doc_id
stringlengths
1
5
text
stringlengths
42
393k
31414
ቶቤል ቶቤል፣ ዕብራይስጥ፦ תובל ቱባል፣ በኦሪት ዘፍጥረት 10 መሠረት የያፌት ልጅና የኖኅ ልጅልጅ ነበረ። ከዚህ በላይ በትንቢተ ሕዝቅኤል 38፡23፣ 39፡1 ቶቤል ይጠቀሳል። የተለያዩ ልማዶች ስለ ቶቤል መታወቂያ በ1ኛው ክፍለ ዘመን ዓም የአይሁድ ሊቅ ፍላቪዩስ ዮሴፉስ እንዲህ ብሎ ጻፈ፦ «ቶቤል የቶቤላውያን ጦቤሌስ አባት ሆነ፤ አሁንም ኢቤራውያን ኢቤሬስ ይባላሉ።» ይህ በአናቶሊያና በኋላ በካውካሶስ ተራሮች የተገኘ ሕዝብ ነበር። የካውካሶስ ኢቤራውያን ሕዝብ ከዛሬው ጂዮርጂያ ወላጆች መካከል ነበሩ። ...
31415
እንዳ ማርያም እንዳ ማርያም ቅድስት ማርያም በቀደመው አርባዕተ አሥመራ ተብሎ በሚታውቀው መንደር አማካይ ቦታ ላይ የተሰራ ቤተክርስቲያን ነው። አርባዕተ አሥመራ በተራው የድሮውም ሆነ የአሁኑ አስመራ አማካይ ቦታ ነው። በዚህ በድሮው ቤተክርስቲያን ፈንታ አዲስ ቤተክርስቲያን በጣሊያኑ አርክቴክት ኢ ጋሎ አቅድ መሰረት 1920 ላይ ተሰራ። 1938 ላይ ከእንደገና በመታነጽ ቤተክርስቲያኑ አሁን የያዘውን ቅርጽ አገኘ።
31416
የስያትል መንግስታዊ ትምህርት ቤቶች የስያትል መንግስታዊ ትምህርት ቤቶች የስያትል መንግስታዊ ትምህርት ቤቶች እንግሊዝኛ፦ Seattle Public Schools በስያትል ከተማ በአሜሪካ በዋሽንግተን ክፍለ ሀገር የሚገኝ የሕዝብ ትምህርት ቤት ሥርዓት ነው። ሥራዓቱ በ1867 እኤአ የተመሠረተ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ የሚመራው በዶር ሱዛን ኤንፊልድ ነው። በ200607 እኤአ 45581 ተማሪዎችና 2663 አስተማሪዎች ነበሩት። በ2007 እኤአ፣ ሥርዓቱ 58 የ፩ኛ ደረጃ፣ 8 የከፍተኛ ፩ኛ ደረጃ እስከ ስምንተኛ ክፍል፣ ...
31417
ስያትል ስያትል ስያትል በአሜሪካ ሀገር በዋሽንግተን ክፍለ ሀገር የምትገኝ ከተማ ናት። የከተማዋ ከንቲባ ማይክል ማክጊን ናቸው።
31418
ራዲዮ ራዲዮ የራዲዮ ቴክኖሎጂ ብዙ ተማሪወችንና ብዙ ጊዜ የወሰደ ጥረት ነው እንጂ ያንድ ሰው ድንገተኛ ፈጠራ አይደለም። ሆኖም አንድ አንድ ተማሪወች ከሌሎች በተለየ መልኩ ጉልህ አስተዋጾ ስላደረጉ በታሪክ ተጠቃሽ ናቸው፣ ከነዚህ ውስጥ ቶማስ ኤድሰን፣ ኒኮላ ቴስላ እና ጉግሊሞ ማርኮኒ ዋንወቹ ናቸው። በ1885 ዓም ኒኮላ ቴስላ እንዴት መልዕክትን ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ያለ ሽቦ ማስተላለፍ እንዲቻል አሳየ ። ከዚያ በኋላ ተመራማሪወች፣ አንዱ ያንዱን ስራ በማሻሻል በ1887ዓም ጉግሊሞ ማርኮኒ ያለ ሽቦ መ...
31419
ዋርካ ድረገጽ ዋርካ ድረገጽ ዋርካ ሳይበር ኢትዮጵያ በመባል የሚታወቀው ድኅረ ገጽ የአማርኛ ቋንቋ የውይይት መድረክ ድረ ገጽ ነው። ይህ ድኅረገጽ ኢትዮጵያውያን በራሳቸው ፊደል ለመወያየት ይችሉ ዘንድ በሁለት ወንድማማች ኢትዮጵያዊያን በሰኔ 1992ተፈጥሮ ዛሬ ሁሉንም ኢትዮጵያዊያን በስፋት እያገለገለ ያለ ዌብሳይት ሆኖአል። ይሁን እንጂ ኅረ ገጹ እንደሚለው ከግንቦት 1998 ጀምሮ፥ የኢትዮጵያ መንግሥት ድረገጽን ስለአገደው በአገር ውስጥ እንዳይሰራ ወይም እንዳይታይ አግዷል። ሆኖም የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስ...
31420
ያሁ ያሁ yahoo በአሜሪካ የሚገኝ የኮምፕዩተር አገልግሎቶች የሚሰጥ ድርጅት ነው። የያሁ ኢሜይል፣ ያሁ ዌብሳይት ማውጫ እና ሌሎች አገልግሎቶችን ያቀርባል። ከስታንፎርድ በተመረቁት ዴቪድ ፊሎ እና ጄሪ ያንግ በጃንዩዌሪ 1994 እኤአ ነው የተመሠረተው። የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት በሰኒቬል፥ ካሊፎርኒያ ይገኛል። እንደ አሌክሳ ኢንተርኔት እና ኔትክራፍት ዓይነት የኢንተርኔት አጠቃቀምን የሚመዘግቡ ድርጅቶች በኩል፣ ያሁ ከ400 ሚሊዮን በላይ የሆኑ ሰዎች የሚጎበኙት ሲሆን፣ ይህም በኢንተርኔት ከሚጎበኙ ዌብሳይቶ...
31421
ሲልቪያ ፓንክኸርስት ሲልቪያ ፓንክኸርስት ግፈኛው ፋሺስት ኢጣልያ ኢትዮጵያን በወረረ ጊዜ መጀመሪያ ይሄው የሙሶሊኒ የፋሺስት ሥርዓት እና በጊዜው የነበረው የእንግሊዝ መንግሥት ኢትዮጵያን ለመቆራረስ የነበራችውን ዓላማ በመቃወም በወረራው ዘመናትም ለኢትዮጵያ ነጻነት፣ በሙሉ ቆራጥነት ባከናወኑት ከፍ ያለ ተጋድሎና ላስገኙት ውጤት የኢትዮጵያ ሕዝብ ባለውለታ የሆነላቸው ሲልቪያ ፓንክኸርስት ከዚህም ባሻገር የልዕልት ፀሐይን ሆስፒታል ለማሠራት ያስፈለገውን ገንዘብ በማሰባሰብ፤ የኢትዮጵያ ሴቶች መብት እንዲከበርና ...
31423
ራዲዮ ሞገድ የራዲዮ ሞገዶች ልክ እንደ ብርሃን እና ኤክስሬይ የኤሌክትሮመግነጢስ ማዕበል አካል ናቸው። ልዩነታቸው ሞገዳቸው በጣም ረጅም መሆኑ ነው። በዓይን የሚታየው ብርሃን የሞገድ ርዝመት ከሰው ልጅ ፀጉር እጅግ የሚያንስ፣ ከማይክሮ ሜትር በታች የሆነ ጥቃቅን ነው። የራዲዮ ሞገድ በአንጻሩ ሞገዱ በሴንቲሜትርና በሜትር የሚለካ ሲሆን በአይን ግን አይታይም። ሰው ሰራሽ የራዲዮ ሞገዶች መረጃን ለመለዋወጥና ዜና ለማሰራጨት ሲያገለግሉ ከ100 አመት በላይ አስቆጥረዋል። ራዲዮን፣ ቴሌቪዥን፣ ሳተላይቶች፣ የዕጅ...
31424
ድግግሞሽ መከርከም ድግግሞሽ መከርከም ድግግሞሽ መከርከም በእንግሊዝኛ ምህጻረ ቃል FM ማለቱ የተሸካሚ ሞገድን ድግግሞሽ በመለዋወጥ አንድን መልዕክት ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ የሚተላለፍበት መንገድ ነው። በቴሌኮሚዩኒኬሽን ስልክ እና በራዲዮ ስርጭት ስራ ላይ ጠቀሜታ አለው። የድግግሞሽ ክርክም ስርጭት ከቁመተ ክርክም ስርጭት በተሻለ መልኩ የድምፅን ጥራት ጠብቆ ይተላልፋል፣ ስለሆነም ብዙ ጊዜ የራዲዮ ጣቢያወች የዘፈን ጣቢያቸውን በFM ሲያስተላልፉ ይደመጣሉ። ነገር ግን የድግግሞሽ ክርክም እንደ ቁመተ ክርክ...
31425
ኤሌክትሪክ መስክ የኤሌክትሪክ መስክ በኤሌክትሪክ ቻርጅ ዙሪያ ወይንም ከጊዜ አንጻር በሚለዋወጥ የመግነጢስ መስክ ዙሪያ የሚገኝ የጉልበት መስክ ነው። q1 q2 q3 የተሰኙ ቻርጆችን ያቀፈ የቻርጅ ስርዓት ቢሰጥና እና እያንዳንዳቸው ቻርጆች እርስ በርሳቸው የሚያሳርፉትን ጫና ሳይሆን ከውጭ በሚመጣ እንግዳ ቻርጅላይ የሚያሳርፉትን ጫና ለማስላት የሚጠቅም አይነተኛ መንገድ ነው። ይህንም የሚያረገው በእያንዳንዱ የከባቢው ኅዋ ነጥብ ላይ ከየሙላቱ የሚመነጩ ጉልበቶችን በቬክተር ስርዓት በንብብር በመደመርና የቬክተ...
