኑ ኡማያዶችን ከስልጣን ያስወገዱት ናቸው። ዘራቸው እንዲሁም መጠሪያቸው የነብዩ መሃመድ አጎት ከነበረው ከአባስ ኢብን አብደል ሙጣሊብ እንደወረደ ይተረካል። በ742 ካሊፍነቱን ከተቆናጠጡ በኋላ የመንግስታቸውን መቀመጫ ከደማስቆ የአሁኗ ሶርያ ዋና ከተማ ወደ ባግዳድ አዙረው ለ2 መቶ አመ...
31290
አስራት ወልደየስ አስራት ወልደየስ ፕሮፈሰር አስራት ወልደየስ አዲስ አበባ ተወልደው ድሬዳዋ ያደጉት ሲሆኑ፣ ለመጀመርያ ጊዘ ፕሮፌስናል ስልጠና ያገኙ የመጀመርያው ኢትዮጵያዊ ቀዶ ጠጋኙ ነበሩ። ፕሮፌሰር አስራት ወያኔ ስልጣን በያዘ ጊዜ የወያኔ ተቃዋሚ በመሆን መአሀድ የመላው አማራ ህዝብ ድርጅት መስራችና ዋና ሊቀመንብር በመሆን ታላቅ የወያኔ ተቃዋሚ ሲሆኑ ወያኔም በፍረሀት ወደ እስርቤት ካስገባቸው በሗላ በሰሜን ሸዋ ደብረ ብርሀን ፣ ጅሩ እነዋሪ፣ መንዝ ፣ ተጉለትና ቡልጋ ፣ አውራጃ ውስጥ እንዲሁም በመላ...
31291
ካዲዝ ካዲዝ ካዲዝ እስፓንኛ፦ Cádiz በደቡብ እስፓንያ የሚገኝ ጥንታዊ ከተማ ነው። የካዲዝ ክፍላገር መቀመጫ ሲሆን 130፣000 ያህል ሰዎች ይኖሩበታል። በአካባቢው ዙሪያ 500፣000 ሰዎች አሉ። ይህ ከተማ ምናልባት ለጥንታዊነት በአውሮፓ ከሁሉ የላቀ ይሆናል። የተመሠረተው በፊንቄ ከነዓን ሰዎች ሲሆን፣ በ1112 ዓክልበ እንደ ሆነ የሚል ልማድ አለ። በከነዓን ቋንቋ ስሙን «ጋዲር» גדר ማለት ግምብ፣ ግድግዳ አሉት። በኋላ ዘመን ግሪኮች ይህን ወደ Γάδειρα ጋዲራ፣ ጋዴራ ቀየሩት። በሮማይስጥም ስ...
31292
5ኛው አብጋር 5ኛው አብጋር 5ኛው አብጋር ወይም 5ኛው አብጋሮስ ዘኤደሣ 42 ዓም የሞቱ ከ12 ዓክልበ እስከ 1 ዓክልበ እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር እና እንደገና ከ5 ዓም እስከ 42 ዓም በኦስሮኤና ግዛት በዛሬው ሶርያ ላይ የነገሡ ንጉሥ ነበሩ። ዋና ከተማቸው ኤደሣ ነበረ። በታሪካዊ ሰነዶች ደግሞ «አብጋር ኡካማ» ጽርዕ፣ «አብጋር ጥቁሩ» ይባላል። በአንድ ጥንታዊ ትውፊት መሠረት፣ እሳቸው መጀመርያው ክርስቲያን የሆኑ ንጉሥ ነበሩ። ከኢየሱስ 72 ደቀ መዛሙርት አንዱ ታዴዎስ ወይም ዓዳይ እንዳጠመቋቸው ያባ...
31293
ዶን ወንዝ ዶን ወንዝ ከ1722 ዓም አስቀድሞ ይህ ወንዝ የአውሮፓና የእስያ ጥንታዊ ጠረፍ ሆኖ ይቆጠር ነበር። በዚያን አመት የአውሮፓ ጠረፍ እስከ ኡራል ወንዝ እንዲዘረጋ የሚል ሀሣብ ለመጀመርያ ግዜ ቀረበ። በመጽሐፈ ኩፋሌ መሠረት 9፡2፣ 6፣ 13 ከምሥራቁ ጫፍ «ራፋ» ጀምሮ በአዞቭ «ሜአት» ወይም «ሜኦት» ባሕር ወዳለው እስከ አፉ ድረስ፣ ይህ ወንዝ «ጤና ወንዝ» ተብሎ ከኖኅ ልጆች ከሴምና ከያፌት ርስቶች መካከል የሆነው ጠረፍ ይሠራል። ጠረፉም ከዚያ ከምሥራቁ ጫፍ ቀጥታ ወደ ምሥራቅ ይሄዳል። በኩ...