31426
ታገስ ወንዝ ታገስ ወንዝ ታገስ ወንዝ እስፓንኛ፦ Tajo ታሖ፤ ፖርቱጊዝኛ፦ Tejo ቴኁ በአውሮፓ ውስጥ የሚገኝ ታላቅ ወንዝ ነው። ይህ ወንዝ 1006 ኪሜ ያህል የሚረዝም ሲሆን ዓለማችን ከሚገኙ ወንዞች 173ኛ ረዥሙ ወንዝ ነው። ወንዙ በዚህ ርዝመቱ ስፔን እና ፖርቹጋል ውስጥ 80100 ኪሜ ካሬ ያህል ስፋት ያካልላል። ይህንን ያህል ርዝመት እና ስፋት በሀገራቱ ላይ ካካለለ በኋላ የወንዙ መዳረሻ አትላንቲክ ውቅያኖስ ነው።
31427
ካጊሾ ዲክጋኮይ ካጊሾ ኤቪደንስ ዲክጋኮይ ኅዳር ፲፭ ቀን ፲፱፻፸፯ ዓም ደቡብ አፍሪካዊ እግር ኳስ ተጫዋች ነው። በአሁኑ ጊዜ ለፉልሃም እና የደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ይጫወታል። ፓይታጎረስ ፓይታጎረስ ፓይታጎረስ በጥንቱ ግሪክ ስሙ የገነነ ሐሳቢ እና ፈላስፋ ነበር፤ የተወለደው ከክርስቶስ ልደት በፊት በ580 ዓዓ ሲሆን የሞተውም በ500 ዓዓ ነው። በአሁኑ ዘመን ታዋቂነቱ የሚመነጨው የፓይታጎረስ እርጉጥ formula1 የተባለውን የሂሳብ ቀመር በማግኘቱ ነው። በኖረበት ዘመን ፓይታጎሪያንስ የ...
31428
ሰቨርስኪ ዶኔትስ ወንዝ ሰቨርስኪ ዶኔትስ ወንዝ ሰቨርስኪ ዶኔትስ በአውሮፓ ውስጥ የሚገኝ ታላቅ ወንዝ ነው። ይህ ወንዝ 1078 ኪሜ ያህል የሚረዝም ሲሆን ዓለማችን ከሚገኙ ወንዞች 160ኛ ረዥሙ ወንዝ ነው። ወንዙ በዚህ ርዝመቱ ሩሲያ እና ዩክሬን ውስጥ ተንሰራፍቶ ይገኛል። በሀገራቱ ላይ የለውን ጉዞ ከጨረሰ በኋላ የወንዙ መዳረሻ የዶን ወንዝ ነው። ቪቼግዳ ወንዝ ቪቼግዳ ወንዝ በአውሮፓ ውስጥ የሚገኝ ታላቅ ወንዝ ነው። ይህ ወንዝ 1006 ኪሜ ያህል የሚረዝም ሲሆን ዓለማችን ከሚገኙ ወንዞች 142ኛ ረዥሙ ...
31429
ጎርጎራ ጎርጎራ ወይም ጐርጎራ የድሮው ጎርጎራ በጣና ሐይቅ ሰሜን የሚገኝ ልሳነ ምድርና ከተማ ነው። ጎርጎራ ከማሪያም ግምብ አዲሱ ጎርጎራ 5ኪሎ ሜትር በስተ ሰሜን ምስራቅ ሲገኝ፣ ከደብረሲና ደግሞ 5ኪሎሜትር በስተ ምዕራብ ይገኛል። እድሜያቸው ከ140፣000 እስከ 230፣000 የሚገመቱ የድንጋይ መሳሪያወች በጎርጎርጎራ እንደተገኙ ይጠቀሳል። ከክርስቶስ ልደት በፊት 7000 ዓዓ ጀምሮ የሸክላ ስራ ውጤቶች በአካባቢው ይመረቱ እንደነበር ከአካባቢው በተገኙ ናሙናወች ተነስቶ የኖርዲክ አፍሪካ ኢንስቲቱት ይዘግባ...
31430
ሀዲስ ዓለማየሁ ደራሲ ዶር ሀዲስ ዓለማየሁ ሃዲስ ኣለማየሁ ከአባታቸው ከቄስ ዓለማየሁ ሰለሞን እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ደስታ ዓለሙ በደብረ ማርቆስ አውራጃ በጎዛመን ወረዳ በእንጾር ኪዳነ ምኅረት ቀበሌ በጥቅምት ፯ ቀን ፲፱፻፪ ዓም ተወለዱ። ገና በጨቅላ እድሜያቸው በቤተ ክርስቲያን የሚሰጠውን ትምህርት በቤተሰባቸው አጠገብና ባባታቸው አገር ደብረኤልያስ ሄደው የግእዝ ትምሕርት ቤት ቅኔ ተቀኝተዋል። የቤተክርስቲያን ስርዐታትንና መንፈሳዊ ትምህርትን በጎጃም ገዳማት በደብረ ኤልያስ፣ በደብረ ወርቅና በዲማ ከቀ...
31431
ካቶቪጸ ካቶቪጸ Katowice ድምጽ ፣ ደግሞ በጀርመንኛ ካቶቭትዝ Kattowitz ይባላል የፖሎኝ ከተማ ነው። ሲሌሲያ በሚባል ታሪካዊ አካባቢ በአገሪቱ ደቡብ በክሎድኒጻ እና በራቫ ወንዞች መካከል ይገኛል። 315123 ያሕል ሰዎች ይኖሩበታል። የከተማው ከንቲባ ፕዮትር ኡሦክ ናቸው። የከተማነት ሁኔታ በሕግ የተቀበለው በ1857 ዓም ነበር። ሲሌሲያ ለረጅም ጊዜ የጀርመን ክፍላገር ሆኖ ከተማው እስከ 1910 ድረስ በጀርመን ውስጥ ይገዛ ነበር። ከ1946 ዓም እስከ 1948 ድረስ የካቶቪጸ ስያሜ ስታሊኖግሮድ ...
31432
ጳጉሜ ፮ ጳጉሜ ፮ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር በወንጌላዊው ሉቃስ ስም በተሠየሙት እና በየአራት ዓመቱ በሚደገሙት ሰግር ዓመታት ብቻ የሚውል የዓመቱ የመጨረሻውና ፫፻፷፮ኛው ቀን ሲሆን የክረምት ወቅት ፸፩ኛው ቀን ነው። በቅርብ ዘመናት ጳጉሜ ፮ ከዋለባቸውና ወደፊትም ከሚውልባቸው ሰግር ዓመታት፤ ፲፱፻፷፫፣ ፲፱፻፷፯፣ ፲፱፻፸፩፣ ፲፱፻፸፭፣ ፲፱፻፸፱፣ ፲፱፻፹፫፣ ፲፱፻፹፯፣ ፲፱፻፺፩፣ ፲፱፻፺፭፣ ፲፱፻፺፱፣ ፳፻፫፣ ፳፻፯፣ ፳፻፲፩፣፳፻፲፭እና ፳፻፲፱ ዓመታተ ምሕረት ይቆጠራሉ። መስከረም ፲፬ ቀን በኢትዮ...
31433
ነሐሴ ፯ ነሐሴ ፯ ነሐሴ ፯ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፴፯ ኛው ቀን ሲሆን የክረምት ወቅት ፵፪ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፳፱ ቀናት፣ በዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፳፰ ቀናት ይቀራሉ። ሚያዝያ ፲፰ ሚያዝያ ፲፰ ሚያዝያ ፲፰፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፳፰ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ በልግወቅት ፳፫ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፴፰ ዕለታት ሲቀሩ ...
31434
ዕዝራ ዕዝራ ዕዝራ ዕብራይስጥ ወይም ሱቱኤል በመጽሐፈ ዕዝራ ምዕ 7 በብሉይ ኪዳን ዘንድ በባቢሎን ምርኮ ጊዜ የአይሁድ ካህን ነበረ። የሠራያ ልጅ ሲሆን በፋርስ ንጉስ አርጤክስስ 7ኛው አመት 464 ክበ ከ5000 ከወገኖቹ ጋራ ወደ ኢየሩሳሌም ለመመለስ ፈቃድ ተቀበለ። ከዚህ 13 አመት በኋላ ነህምያ የከተማውን ቅጥር ሲጠግነው ዕዝራ ኦሪት በሙሉ ለሕዝብ አነበበ መጽሐፈ ነህምያ ምዕ 8። በአይሁዳዊው ታሪክ ጸሐፊ በዮሴፉስ ዘንድ ይህ የፋርስ ንጉስ አርጤክስስ ሳይሆን አሕሻዊሮስ ነበረ። አርጤክስስ የአሕሻዊሮ...
31435
ጎባ ጎባ ጎባ በኢትዮጵያ የኦሮሚያ ክልል ከተማ ሲሆን በባሌ ዞንና በጎባ ወረዳ ይገኛል። በ1998 ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለስልጣን እንደተመነው የ50650 ሰው መኖሪያ ሲሆን ከነሱም 24256 ወንዶችና 26394 ሴቶች ይገኙበታል። በሌላ ገለልተኛ ትምና ደግሞ የ34868 ሰው መኖሪያ ተደርጎ ተገምቷል። የከተማው አቀማመጥ በ ላይ ነው። ደገሃቡር ደገሃቡር ደገሃቡር በኢትዮጵያ የሶማሌ ክልል ከተማ ሲሆን በደገሃቡር ዞንና በደገሃቡር ወረዳ ይገኛል። በ1998 ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለስልጣን እንደተመነው ...
31436
የተፈጥሮ ሕግጋት ጥናት ፊዚክስ ከግሪክ φυσικη ፊውሲኬ በቃሉ አመጣጥ የተፈጥሮ ጥናት ወይም የተፈጥሮ ሳይንስ ማለት ነው። የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈጥሮአዊ በሆነ አቀራረብ ጠፈር የተገነባባችውን መሰረታዊ ቁሳቁሶችን፥ በነሱ ላይ የሚከሰቱን የሃይሎችና ውጤቶቻቸውን ያጥናል። ይህም የተፈጥሮን ህጎች ማክበር ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል። በዚህ ሳይንስ የሚገነቡ ቴኦሪዮች ስነ ሒሳብን እንደ መሳሪያ በመጠቀም ያንድ ሥርአትን እንቅስቃሴ ለማስረዳትና ለመተንበይ የሚያልሙ ናቸው። ይህ ሳይንስ የሚቀበለው ሊለኩና ተመልሰው ሊ...
31437
ብርሃኑ ነጋ ብርሃኑ ነጋ ዶር ብርሃኑ ነጋ1958 እኤአ በደብረ ዘይት ከተማ ተወለዱ። እድሜያቸውም 17 ዓመት እንደሞላ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የከፍተኛ ትምህርት መከታተል ጀመሩ። በመጀመሪያ ዓመት የዩኒቨርስቲ ቆይታቸው በወቅቱ ከነበሩ ተማሪዎች ጋር በመሆን ስለ ዲሞክራሲና የስብኣዊ መብት ይከበር ሲሉ፡ ይታገሉ ከነበሩ ወጣት የአብዮቱ የበኩር ልጆች ጋር ትግላቸውን ጀመሩ። ዶር ብርሃኑ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ኢኮኖሚክስ ትምህርት ክፍል አስተማሪ ነበሩ። እስከ ሐምሌ 1999 ድረስ በቃሊቲ እስር ቤት ታስረ...
31438
ብርጅታውን ብርጅታውን ብርጅታውን የባርቤዶስ ዋና ከተማ ነው። የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር 1998 ዓም 96578 ሆኖ ይገመታል። ከተማው ላይ ተቀምጦ ይገኛል። የእንግሊዝ አገር ሰዎች መጀመርያ በ1617 ዓም በደረሱበት ግዜ ደሴቱ በሙሉ ወና እንደ ነበረ መዘገቡ። የድሮ ኗሪዎች የአራዋክ ሕዝብ ሲሆኑ ከደሴቱ በካሪቦች ወይም በስፓንያውያን ምክንያት ሸሽተው ነበርና። በደሴቱ የተገኘው ትልቅ ቅርሳቸው ብቻ አንድ ቀላል ድልድይ ነበር። እንግሊዞች ይህን ሲያገኙ ዙሪያውን ኢንዲያን ብሪጅ የቀይ ሕንድ ድልድይ አሉት። ከ...
31439
ፖርቶ ኖቮ ፖርቶ ኖቮ ፖርቶ ኖቮ ሆግቦኑ፣ አጃሽ ተብሎ የቤኒን ዋና ከተማ ነው። የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር 1998 ዓም 238199 ሆኖ ይገመታል። ከተማው ላይ ተቀምጦ ይገኛል። ፖርቶ ኖቮ በድሮ አጃች ሲባል የአጃ መንግሥት መቀመጫ ነበረ። የአሁኑ ስም ከፖርቱጊዝ ባርያ ፈንጋዮች በ17ኛ ክፍለ ዘመን ወጣ። እነሱ አንድ ጣቢያ እዚያ ሰርተው ነበር። በኋለኛ ዘመን በ1855 ዓም እንግሊዞች አደጋ ስለ ጣሉ የፖርቶ ኖቮ መንግሥት የፈረንሳይ ጠባቂነትን ተቀበለ። ነገር ግን የጎረቤት ዳሆመይ መንግሥት የፈረንሳያውያ...
31440
ፓሪስ ፓሪስ ፓሪስ ፈረንሳይኛ፦ ፓሪ የፈረንሳይ ዋና ከተማ ነው። የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር የአካባቢውን ኗሪ ሲጨምር 9854000 ሆኖ ሲገመት የራሱ የከተማው ኗሪ ቁጥር ደግሞ 2110400 ሆኖ ይገመታል። ከተማው ላይ ተቀምጦ ይገኛል። የኬልቶች ከተማ መጀመርያ «ሉኮቶኪያ» ተብሎ በስትራቦን ተመዘገበ። ፕቶሎመይ ደግሞ ከተማውን «ለውኮተኪያ» አለው። ዩሊዩስ ቄሳር አገሩን ሲይዘው ሥፍራውን በሮማይስጥ «ሉቴቲያ» አለው። የኖረበት ጎሣ ፓሪሲ ስለ ተባሉ፣ የከተማው ስም በሙሉ «ሉቴቲያ ፓሪሶሩም» «የፓሪሲ ሉቴቲያ...
31441
ማላቦ ማላቦ ማላቦ የኢኳቶሪያል ጊኔ ዋና ከተማ ነው። የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር 100000150000 ሆኖ ይገመታል። ከተማው ላይ ተቀምጦ በቢዮኮ ደሴት ቀድሞ ፌርናንዶ ፖ ላይ ይገኛል። ከተማ የተመሠረተው በእንግሊዞች ደሴቱን ከእስፓንያ ሲከራዩ በ1819 ዓም ነበር። በዚያን ግዜ ስሙ ፖርት ክላሬንስ ነበረ። የባርያ ፈንጋዮች ንግድ ለማቆም ተመሠረተ። አንዳንድ ነጻ የወጣ ባርያ ደግሞ እከተማው ሠፈረ። በኋላ ከነዚህ ሠፈረኞች ብዙ ወደ ሴየራ ሌዎን ቢፈልሱም የሌሎች ክፍል ልጆች እስከ ዛሬ በማላቦ ተገኝተው ቋን...
31442
ታሪክ ዘኦሮሞ ታሪክ ዘኦሮሞ ታሪክ ዘኦሮሞ ወይንም ታሪክ ዘጋላ የኦሮሞን ህዝብ አመጣጥ እና መስፋፋት የሚዘግብ ጽሑፍ ነው። በ19ኛው ክፍለ ዘመን የተደረሰው ይሄ መጽሐፍ የዓፄ ልብነ ድንግልን ስርአተ ነገስት በመዳሰስ በርሳቸው ዘመን አገሪቱ ለመጥፋት መድረሷን ሲዘግብ ከአባ ባህረይ በተቃራኒ መልኩ የዚህን ጥፋት ምክንያት በልብነ ድንግል ሃጥያት ያሳብባል። በንጉሱ መታበይ፣ ሲጃራ ማጨስ መፍቀድን፣ የፈርስ ጉግስ መፍቀዱንና ሌሎች የአህዛብ ስራ ናቸው ተብለው ይሚገመቱ ስራዎችን በመስራቱ ሕዝቡ በእግዚአብሐር ...
31443
ያንጎን ያንጎን ያንጎን ቡርምኛ፦ አንድ ታላቅ ከተማ በምየንማር የቀድሞው ቡርማ ነው። የምየንማ ዋና ከተማ እስከ 1998 ዓም ነበረ። በ 1998፣ የምየንማ መንግሥት ናይፕዪዳው አዲሱ ዋና ከተማ መሆኑን አዋጀ። የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር 4344100 ሆኖ ይገመታል። ከተማው ላይ ተቀምጦ ይገኛል። ያንጎን ማለት ከያን ጠላት ወይም ጥላቻ እና ከኮውን አልቋል ተወሰደ። ስለዚህ የከተማው ስም ጥላቻ ወይም ጠላቶች አልቀዋል ለማለት ነው። መጀመርያ በ6ኛ ክፍለ ዘመን በሞን ሕዝብ ሲመሠረት ስሙ ዳጎን ነበር። በ1745...
31444
ጥግ ጥግ በካልኩለስ ጥናት የአንድ አስረካቢ ወይንም ድርድር ግቤት የተወሰነ ዋጋ እየቀረበ ሲሄድ የዚያ አስረካቢ ወይንም ድርድር ውጤት እየተጠጋ የሚሄደው ዋጋ ጥግ ይባላል። ጥግ መሰረታዊ ጽንሰ ሐሳብ እንደመሆኑ ሪጋነት፣ ውድድር እና አጠራቃሚ የተሰኙት የካልኩለስ ዋና ዋና ሃሳቦች የሚተረጎሙት በጥግ ነው፡፡ የአስረካቢ ጥግ አስረካቢ እና ነጥብ ቢሰጡ፣ አስረካቢው በተሰጠው ነጥብ ላይ ሊኖረው የሚችለው ጥግ እንዲህ ይጻፋል እዚህ ላይ f1 በዜሮ ማካልፈል ስለሚሆን አስረካቢው 1ን ማስረከብ አይችልም። በሌላ ...
31445
ማዕከላዊ ዋጋ እርግጥ ማዕከላዊ ዋጋ እርግጥ አንድ መኪና የመጀመሪያውን የቆመ ፖሊስ መኪና ሲያልፍ ከጠዋቱ 2ስዓት ነበር። ያው መኪና፣ ሁለተኛ የቆመ የፖሊስ መኪናን ከ200 ኪሎሜትር በኋላ በ3ሰዓት ላይ አለፈ። በዚህ ጊዜ ግን መኪናው ጸባይ ገዝቶ በቀስታ፣ በ40ኪሎሜትር በሰዓት ነበር ሚጓዘው። የመንገዱ የፍጥነት ወሰን 60 ኪሎሜትር በሰዓት ቢሆን፣ ፖሊሱ ህግ ጥሰሃል ብሎ መኪናውን ሊያስቆም ይችላል ወይ መልሱ አዎ ነው፣ ምክንያቱም በማዕከላዊ ዋጋ እርግጥ መሰረት አጠቃላይ ማዕከላዊ ፍጥነቱ 200ኪሎሜትር1...
31446
ይሖዋ ይሖዋ ይሖዋ በዕብራይስጥ ቋንቋ יהוה በመባል በአራት ፊደላት ሲነበቡ ዮድ ሔ ዋው ሔ የተጠቀሰው የፈጣሪ ስም በአማርኛ የተለመደ አጠራር ነው። በ1879 የታተመው የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ በዘጸዓት 6፡3 ላይ እግዚአይሆዋ Lord Jehovah በማለት ይህንን ስም አስቀምጧል። አብዛኞቹ ዘመናዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች በአንዳንድ ቦታዎቻቸው ላይ ያህዌ ወይም ያህዌህ የሚለውን አጠራር የተጠቀሙ ሲሆን በአጠቃላይ እግዚአብሔር በሚለው ቃል መጠቀምን መርጠዋል። በመጽሐፍ ቅዱስህ ውስጥ መዝሙር 83፡18 የተ...