31294
ብራና መቅደስ ብራና መቅደስ ብራና መቅደስ በሞት ባሕር ብራናዎች መኃል አንድ ነው። ይህ ብራና ጥቅል በ1948 ዓም በዋሻ ቢገኝም እስከ 1959 ዓም ድረስ በሊቃውንት አልተተረጎመም ነበር። የተጻፈው በዕብራይስጥ ሲሆን ስለቤተ መቅደስ የሚነኩ የእግዚአብሔር ትዕዛዛት ለሙሴ ይከትታል። በነዚህ ትእዛዛት የዘላለማዊ ቤተ መቅደስ ዝርዝሮች፣ ሥርዓቶችና ደንቦች ለሙሴ ይገለጻሉ። ሆኖም በታሪክ የእስራኤል ንጉስ ሰሎሞን ቤተ መቅደስ በኢየሩሳሌም በሠሩ ጊዜ፣ አሠራሩ በዚህ አይነት እቅድ አልነበረም። በዚህ ብራና የተ...
31295
ማዴ ማዴ ማዴ ወይም ማዳይ ዕብራይስጥ፦ מדי ማዳይ፤ ግሪክ፦ Μηδος ሜዶስ በኦሪት ዘፍጥረት 10 መሠረት የያፌት ልጅና ከኖህ 16 ልጅ ልጆች አንዱ ነው። በዮሴፉስና በሌሎች የድሮ ጸሐፊዎች ዘንድ፣ ማዴ በስሜንምዕራብ ፋርስ የኖሩት የሜዶን ሰዎች አባት ነበረ። በግሪክ «ሜዶን» የተባለው ሕዝብ በአሦርኛና በዕብራይስጥ «ማዳይ» ይባል ነበርና። እንዲሁም ዛሬ በአካባቢ የሚኖሩት ኩርዶች እስካሁን ከሜዶን ሰዎችና ከማዳይ እንደተወለዱ ይላሉ። በአንዳንድ መምህር ግመት፣ ከጥንታዊ መዝገብ የታወቀው አገር ሚታኒ ከ...
31296
ፖለቲካ ፖለቲካ ፖለቲካ የሚለው ቃል ከግሪኩ πολιτικος «ዜጋ» ከሚለው ቃል የመጣ ነው። በአሁኑ ወቅት ፖለቲካ ማለት በቡድን ያሉ ግለሰቦች የጋራ ውሳኔ ላይ ለመድረስ የሚያስችላቸው ሂደት ነው። በዚህ ምክንያት ምንም እንኳ ፖለቲካ የሚለው ቃል ብዙ ጊዜ ከሃገርና ከመንግስት ጋር የተገናኘ ቢሆንም በሌላ አንጻር የሰው ልጆች በቡድን ሆነው በሚገኙበት ማናቸውም ስብስብ ይገኛል፣ ለምሳሌ በኩባንያወች፣ በትምህርት ቤቶች፣ በሃይማኖት መዋቅሮች፣ በቤተሰቦች ውስጥ ሳይቀር ፖለቲካ አለ። የኃይል አመዳደብ፣ የቁጥጥ...
31297
ጋያነሸጎዋ ጋያነሸጎዋ ወይም ካያነረኮዋ «ታላቅ ሕገ ሰላም» የሆደነሾኒ ኢሮኳ ኗሪ ብሔሮች የተባበሩበት ሕገ መንግሥት ነው። በተለመደው ታሪክ ዘንድ፣ በ1100 ዓም ገደማ አለቃው ደጋናዊዳ በዛሬው ኒው ዮርክ ክፍላገር የሚኖሩትን 5 ብሔሮች በዚህ ሕግ አባበራቸው። 5ቱ ብሔሮችም በስም ካንየንከሃካ ሞሃውክ፣ ኦንዮታአካ ኦናይዳ፣ ኦኖኝዳጌጋ ኦኖንዳጋ፣ ጋዮጎሆኖ ካዩጋ፣ እና ኦኖንዶዋጋ ሰነካ ናቸው። በኋላም በ1706 ዓም ስድስተኛ ብሔር ተስከሮራ ተጨመረላቸው። የአሜሪካ ኗሪዎች ኅብረተሠብ እንደ አውሮፓውያን ኅ...