31447
አበሳሰል አበሳሰል ፈረንሳይኛ፦ኲዚን የምግብ አዘገጃጀት ሙያንና ጥበብን የሚያካትት መደብ ነው። በባልትና ሰፋ ባለው ትርጉሙ ደግሞ ከቅመምና ንጥረ ነገር አመራረጥና አዘገጃጀት አንስቶ እንደ እቃ አጠቃቀምና የምግቡ አቀራረብ ሙያ ሊያካተት ይችላል። የመጠጦችም አጠማመቅ ዘዴዎች የገበታ ማበጃጀትም አብረው ሊታዩ ይችላሉ።
31448
1 ኤሪክ 1 ኤሪክ በስዊድን አፈ ታሪክ የጎታውያን ንጉሥ ነበረ። በ1546 ዓም በኡፕሳላ ኤጲስ ቆጶስ በዮሓንስ ማግኑስ በታተመው የስዊድን ታሪክ መጽሐፍ እንደሚለው፣ 1 ሲጎ በስዊዶች ላይ እየነገሠ ኤሪክ በጎታውያን ነገድ ላይ ተመረጠ፤ ለ68 ዓመታት 22012133 ዓክልበ ገደማ እንደ ነገሠ ይባላል። ይህ ኤሪክ የ1 ጌጣር ጎጉስ ልጅ ወይም ልጅልጅ ነበረ። ሕግጋትን አወጣ፤ ግዛቱንም በሩቅ አገራት አስፋፋ፤ ሰውም ገና ወደማይኖርበት ወደ «ቬታላ» የአሁኑ ዴንማርክ ሰፈረኞችን ሰደደ። ስለዚሁ ድርጊት ማግኑስ «...
31449
ዛሬማ ጊዮርጊስ ዛሬማ ጊዮርጊስ ዛሬማ ጊዮርጊይስ ከአጽቢ ሰሜን 20 ኪሎሜትር ላይ ባለው የዛሬማ መንደር የሚገኝ ጥንታዊ ቤተክርስቲያን ነው። ቤተክርስቲያኑ ሁለት ክፍል ሲኖረው፣ የመጀመሪያው ክፍል የውጨኛው ህንጻ ሲሆን በቅርብ ጊዜ ይተሰራና ውስጡ ያለውን ህንጻ የሚደብቅ ነው። ይሄው ክፍል አጠቃላይ ስፋቱ 1370 mx 890 m ሲሆን በሳር የተሸፈነ ጣሪያና ብዙም እንግዳ ያልሆነ ግድግዳ አለው። ሁለተኛውና በውስጥ ተደብቆ የሚገኘው ቀደምት ቤተክርስቲያን ሲሆን የተገነባውም ከ913ኛው ክፍለ ዘመን ባለው ጊዜ...
31450
አይቲዮፒያ የግሪክ ቃል አይቲዮፒያ የግሪክ ቃል አይቲዮፒያ ግሪክ፦ Αιθιοπία፣ ሮማይስጥ፦ Aethiopia የሚለው ቃል መጀመርያ በጥንታዊ ምንጮች የመልክዓ ምድር ስያሜ ሆኖ ሲታይ፣ የላየኛ አባይ ወንዝ አውራጃ እንዲሁም ከሳህራ በረሃ በስተደቡብ ላለው አገር በሙሉ ያመለከት ነበር። ይህ ስም በግሪክ በሆሜር ጽሁፎች በኢልያዳና ኦዲሲ ምናልባት 850 ዓክልበ ብዙ ጊዜ ይጠቀሳል። በተለይ ከግሪክ ታሪክ ምሁር ሄሮዶቱስ 440 ዓክልበ ግድም ጀምሮ «አይቲዮፒያ» ሲጻፍ ትርጉሙ ከግብጽ ወደ ደቡብ ለተገኘው የአፍሪ...
31451
ማልትኛ ማልትኛ ማልትኛ የሴማዊ ቋንቋዎች ቤተሠብ አባል ነው። በሜድትራኒያን ባሕር ውስጥ በሚገኘው ደሴት አገር በማልታ ላይ ይናገራል። መንስኤው ከቅርብ ዘመዱ ከአረብኛ ነው። ከሁሉ የሚመስለው የቱኒዚያ አረብኛ ሆኖም ከማልታ ቅርብ ጊዜ ታሪክ የተነሣ ብዙ ቃላትና ድምጽ ከጣልኛ እና ከእንግሊዝኛ ወስዷል። ከሴማውያን ቋንቋዎች ሁሉ ማልትኛ ብቻ በላቲን አልፋቤት የተጻፈ ነው። በ1928 ዓም ማልትኛና እንግሊዝኛ የደሴቱ መደበኛ ቋንቋዎች ተደረጉ። ከዚያ ዓመት በፊት መደበኛው ቋንቋ ጣልኛ ነበር። ዛሬ የተናጋሪዎ...
31452
ፍሪታውን ፍሪታውን ፍሪታውን የሴራሊዮን ዋና ከተማ ነው። የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር 1051000 ሆኖ ይገመታል። ከተማው ላይ ተቀምጦ ይገኛል። ቦታው መጀመርያ በ1779 ዓም በቀድሞ ባርያ ገበያ ሥፍራ ላይ በ400 ነጻ ጥቁሮች ከአሜሪካ ተሠፈረ። በአሜሪካ ነጻነት ጦርነት ጊዜ ለእንግሊዝ መንግሥት ታማኝ ስለ ነበሩ የእንግሊዝ ጸረባርነት ድርጅቶች መሬት ለዋጋቸው ሰጣቸው። መሬቱን ከዙሪያው ተምኔ ወገን ገዙ። ነገር ግን ብዙዎቹ ሠፈረኞች ከበሽታ አርፈው ፍሪታውን በ1782 ዓም ተቃጠለ። የሲዬራ ሊዎን ድርጅት የ...
31453
ሲንጋፖር ሲንጋፖር ሲንጋፖር ከተማአገር ነው። የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር 3438600 ሆኖ ይገመታል። ከተማው ላይ ተቀምጦ ይገኛል። የግሪክ መልክዐ ምድር አዋቂ ቶሌሚ 150 ዓም ግድም በዚያ ሥፍራ ሳባና የተባለ የንግድ ወደብ በካርታው ላይ አሳየ። በ250 ዓም ግድም ደግሞ አንድ ቻይናዊ መዝገብ በዚያው ቦታ ፑ ልዎ ቾንግ የተባለ ደሴት ይገልጻል። በ680 ዓም ገዳማ ደሴቱ በሽሪዊጃያ መንግሥት ግዛት መካከል ሆነ። ከ1300 ዓም በፊት ተማሲክ የተባለ መንደር ነበረበት። በአንድ ትውፊት ዘንድ ሳንግ ኒላ ኡታማ...
31454
ጋሜር ጋሜር ዕብራይስጥ፦ גֹּמֶר ጎሜር በኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 10 መሠረት የያፌት በኲር ልጅና የአስከናዝ፣ የሪፋትና የቴርጋማ አባት ነበር። በመጽሐፈ ኩፋሌ ደግሞ ስሙ «ጎሜር» ወይም አንዴ በግድፋት «ሰሜር» ሆኖ ይታያል። የአይሁድ ታሪክ ጸፈፊ ዮሴፉስ 1ኛው ክፍለ ዘመን ዓም እንዳለው፣ «ጎሜር ግሪኮች አሁን ገላትያውያን የሚሏቸውን፣ በድሮ ግን ጎመራውያን የተባሉትን ሰዎች የመሠረተ ነበር።» በእርግጥ የገላትያ ስም የመጣ በዚያ አገር ከሰፈሩት ጋሊያውያን ኬልቶች ነበረ። ዳሩ ግን አቡሊድስ የተባለው...
31455
ሞላላ ሞላላ በሂሳብ ጥናት፣ ከሁለት ነጥቦች F 1 እና F 2 ያላቸው እርቀት ተደምሮ ምንጊዜም አንድ ቋሚ ውጤት የሚሰጡ ነጥቦች p ስብስብ ነው። F 1 እና F 2 የሞላላው ትኩረት ወይም ፎከስ በመባል ይታወቃሉ። ሞላላ ሌላም እኩል የሚሰራ ትርጉም አለው፣ እርሱም፣ ሞላላ ማለት አንድ ክባዊ ሾጣጣን በተንጋደደ ጠፍጣፋ ጠለል ስንቆርጠው የምናገኘው ቅርጽ ነው። በሌላ መልኩም ሲተረጎም ሞላላ ማለት፣ ለምሳሌ ውሃን በክብ ብርጭቆ ውስጥ ሳይሞላ ካስቀመጥን በኋላ ያን ብርጭቆ ጋደም ስናደርገው፣ የውሃው ገጽታ የሚ...
31456
ዮቅጣን ዮቅጣን ዮቅጣን ዕብራይስጥ፦ יָקְטָן ፤ አረብኛ፦قحطان ቃህጣን በብሉይ ኪዳን መሠረት ከኤቦር 2 ልጆች ታናሹ ነበረ። ታላቅ ወንድሙ ፋሌክ ነበረ። ልጆቹም ዘፍ 10፡2629 ኤልሞዳድ፣ ሣሌፍ፣ ሐስረሞት፣ ያራሕ፣ ሀዶራም፣ አውዛል፣ ደቅላ፣ ዖባል፣ አቢማኤል፣ ሳባ፣ ኦፊር፣ ኤውላጥና ዮባብ ናቸው። የመጽሐፍ ቅዱስ ቅርሶች Biblicarum antiquitatum liber ወይም «ፕሲውዶፊሎ» በተባለው ጽሑፍ ዘንድ 70 ዓም ያሕል፣ ከኖህ ዘመን በኋላ ዮቅጣን የሴም ወገኖች ልዑል የተደረገ ሲሆን፣ እ...
31457
ጀርመን ጀርመን ወይንም በይፋ ስሙ የጀርመን ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ በመካከለኛ አውሮፓ የሚገኝ ታሪካዊ አገር ነው። አገሩ 16 ክልሎች ሲኖሩት ዋናና ትልቁ ከተማውም በርሊን ነው። ጀርመን አንድ ይፋዊ ቋንቋ ብቻ አለው እርሱም ጀርመንኛ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ብዙ ልዩ ልዩ የጀርመንኛ ቀበሌኞች በአገሩ ይገኛሉ። ለአንዳንድ ሰዎች ጀርመን «የገጣሚዎችና የአሳቢዎች አገር» በመባል ታውቋል። በዓመታት ላይ በሥነ ጽሑፍ፣ በሥነ ጥበብ፣ በፍልስፍና፣ በሙዚቃ፣ በሲኒማ፣ እና በሳይንስ ዘርፎች በርካታ አስተዋጽኦች በማቅረባቸው ...
31458
ጉብጠት ጉብጠት አንድ መስመር ወይም ገጽታ ከቀጥተኛ መስመር ወይም ከጠፍጣፋ ጠለል የሚለይበትን መጠን የምንለካበት የሂሳብ ጽንሰ ሃሳብ ነው። ከዚህ አንጻር ጉብጠት ማለት በአንድ መስመር ላይ የሚያጋጥመን የአቅጣጫ ለውጥ በእያንዳንዷ የርዝመት መስፈርት ሲካፈል ማለት ነው። ቀስ ብሎ አቅጣጫው ከቀየረ፣ አንስተኛ ጉብጠት አለው እንላለን። አቅጣጫው በፍጥነት ከቀየረ ከፍተኛ ጉብጠት አለው እንላለን የጉብጠት ጽንሰ ሃሳብ መነሻ ክብ ነው። ሁለት ክቦችን የሚለያያቸው የሬዲየሳቸው መጠን ነው። ከፍተኛ ራዲየስ ወይም...
31459
አዙሪት ጉልበት አዙሪት ጉልበት አዙሪት ጉልበት አንድ ቁስ ቀጥተኛ ሳይሆን የጎበጠ መንገድ ይዞ እንዲንቀሳቀስ የሚያደርግ የጉልበት አይነት ነው። አዙሪት ጉልበት ምንግዜም ለቁሱ ፍጥነት ቀጤነክ orthogonal ነው ፤ ማለት አቅጣጫው ወደ ሚጓዝበት መንገድ ቅጽበታዊ የጉብጠት ማዕከል የሚያመላክት ነው ኢሳቅ ኒውተን አማካሊ ጉልበትን ሲተረጉም «አዙሪት ጉልበት ማለት ቁሶች ወደ ማዕክላዊ ነጥብ እንዲያዘነብሉ የሚገደዱበት ወይም የሚሳቡበት ጉልበት ነው» ሲለው የዚህን ጉልበት ሂሳባዊ ቀመር ለመጀመሪያ ጊዜ ያሰ...
31460
ማጎግ ማጎግ ዕብራይስጥ፡ מגוג በኦሪት ዘፍጥረት ምዕ 10 መሠረት ከያፌት ሰባት ልጆች ሁለተኛው ነው። ማጎግ ደግሞ በትንቢት ይጠቀሳል፤ በተለይ ትንቢተ ሕዝቅኤል 38፡2 ጎግ የሚባለው አለቃ ሲገልጽ የአገሩ ስም «ማጎግ» ይባላል፦ «በጎግ ላይና በማጎግ ምድር ላይ፣ በሞሳሕና በቶቤል ዋነኛ አለቃ ላይ» ይላል። በዮሐንስ ራዕይ 20፡8 «በአራቱም በምድር ማዕዘን ያሉትን አሕዛብ፥ ጎግንና ማጎግን፥ እንዲያስታቸው ለሰልፍም እንዲያስከትታቸው ይወጣል፤ ቍጥራቸውም እንደ ባሕር አሸዋ የሚያህል ነው» ሲል እዚህ ለ...
31461
3 ቴልጌልቴልፌልሶር 3 ቴልጌልቴልፌልሶር አሦርኛ፦ ቱኩልቲአፒልኤሻራ ከሚያዝያ ወር 753 ዓክልበ ጀምሮ እስከ 735 ዓክልበ ድረስ የአሦር ንጉሥ ነበረ። ዙፋኑን በመንፈቅለ መንግሥት ከመያዙ አስቀድሞ፡ ስሙ ፑሉ የተባለ የካልሁ አለቃ ነበረ። ይህም ፑሉ በአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ «ፎሐ» ተጽፎ ይገኛል። በ754 ዓክልበ የአሦር ቤተ መንግሥት የተገኘበት ሠፈር ካልሁ በአመጽ ተያዘ። በድካሙ ንጉሥ 5 አሹርኒራሪ በደረሰው ብሔራዊ ሁከት መካከል፡ በ13 አያሩ ወር ሚያዝያ አካባቢ 753፣ የካልሁ ጦር አለቃ ፑሉ በግ...
31462
የአሦር ነገሥታት ዝርዝር የአሦር ነገሥታት ዝርዝር የአሦር ነገሥታት ዝርዝር ከብዙ ቅርሶች ተገኝቷል። ከነዚህ ዋንኛው እራሱ «የአሦር ነገሥታት ዝርዝር» የተባለው ጽሑፍ ነው። ይህ ጽሑፍ ከ3 ቅጂዎች ሲታወቅ፣ ከ2 ሳርጎን አስቀድሞ ወይም እስከ 730 ዓክልበ ድረስ የነገሡትን ነገሥታት ይዘረዝራል። ከ1 ኤሪሹም ጀምሮ ሰነዱ ለያንዳንዱ ንጉሥ የዘመኑን አመታት ቁጥር ይሰጣል። ስለዚህ ዝርዝሩ የተቀናበረው በ2 ሳርጎን ዘመን እንደ ሆነ ይታመናል። በአሦራዊው መቆጠሪያ፣ እያንዳንዱ አመት በሊሙ ሹም ስም ይባል ነበ...
31463
1 እሽመዳጋን 1 እሽመዳጋን ከ1688 እስከ 1678 ዓክልበ ኡልትራ አጭሩ አቆጣጠር የአሦር ንጉሥ ነበረ። አባቱ 1 ሻምሺአዳድ የአሦር ንጉሥ እየሆነ፣ ልጁን እስመዳጋንን በኤካላቱም ዙፋን ላይ አስቀምጦት ነበር። ታናሹ ወንድሙ ያስማሕአዳድ ደግሞ የማሪን ዙፋን ተቀበለው። በባቢሎን ንጉሥ ሃሙራቢ 17ኛው አመት በ1688 ዓክልበ 1 ሻምሺአዳድ እንደ ሞቱ ልጁም እሽመዳጋን የአሦርን መንግሥት እንደ ወረሰው ይታወቃል። በማሪ ጽሑፎች እንደሚዘገብ፣ በዚምሪሊም 9ኛው አመት በ1679 ዓክልበ፣ ኤላማውያን እሽመዳጋንን...
31464
ሶማሊላንድ ሶማሊላንድ ሶማሊላንድ እውቅና ያልተሰጠው በስራው ግን እንደ አንድ ልዑላዊ ሃገር የሚንቀሳቀስ በአፍሪካ ቀንድ በሰሜን ምስራቅ ሶማሌ የሚገኝ አካል ነው። ግንቦት ፲ ቀን ፲፱፻፹፫ ዓም፥ የሶማሊላንድ ሕዝብ ነጻነቱን አውጆ ከሶማሌ ፲፰ ክፍለ ሀገራት ፭ቱን አካቶ ይዟል። ይህም በጅቡቲ፣ በኢትዮጵያ፣ በቀድሞው የጣልያን ሶማሊላንድና በአደን ባሕረሰላጤ የሚካለለውን ፻፴፯ ሺ ፮መቶ ካሬ ኪሎሜትር የሚሸፍነውን ቦታ ከሞላ ጎደል ይሸፍናል። የሶማሊላንድ ዋና ከተማ ሃርጌሳ ነው።
31465
ኢሲን ኢሲን ከ1900 እስከ 1709 ዓክልበ ድረስ የሱመር መጨረሻ ከተማግዛት ነበረ። በ1900 ዓክልበ የኡር መንግሥት ሥልጣን እየደከመ የኢሲን ገዥ እሽቢኤራ ከኡር ነጻነቱን አዋጀ። ከጥቂት አመት በኋላ በ1879 የኤላም ሕዝቦች ኡርን ዘረፉና የኡር መንግሥት ሲወድቅ ኢሲን ያንጊዜ ላዕላይነቱን በሱመር ያዘ። የኢሲን ንጉሶች እጅግ አረመኔ ተከታዮች ነበሩ። በ1844 የላርሳ ከተማ ገዥ ጉንጉኑም በተራው ነጻነቱን ከኢሲን አዋጀና 2 ከተሞቹ ብርቱ ተፎካካሪዎች ሆኑ። ከ1835 ጀምሮ ጉንጉኑም ኡርን ያዘ። በ1...
31466
ነፋስ ስልክ የነፋስ ስልክ ወይም ተንቀሳቃሽ ሞባይል ስልክ ሽቦ አልባ በእጅ የሚይዝ ስልክ አይነት ነው። በአሁኑ ዘመን በመላ ዓለሙ ውስጥ የነፋስ ስልኮች ቁጥር ከቆዩት ቤት ውስጥ ቋሚ ባለ ገመድ ስልኮች ቁጥር ይበልጣል። ይህ የሚገርመው የድሮው ቋሚ አይነት ስልኮች ከንፋስ ስልኮች ይልቅ እጅግ ብዙ ዓመታት በገበያው ላይ ኑረዋል፤ ንፋስ ስልኮች ግን ለአጭር ዘመን ብቻ ተገኝተዋል። ስለዚህ በዓለሙ በጠቅላላ የንፋስ ስልክ መስፋፋት ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ እጅግ ተከናወነ። እንዲህም የሆነበት ሳቢያ የንፋስ...
31467
ሲቪል ኢንጂኔሪንግ ሲቪል ኢንጂኔሪንግ ሲቪል ምህንድስና የምህንድስና ሙያ አይነት ሲሆን ሰው ሰራሽ ወይም ተፈጥሮአዊ ግንባታዎችን፣ ለምሳሌ የመንገድ፣ ቦይ፣ ግድብ፣ ሕንጻ የመሳሰሉትን በንድፍ፣ በግንባታ፣ በጥገና ፣ መስራት፣ መለወጥ፣ መጠገን፣ መንከባከብን ወዘተ የሚጠይቅ የሳይንስ ክፍል ነው። ሲቪል ምህንድስና ከጦርሰራዊት ምህንድስና ሚሊታሪ ምህንድስና ቀጥሎ ረጅም ዕድሜ ያለው የምህንድስና ክፍል ነው፤4 በፈረንጅኛም ሲቪል የሚለውን ስያሜ ያገኘውም ከሚሊታሪ ምህድስና ልዩነቱን ለማሳየት ሲባል የመጣ ቃል ነ...