31298
ታምራት ገለታ ታምራት ገለታ ናዝሪት ፍቼ እና አአ ቃልቻ ቤት በመክፈት እምነት ሳይለይ አዋቂ ነኝ የታመመ እፈውሳለሁ ገንዘብና ሀብት አበዛለሁ እበራለሁ ክንፍ አለኝ ወዘተ በሚሉ ማደናገሪያዎች እምነታቸውን ሽጠው ጥረው ግረው ሳይሆን በአጭር መነገድ ለመክበር ያሰቡ ከንቱ ኢተዮጵያውያንን ሲያጭበረብር የነበረው ታምራት ገለታ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሎ ጉዳዩ በፍርድ እየታየ ነው። ታምራት ገለታ ከወገብ በላይ ታቦት ከወገብ በታች ጣዖት ከሆኑ ተከታዮቹ አገናኝነት አለአግባብ በሰበሰበው ከፍተኛ ሀብትና ንበረት እ...
31299
ጥላሁን ገሠሠ ጥላሁን ገሠሠ ክቡር ዶር አርቲስት ጥላሁን ገሠሠ መስከረም ፲፯ ቀን ፲፱፻፴፫ እስከ ፳፻፩ ዓም ዝነኛ ኢትዮጵያዊ ዘፋኝ ነበር። በአዲስ አበባ ልዩ ስሙ ጠመንጃ ያዢ እየተባለ ከሚጠራው ሰፈር የመስቀል በዚያም በራስ ጎበና በሚባለው አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ትምህርት ጀመረ። ትኩረቱን በሙሉ በትምህርቱ ላይ እንዲያደርግ ይመክሩት ነበር። የራስ ጎበና ጥላሁን አዲስ አበባ እንደገባ በሀገር ፍቅር ቲያትር ቤት ተቀጠረ። በዚያም ጥቂት አመታት ከሰራ በኋላ ወደ ክብር ዘበኛ ባንድ በመቀላቀል ...
31300
ባህታ ሃጎስ ባህታ ሃጎስ ደጃዝማች ባህታ ሃጎስ የአካለ ጉዛይ መሪ የነበረና ብቻውንም ሆነ ከኢትዮጵያ መሪወች ጋር ለምሳሌ ራስ መንገሻ በመሆን የጣሊያን ቅኝ ገዥወችን በ19ኛው ክፍለ ዘመን የተዋጋ አርበኛ ነው። እኤአ ታህሳስ 19፣1894 ከጣሊያኖች ጋር ሲዋጋ ወድቋል።
31301
አስዋን ግድብ የአስዋን ግድብ ደቡባዊ የግብፅ ከተማ በሆነችው አስዋን ውስጥ የሚገኝ የናይል ትልቅ ግድብ ነው። ከ1950ዎቹ እአአ ጀምሮ ሥሙ የሚገልፀው ከፍተኛው ግድብ የሚለውን ሲሆን ይህም በ1902 እአአ የተጠናቀቀውን የአስዋን ዝቅተኛ ግድብ አዲስ እና ታላቅ መሆኑን ለማሳየት ነው። ከ1960 እስከ 1970 እአአ ነበር ከእንግሊዝ የሀገሪቱን ቅኝ ግዛት ነፃ መሆን ተከትሎ የዚህ ግድብ ግንባታ የተካሄደው። የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ከማሳደግ አንጻር ከፍተኛ ሚና እንዲጫወት ተደርጎ የተገነባው ይኸው ግድብ ከአላስፈ...
31302
ክሪስታል ራዲዮ የክሪስታል ራዲዮ የሚሰኘው ከሁሉ በላይ በጣም ቀላል ራዲዮ ተቀባይ ሲሆን፣ በድሮው የራድዮ ዘመን ታዋቂነት ያገኘ ነበር። ክሪስታል ራዲዮ ባትሪም ሆነ ሌላ የኤሌክትሪክ ኃይል አይፈልግም። ይልቁኑ ከሚተላለፍ የራዲዮ ሞገድ አቅም በመውሰድ በራሱ ይሰራል። ለዚህ ተግባር ሲባል ክሪስታል ራዲዮ ረጅም የሽቦ አንቴና ይፈልጋል። ክሪስታል መባሉ ድሮ ይሰራበት ከነበርው ወሳኝ ክሪስታል ጋሌና የተባለ ክፍል የመጣ ስም ነው። በአሁኑ ዘመን ይህ ክፍል በዳዮድ ተተክቷል። ክሪስታል ራዲዮ በጣም ቀላል ከመሆኑ...