31468
የ፳፻፫ ዓም የሊቢያ ሕዝባዊ አብዮት የ፳፻፫ ዓም የሊቢያ ሕዝባዊ አብዮት በሊቢያ ውስጥ የተከሰተ እና በሰሜን አፍሪቃ በተከታታይ ከተደረጉ የተለያዩ ሀገራት ፀረ መንግስታዊ አብዮቶች አንዱ ነው። ይህ አብዮት የተጀመረው በእአአ 15 ፌብሩዋሪ 2011 ሲሆን በዚሁ ወር መጨረሻ አካባቢ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች ተባብሶ ታይቷል። አብዮቱ በዋናነት የኮለኔል ሞአመር ጋዳፊን የ42 ዓመታት የስልጣን ላይ ቆይታ በመቃወም ነው። ፀረ መንግስታዊ አገዛዙን በመካከለኛው ምስራቅ የተከሰቱ አብዮቶች ጋር እንዲያያዝ የሚያደር...
31469
ሞልዶቭኛ ሞልዶቭኛ ሞልዶቨኛስክዕ በሞልዶቫ ሬፑብሊክና በትራንስኒስትሪያ የሚናገር የሮማንኛ አይነት ነው። በሞልዶቫ ሕገ መንግሥት መሰረት ሞልዶቭኛ የአገሪቱ መደበኛ ቋንቋ ሲሆን አብዛኞቹ የቋንቋ ምሁሮች ግን ከይፋዊ ሮማንኛና ከይፋዊ ሞልዶቭኛ መካከል ምንም ልዩነት የለም ባዮች ናቸው። ሞልዶቭኛ ማለት ደግሞ የሞልዶቫና የስሜን ሮማንያ ቀበሌኛ ሊሆን ይችላል። ሞልዶቭኛ የሚጻፍበት ፊደል ወይም በላቲን አልፋቤት ወይም በቂርሎስ አልፋቤት ሊሆን ይችላል። አሁኑኑ የላቲን አልፋቤት በሞልዶቫ ሬፑብሊክ ይፋዊ ሲሆን ...
31470
ሞቃዲሾ ሞቃዲሾ ሞቃዲሾ ሶማልኛ፦ ሙቅዲሾ የሶማሊያ ዋና ከተማ ነው። የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር 1208800 ሆኖ ይገመታል። ከተማው ላይ ተቀምጦ ይገኛል። ሞቃዲሾ ከ686 ዓም ጀምሮ ታውቆአል። በዚያን ጊዜ ሡልጣን አብዱል ማሊክ ቢን ሙሪያሚ እንደራሴውን እንደሾመበት ይባላል። የወደቡም መጀመርያ ስም «ሐማር» ተባለ። ከመካከለኛ ዘመን በናዲር ብዙ መሐለቅ ከቻይና በመገኘቱ፣ ከሩቅ አገሮች ንግድ እንደ ተደረገ ይመሰክራል። የዛንዚባር ሡልጣን በ1863 ዓም ከተማውን ያዙ። እሳቸው በ1884 ዓም ለጣልያኖች አከራዩ...
31471
ማሞ ውድነህ ማሞ ውድነህ ማሞ ውድነህ የቴአትር ደራሲ፥ ጋዜጠኛና ለ12 አመት የቀድሞው የኢትዮጵያ ደራሲዎች ማኅበር ሊቀ መንበር ነበሩ ። በአቡነ ጳውሎስ በሚመራው የሃይማኖት ኮሚቴ ውስጥ በኤርትራና በኢትዮጵያ መካከል ሰላምን ለማምጣት ጥረት ካደረጉ ሰዎችም አንዱ ነበሩ። የ54 መጻህፍት ደራሲና ተርጓሚ የነበሩት አቶ ማሞ በማስታወቂያ ሚኒሰቴር ስር በሚታተሙ ጋዜጦችና መጽሔቶች በጋዜጠኝነት የሰሩ ሲሆን የፖሊስና እርምጃው ጋዜጣ መስራችና ተባባሪ ዋና አዘጋጅ ነበሩ፡፡ በኤርትራ ጠቅላይ ግዛት የማስታወቂያ ሚኒ...
31472
አንድሪው ጃክሰን አንድሪው ጃክሰን እንግሊዝኛ Andrew Jackson የአሜሪካ ሰባተኛ ፕሬዝዳንት ነበሩ። ፕረዝዳንቱ ሥልጣን ላይ የወጡት እአአ በ1829 ሲሆን በስልጣን ዘመናቸው ምክትል ፕሬዝዳንት የነበሩት ጆን ሲ ካልሆውን ሲሆን በመሃል ክፍተት በመጨረሻም ማርቲን ቫንቡረን ነበሩ። ፕሬዝዳንቱ የዴሞክራቲክ ፓርቲ አባል የነበሩ ሲሆን ከሥልጣን የወረዱት እአአ በ1837 ነበር።
31473
ከበደ ሚካኤል ከበደ ሚካኤል ከበደ ሚካኤል 19091991 በደብረ ብርሃን ከተማ፣ ገርም ገብርኤል አጥቢያ ጥቅምት ፳፫ ቀን ፲፱፻፱ ዓምተወለዱ። ወደ አዲስ አበባ እንደ መጡ መጀመሪያ በአሊአንስ ኢቲዮፍራንሴዝ በኋላም በላዛሪስት ሚሲዮን ትምህርታቸውን ተከታተሉ። የሼክስፒርን ሮሜዎና ዡልየትን ማክቤዝን በመተርጎም እውቅናን ለማትረፍ ችለዋል። ከበደ ሚካኤል 30 ገደማ መፃሕፍትን ፅፈዋል። ይገኙባቸዋል።
31474
ደማስቆ ደማስቆ ደማስቆ ወይም ደማስቆስ፤ አረብኛ፦ የሶርያ ዋና ከተማ ነው። የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር የአካባቢውን ኗሪ ሲጨምር 2381800 ሆኖ ሲገመት የራሱ የከተማው ኗሪ ቁጥር ደግሞ 1861900 ሆኖ ይገመታል። ከተማው ላይ ተቀምጦ ይገኛል። በአንዳንድ ሊቃውንት ዘንድ፣ ደማስቆ ከሁሉ ይልቅ ረጅሙ እድሜ ያለው ከተማ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ዘንድ በአብርሃም ዘመን ይገኝ ነበር። በፍላቪዩስ ዮሴፉስ ዘንድ በአራም ልጅ በዑፅ ተሠራ። ሚካኤል ሶርያዊው 12ኛው ክፍለ ዘመን እና ባር ሄብራዩስ አቡልፋራጅ 13ኛው ...
31475
ሙሃመድ ዩኑስ ሙሃመድ ዩኑስ ፕሮፌሰር ሙሃመድ ዩኑስ በቤንጋሊ ትውልድ በ28 ጁን 1940 እኤአ የባንግላዴሽ የባንክ ባለሞያና ኤኮኖሚስት ናችው። ማይክሮክሬዲት ተብሎ የሚታወቀውን የአነስተኛ የብድር አገልግሎት በችግር ለሚኖሩ ወገኖች የመስጠትን ስራ የጀመሩትና የስፋፉት ሰው ናችው። ፕሮፌሰሩ እንነኝህ ባንክ አላስተናግድ ብሎ የተዋቸውን ድሆች የሚያገለግለውን ግራሚን ባንክን አቋቁመዋል። በጥቅምት 1999 ፕሮፈሠሩና ባንኩ የሰላም የኖቤል ተሸላሚ ለመሆነ በቅተዋል ይህም ሽልማት የልማት እድገትና ማህበረሰባዊ ለ...
31476
የአለቃ ታየ ተረትናምሳሌዎች የአለቃ ታየ ተረትና ምሳሌዎች ሁለት የወደደ አንድ ያጣል ላለፈው አይጠጠቱም ለሚመጣው አይበለጡም ለሽማግሌ የሚያስተምር በውኃ ላይ ይጽፋል ለሕፃን የሚያስተምር በደንጊያ ላይ ይጽፋል ሲመክሩት ያጠፋል ልጅ ሲታጠቡት ያድፋል እጅ ስንዴ ቢፈትጉት ይነጣል ነገር ቢመረምሩት ይወጣል በጆሮ ከሰሙት ባይን ያዩት ባፍ ላይ ይረሳል በመጣፍ ላይ ይወሳል ነገር ሁሉ በመጀመሪያ ይከብዳል በኋላ እየቀለለ ይሔዳል አህያን ተላም ነድዋት እንደ ሰው በከተማ እንዳውሬ በጨለማ እንጀራን ከባድ ዋይን ከ...
31477
ሰንጠረዥ ሰንጠረዥ ክፍሎች ስለ ሠንጠረዥ መጀመርያ በአብዛኛው የታሪክ ሊቃውንት የተቀበለው ሀልዮ በሕንድ አገር ከ500 ዓም ግድም አስቀድሞ እንደ ተለመደ የሚለው ነው። ሆኖም ከዚያ በፊት ግሪኮች በታላቁ እስክንድር ዘመን ወደ ሕንድ እንዳስገቡት የሚያስቡ ደራስያን ኖረዋል። በዚህ ሀሣብ በትሮያን ጦርነት ወቅት 1200 አክልበ ያሕል በፓላሜዴስ ተፈጠረ። እንኳን ከግሪኮች በፊት የእስኩቴስ ሰዎች እንዳወቁት የሚል አስተሳሰብ ደግሞ ሊገኝ ይቻላል። በሕንድ አገር በድሮ 2 ተመሳሳይ ቻቱራንጋ የተባሉት ጨዋታዎች ...
31478
ርንኛ ኮርንኛ ኮርንኛ በእንግሊዝ የሚናገር ቋንቋ ነው። በኬልቲክ ቋንቋዎች ቤተሠብ ሆኖ የብረቶንኛና የዌልስኛ ቅርብ ዘመድ ነው። የሚናገረው በእንግሊዝ አገር ደቡብምዕራብ ጫፍ ወይም ኮርንዋል ነው። ቀደም ሲል ይህ ቋንቋ ከ1800 ዓም በፊት ጠፍቶ ነበር። በ20ኛው ክፍለ ዘመን ግን ስለ ቋንቋው አዲስ ትኩረት ተገኝቶ አሁን እንደ መነጋገርያ ታድሷልና 3500 የሚያሕሉ ሰዎች ይችሉታል። በ569 ዓም ከዴዮርሃም ውግያ ቀጥሎ የደቡብምሥራቅ ብሪታንያ ሕዝቦች በዌልስ ከኖሩት ዘመዶቻቸው በሴያህስ ጀርመናዊ ወገን ተ...
31479
ፖርት ኦፍ ስፔን ፖርት ኦፍ ስፔን ፖርት ኦፍ ስፔን የትሪኒዳድና ቶቤጎ ዋና ከተማ ነው። የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር የአካባቢውን ኗሪ ሲጨምር 263800 ሆኖ ሲገመት የራሱ የከተማው ኗሪ ቁጥር ደግሞ 45300 ሆኖ ይገመታል። ከተማው ላይ ተቀምጦ ይገኛል። በደሴቱ የነበሩ ኗሪዎች በሥፍራው ኩሙኩራፖ የተባለ መንደር ነበራቸው። በ1530ዎቹ ስፓንያውያን እንዲሠፈሩት አንዳንድ ሙከራዎች አድርገው ስሙን ፕዌርቶ ዴ እስፓንያ የእስፓንያ ወደብ አሉት። ነገር ግን ሠፈሩ ቋሚ አልሆነም። በ1552 ዓም የእስፓንያ ወታደሮች...
31480
ፍራንክሊን ሮዘቨልት ፍራንክሊን ሮዘቨልት ፍራንክሊን ዴላኖ ሮዘቨልት 18741937 ዓም የኒው ዮርክ አገረ ገዥና የአሜሪካ 32ኛ ፕሬዚዳንት ነበሩ። ሮዘቨልት በቀድሞ ፕሬዚዳንት ዉድሮው ዊልሶን ዘመን የባሕር ኅይል ምክትል ሚኒስትር ነበሩ። በ1913 ምርጫ የምክትል ፕሬዚዳንት ዕጩ ሆኑ። ጄምስ ኮክስም የፕሬዚዳንት ዕጩ ነበሩ። ነገር ግን ኮክስና ሮዘቨልት በዋረን ሃርዲንግና በካልቪን ኩሊጅ ተሸነፉ። ሮዘቨልት በ1920 ዓም የኒው ዮርክ አገረ ገዥ ሆኑ። በታላቁ ጭፍግግ ሳቢያ ፕሬዚዳንት ሄርበርት ሁቨር በጣም...
31481
ወልደያ ወልደያ ወይንም ወልዲያ ከደሴ ሰሜን 75 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ከላሊበላ ደግሞ በደቡብ ምስራቅ ያለ በኢትዮጵያ የአማራ ክልል ከተማ ሲሆን በሰሜን ወሎና በወልዲያ ወረዳ ይገኛል። ከኢኮኖሚ አንጻር ለሕንጻ ስራ የሚያገለግል የኖራ ምርት በአካባቢው በትንሹ መካሄዱ በታሪክ ይጠቀሳል። ከተማው በታሪካዊ ቦታወች የተከበበ ሲሆን በ1834ዓም ወልደያን ጎብኝቶ የነበረው ሚስዮኑ ጆዓን ሉዊግ ክራፍ ደጅአዝማች ፋሪስ አሊጋዝ እና ወንድሙ ብሩ አሊጋዝ መምሪያቸውን በዚሁ ቦታ አድርገው እንደነበር ዘግቦት ...
31482
ርየ ግምብ ባርየ ግምብ ባርየ ግምብ ከጎንደር ከተማ 30 ኬሎ ሜትር በስተ ደቡብ የሚገኝ ቤተክርስቲያን ሲሆን በአጼ ልብነ ድንግል ዘመን እንዳተሰራ በአካባቢው ህዝብ ይታመናል። ለቤተክርስቲያኑ ስራ ወጭ ያደረገው ደጅ አዝማች ባህረይ የተባለ ሰውን እንደነበር ይነገራል። ነገር ግን በአህመድ ግራኝ ወደ አካባቢው መምጣት ምክንያት ስራው እንደተቋረጠና ከዚያም በኋላ ስራው ቢጠናቀቅም የሱዳን ደርቡሾች በ1881ዓም የቃጠሎ ጉዳት አድርሰውበታል። ከህንጻው ምስጢራዊነት የተነሳ በታሪክ አጥኝዎች ዘንድ ብዙ ትኩረት የ...
31483
አፋን ኦርማ ማ መዝገበ ቃላት 1850 አፋን ኦርማ ማ መዝገበ ቃላት 1850 አፋን ኦርማ ማ መዝገበ ቃላት የሜጫ ኦሮምኛን ቋንቋ ሰዋሰው እና ቃላት ትርጉም የሚመመረምር ጽሑፍ ሲሆን፣ የተደረሰው ከ19ኛው ክፍለዘመን አጋማሽ በፊት መሆኑ ነው እርግጠኛው አመተ ምህረት አልተጠቀሰም። ደራሲው ጎጃም ይኖሩ የነበሩ አቶ ሐብተ ስላሴ የተሰኙ ሰው እንደነበሩ ታሪክ አጥኝው ኮንቲ ሮሲኒ ዘግቦት ይገኛል። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ 320 የኦሮምኛ ቃላት፣ ትርጉማቸውና እና አገባባቸው ተዘርዝረው ይገኛሉ። በተጨማሪ፣ ኮንቲ ሮሲ...
31484
ቁስቋም ማርያም ቁስቋም ማርያም ደብረ ፀሐይ ቍስቋም ማርያም ከጎንደር ከተማ በስተ ስሜን ምዕራብ ወጣ ብሎ በሚገኘው በደብረ ፀሐይ ቁስቋም የተሰራ ቤተክርስቲያን ነው። ደብረ ፀሓይ ቁስቋም በእቴጌ ምንትዋብ፣ ከ1725 ዓም እስከ በ1738ዓም ተገንብቶ የተጠናቀቀ ሲሆን በጊዜው 360 መስታዎቶች የነበሩት፣ በቀይና ሰማያዊ ሃር አልባሳት ያሸበረቀ፣ እንደ ደብረ ብርሃን ስላሴ በጥሩ ኪነት የተዘጋጀ፣ ከወርቅና ከብር የተሰሩ የቤተ ክርስቲያን ማገልገያወች የነበሩት፣ በጊዜው የተደነቀ ቤተ ክርስቲያን ነበር። ደብረ...
31485
የጆሜትሪክ ድርድር የጆሜትሪክ ድርድር የጂኦሜትሪክ ድርድር የምንለው የቁጥሮች ድርድር ሰልፍ ሲሆን እኒህ የተሰለፉ ቁጥሮች የኋለኛው የከፊተኛው ቋሚ ብዜት ውጤት ሲሆን ነው። ይህ ቋሚ ቁጥር የጋራ ውድር በመባል ይታወዋል። ለምሳሌ ይህን ድርድር እንመልከት 2 6 18 54 ፣ እያንዳንዱ ተከታይ ቁጥር የፊተኛውን ቁጥር በጋራ ውድሩ 3 ስናበዛ እናገኛለን፣ ስለዚህም የጅኦሜትሪክ ድርድር ይሰኛል። በተመሳሳይ ሁኔታ 10 5 25 125 የጂኦሜትሪክ ድርድር ነው ምክንያቱም የጋራ ውድሩ 12 ነውና እዚህ ላይ የጋራ ...
31486
ላዲኖ ላዲኖ ላዲኖ ከይሁዳዊሮማንስ ቋንቋዎች አንዱ ነው። በእስፓንያ ውስጥ የኖሩት አይሁዶች የተናገሩት ቋንቋ በመሆኑ በተለይ ጥንታዊ እስፓንኛን ይመስላል። ምሳሌ ኤል ጁዴዮኤስፓንዮል ኦ ላዲኖ ኤስ ላ ሊንጓ አቭላዳ ፖር ሎስ ሰፋርዲም ጁዲዮስ እክስፑልሳዶስ ዴ ኤስፓንያ ኤን 1492። ኤስ ኡና ሌንጓ ደሪቫዳ ዴል ኤስፓንዮል ኢ አቭላዳ ፖር 150000 ፔርሶናስ ኤን ኮሙኒታስ ኤን ኢስራኤል ቱርኪያ አንቲካ ዩጎስላቭያ ግሬሲአ ማሩዌኮስ ኤንትሬ ኦትሮስ። አይሁዳዊ እስፓንኛ ወይም ላዲኖ በ1484 ዓም ከእስጳንያ ...
31487
ሹሲን ሹሲን ከ1909 እስከ 1901ዓክልበ ግድም ድረስ የኡርና የሱመር ንጉሥ ነበር። የአማርሲን ተከታይ ነበር፤ በነገሥታት ዝርዝር ላይ የኡማርሲን ልጅ ቢባልም፣ ከሌላ ማስረጃ ግን የታሪክ ሊቃውንት ወንድሙ እንደ ነበር ያምናሉ። ቀድሞ ስሙ እንደ ጊሚልሲን ይታነብ ነበር፤ አሁን ግን አጠራሩ «ሹሲን» ትክክል እንደ ሆነ ይታመናል። ንግሥቱ «ኩባቱም» ተባለች። በአራተኛው ዘመነ መንግሥት1906 ዓክልበ እንደ ተመለከተ፣ አሞራውያን በአገሩ ውስጥ በጣም በመብዛታቸው ምክንያት፣ እነሱን ለመከልከል ሹሲን ከጤግሮስ...
31488
ቦሩ ሜዳ ቦሩ ሜዳ ቦሩ ሜዳ በቀድሞ ወሎ የሆነ ትልቅ ገበያ ከተማ ነው። በመጋቢት 18 ቀን 1870 ዓም በቦሩ ሜዳ ላይ የሸዋ ንጉሥ ምኒልክ ለንጉሠነግስት ዮሐንስ አራተኛ ተገዥ እንደሆኑ ቃላቸውን ገቡ። በምላሽም ዮሐንስ በሸዋ ላይ የምኒልክን ንጉሥነት ተቀበሉ። ዮሐንስ በቦሩ ሜዳ ቤተክርስቲያንን ሠርተው በግንቦት 1870 አንድ ታላቅ የተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስብሰባ ተፈጸመበት። በዚህ ስብሰባ «የጸጋ ልጅ» ወይም «ሦስት ልደት» የተባለ ትምህርት ተከታዮች ከእንግዲህ እንደ ሃራ ጤቃ ይቆጠራሉ የሚል አዋጅ...