31303
ከነዓን የካም ልጅ ከነዓን የካም ልጅ ከነዓን በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት የካም ልጅና የኖህ ልጅልጅ ነበረ። በዛሬው እስራኤልና ሊባኖስ ያለው አገር በጥንት ስለ ስሙ ከነዓን ይባል ነበር። የከነዓን በኩር ልጅ ሲዶን ሲሆን ሲዶና ከተማ እንደ ተመሠረተና የፊንቄ አባት እንደ ሆነ ተብሏል። እንዲሁም ኬጢ ወይም ኬጢያውያን፣ አሞራዊው ወይም አሞራውያን የተባሉት ሕዝቦች ከከነዓን ተወለዱ። ከዚህ በላይ ኢያቡሳውያን፣ ጌርጌሳውያን፣ ኤዊያውያን፣ ዐሩኬዎን ዐርካዊው፣ ሲኒ፣ አራዴዎን፣ ሰማሪዎን፣ እና አማቲ የተባሉት ዘ...
31304
ዙር ግልባጭ ዙር ግልባጭ በሥነ አምክንዮ ዙር ግልባጭ ማለት አንድን ዐረፍተ ነገር አዙረን ስንገለብጠው የምናገኘው አዲስ ዐረፍተ ነገር ነው። በተለይ ይህ የሚሰራው ለጥገኛ አምክንዮ ነው። ለምሳሌ የሚከተለውን ጥገኛ አረፍተ ነገር እንውሰድ፡ ከጎን የሚታየውን ቬን ዳያግራም ያስተውሉ። ከስዕሉ እንደምንረዳ ማናቸውም A ውስጥ ያሉ ነገሮች B ውስጥ አሉ። በሌላ አነጋገር በሌላ ጎን B ውስጥ የሌለ ማናቸው ነገር A ውስጥ ሊኖር አይችልም። ይህ እውነታ በሒሳብ ምልክቶች ሲጻፍ፡ ለማጠቃለል ያክል፣ A ያመላክታል ...
31305
አባተ ኪሾን አባተ ኪሾን አቶ አባተ ኪሾ በሙስና ምክንያት ከስልጣን ወርደው በእሥር አራት ዓመት ያህል ካሳለፉ በኋላ በምህረት ከመለቃቀቸው በፊት ኢሕአዴግ ኢትዮጵያን ሲቆጣጠር በኢሕአዴግ ጥላ ሥር የሲዳማን ዴሞክራሲያዊ ድርጅትን በመመሥርታቸው የመጀመሪያው የደቡብ ኅብረት ዴሞክራሲያዊ ድርጅትደኅዴድ ጸሃፊና በኢሕአዴግ ዘመነ መንግሥት የመጀመሪያው የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት ነበሩ። አቶ አባተ የትምህርት ደረጃቸው በ1ኛ ደረጃ መምህርነት ኮርስ ከአዋሳ መህራን ማሰልጠኛ ተመርቀው የ5ኛ ክፍል ህብረተሰብ ሳይንስ ...
31306
አዜብ መስፍን አዜብ መስፍን ወሮ አዜብ መስፍን የኢትዮጵያው ጠሚኒስትር የአቶ መለስ ዜናዊ ባለቤት ናቸው። ቀዳማዊ እመቤት በነበሩበት ወቅት በኢትዮጵያ ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ተቋሞች ስብስብ የሆነውን የትግራይ መልሶ ማቋቋሚያ ማህበር ትእምት መሪ ነበሩ፡፡ በአዲስ አበባ እና በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ የኢትዮጵያውያን ሚዲያዎች ወይዘሮዋን በተለያዩ ከባድ የሙስና ቅሌቶች ይፈርጁዋቿል፡፡ ወይዘሮ አዜብ የባለቤታቸው መታሰቢያ የመለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን መስራች እና የቦርድ ሰብሳቢ ናቸው፡፡
31307
ሥነ ስብስብ የስብስብ ውህደትና የጋራ መተግበሪያወች እንዲሁም ቬን ዲያግራምና ኦይለር ዳያግራም በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሊሰጡ ይችላሉ፣ ከበድ ያሉት እንደ ተቆጣሪነት አይነት ጽንሰ ሃሳቦች በኮሌጅ ደረጃ ይቀርባሉ። ሥነ ስብስብ የተመሰረተው በ1860ወቹ በጆርጅ ካንተር እና ሪቻርድ ደደኪንድ በተሰኙ የሂሳብ ተማሪወች ነበር። እኒህ ተመራማሪወች፣ በተለይ ካንተር፣ የዋህ ሥነ ስብስብ ተብሎ አሁን የሚታወቀውን ጥናት መሰረት ቢጥልም በ20ኛ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ በበርትራንድ ረስልና ሌሎችም ተማሪወች...