31489
ደበበ ሰይፉ ደበበ ሰይፉ ሚያዚያ 16 ቀን 1992 ዓም ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው ደበበ ሰይፉ ዘርፈ ብዙ የጥበብ ሰው ነው፡፡ ገጣሚ፣ ሃያሲ፣ መምህር፣ ጸሐፊተውኔት፣ የሥነጽሑፍ ተመራማሪ… ነው፡፡ “የብርሃን ፍቅር” እና “ለራስ የተጻፈ ደብዳቤ” የግጥም ሥብስቦቹ የተደጎሱባቸው መጻሕፍቱ ናቸው፡፡ ከዚህ ለጥቆ ያለው መረጃ አቀናባሪ አሉላ ከ EthioCurrent Assimba –Voice Room አማካኝነት የደበበ ሰይፉን 7ኛ ዓመት የሙት ዓመት ምክንያት በማድረግ ሚያዝያ161999ዓም የተቀናበረ ነው፡ “ደ...
31490
ጉታውያን ጉታውያን ከመስጴጦምያ በላይ ባሉት ተራሮች «ጉቲዩም»፣ «ጉቲ» ወይም «ቁቲ» በተባለ ሀገር የመጣ ሕዝብ ነበረ። በ2010 ዓክልበ ገደማ የአካድ መንግሥት በወደቀበት ዘመን ወርረው የሱመር አለቆች ሆኑ። ጉታውያን በመስጴጦምያ ጽሕፈቶች ዘንድ ኋላቀርና ሥልጣኔ የናቀ ሕዝብ ይመስላሉ። ከነገስታታቸው ስሞች በቀር፣ ስለ ቋንቋቸው ጸባይ አንዳችም ነገር ዛሬ አይታወቅም። መጀመርያ በታሪክ መዝገብ የሚታዩ፣ ለአዳብ ንጉሥ ለሉጋልአኔሙንዱ መንግሥት 2130 ግ ግብር ከሚከፍሉ ሕዝቦች መካከል ሲዘረዝሩ ነው። ...
31491
የዳግማዊ አጼ ተክለሃይማኖት ዜና መዋዕል የዳግማዊ አጼ ተክለሃይማኖት ዜና መዋዕል በግዕዝ እንደተጻፈና በኸርበርት ጆሴፍና ዌልድ ብለንዴል ወደ እንግሊዝኛ እንደተተረጎመ ፣ በ1922 በካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ እንግሊዝ እንደታተመ ከጎን ቀርቧል። ይህ መጽሃፍ ዘመነ መሳፍንት ተብሎ በሚታወቀው ጊዜ የተነሱትን የተለያዩ ነገሥታት ግዛት በግዕዝ በኢትዮጵያውያዊ አይን እማኞች የሚመዘግብና ወደ እንግሊዝኛ የሚተረጉም ነው። የግዕዙ የአጼ ተክለ ሃይማኖት ዜና መዋዕል ከገጽ 7 ይጀምራል፣ የእንግሊዝኛ ትርጉሙ ከገጽ 203...
31492
የጂኦሜትሪክ ዝርዝር የጂኦሜትሪክ ዝርዝር በሒሳብ ጥናት ውስጥ አንድ የቁጥሮች ዝርዝር በቀዳሚና ተከታይ አባሎቹ መካከል ቋሚ ውድር ratio ካለው ያ ዝርዝር የጆሜትሪ ዝርዝር ይባላል። እያንዳንዱን ቀጣይ ቁጥር ከፊት ያለውን ቁጥር በ12 ኛ በማባዛት ማግኘት ስለምንችል ከላይ የተቀመጡው ዝርዝር የጆሜትሪ ዝርዝር ይባላል። ከላይ እንዳየነው እያንዳንዱ የጆሜትሪ ዝርዝር አባል ከፊት ካለው አባል በአንድ ቋሚ ቁጥር እይተባዛ የሚገኝ ነው። እታች ያለው ሰንጠረዥ ይሄን ጉዳይ ለማስረዳት ይሞክራል፦ ውድሩ በ1 እና ...
31493
አበራ ለማ አበራ ለማ አበራ ለማ የተወለደው በ1943 ዓም ፍቼ ሰላሌ ውስጥ ነው። እድገቱ ወሊሶንና አዲስ አበባን ያካትታል። ካገራችን ገጣሚያንና አጫጭር ልቦለድ ጸሓፊዎች አንዱ ነው። በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነ ጽሑፍ ጥናት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የማዕርግ ተመራቂ ነው። ሙያው ጋዜጠኘት ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ሬዲዮና ፕሬስ መምሪያዎች ሠርቷል። ከጦር ግምባር ጋዜጠኝነት እስከ ኪነጥበባት ዘርፎች ሃያሲነት ዘልቋል። እስከ ሰማኒያዎቹ አሠርት አጋማሽ ድረስ፥ የኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር ዋና ጸሃፊ ሁኖ አገልግሏ...
31494
የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት በአውሮፓ አገሮች መኻል ከ ፲፱፻፮ ዓም እስከ ፲፱፻፲፩ ዓም መግቢያ፣ ለአራት ዓመታት የተካሄደ ጦርነት ነው። ይኼ ግጭት የዘመኑ ኃያላን አገራት በሁለት ተቃራኒ ወገን ተሰልፈው ያካሄዱት ግብግብ ሲሆን እስከ ሰባ ሚሊዮን ታጣቂዎች የተካፈሉበትና እስከ አስራ አምስት ሚሊዮን አውሮፓውያን ሕይወታቸውን ያጡበት ትልቅ ጦርነት ነው። ለጦርነቱ ቅስቀሳ ብዙ ምክንያቶች በታሪክ ምሑራን ይጠቀሳሉ። ዓቢይ ከሚባሉት ነገሮች ግን የወቅቱ...
31495
ዕንቁጣጣሽ ዕንቁጣጣሽ መስከረም 1 የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ወራት እንደ ቅብጢ ዘመን አቆጣጠር በመሰከረም 1 ቀን ይጀምራሉ። ይህ የሆነበት ምክንያት የሮሜ መንግሥት ቄሣር አውግስጦስ በ33 ዓክልበ የግብጽ ዓመት በዚያ ቀን እንዲጀመር ስለ ደነገገ ነው። እነሆ መንገድህን የሚጠርግ መልእከተኛዬን በፊትህ እልካለሁ የጌታን መንገድ አዘጋጅ ጥርጊያውንም አቅኑ እያለ በምድረ በዳ የሚጮኽ ሰው ድምፅ» ተብሎ በኢሳይያስ እንደ ተነገረ የነቢዩ ዘካርያስ ልጅ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ በዘመነ ብሉይ መጨረሻና በዘ...
31496
ዘ ሐበሻ ጋዜጣ ዘ ሐበሻ ጋዜጣ ዘ ሐበሻ ጋዜጣ በሚኒያፖሊስ ሚኒሶታ በጋዜጠኛ ሄኖክ ዓለማየሁ አሳታሚነት የሚታተምና የሚዘጋጅ ነጻ የግል ጋዜጣ ነው። ጋዜጠኛ ሔኖክ ዓለማየሁ በኢትዮጵያ በነበረበት ወቅት የማዶና ጋዜጣ ምክትል ዋና አዘጋጅ፤ እንዲሁም የመዲና ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ እና አሳታሚ ነበር። ጋዜጠኛው በሃገሪቱ በሰፈነው የነጻ ፕሬስ ረገጣ በአንካሳ ሕጎች በተለያዩ ጊዜያት ክሶች የተመሰረቱበት ሲሆን በተለይ ያልተዘጉ ከ12 በላይ ክሶች በፍርድ ቤት እንጥልጥል ላይ እንዳለ በሱዳን በኩል አድርጎ ሃገሩን ጥ...
31497
ደብረ ታቦር ሆስፒታል ደብረ ታቦር ሆስፒታል በ፲፱፻፳፰ ዓም ላይ በልዑል ራስ ካሣ ኃይሉ አማላጅነት የሰባት ቀን አድቬንቲስት ሚሲዮኖች በደብረ ታቦር ከተማ ሆስፒታል እንዲሠሩ ተፈቀደ። ይህም ከኢትዮጵያ መንግሥት ሰፊ መሬትና ፴ሺ ማሪያ ጠሬዛ ጠገራ ብር የፈጀ ሥራ ነበር። ልዑል ራስ ካሣም ለድሃ ታካሚወች የሚውል ህንጻ በሆስፒታሉ ግቢ እንዲሠራ ከራሳቸው ፲ሺ ማሪያ ጠሬዛ ጠገራ ብር በእርዳታ ሰጡ። የስዊድኑ ጉድሙንድሰን ከአዲስ አበባ ደብረታቦር አስፈላጊ እቃወችን ጭኖ በገበያ ቀን ደረሰ። የከተማይቱ አስተ...
31498
የጁ ስርወ መንግስት የጁ ስርወ መንግስት የየጁ ስርወ መንግስት ከ18ኛው ክፍለዘመን መጨረሻ እስከ 19ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ድረስ ተጠናክረው ኢትዮጵያን በእንደራሴነት ሲያገለግሉ የነበሩ ራሶችን የሚገልጽ ነው። በዚህ ዘመን የጎንደር ነገስታት ሃይል እጅግ ከማሽቆልቆሉ የተነሳ እኒ እንደራሴወች የፈለጉትን ከስልጣን የማንሳትና የፈለጉትን የመሾም ሃይሉ ነበራቸው። ስለዚህም የአገሪቱ መሪ ነበሩ ቢባል ማጋነን አይሆንም። ከየጁ ስርወ መንግስት እንደራሴወች፡ ራስ ዓሊ ትልቁ ራስ ዓሊጋዝ ራስ ጉግሣ ራስ ይማም ራ...
31499
ንዋየ ክርስቶስ ንዋየ ክርስቶስ ዓፄ ንዋየ ክርስቶስ በዙፋን ስማቸው ሰይፈ አርድ ከ1344 1372 እኤአ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት ነበሩ። የቀዳማዊ አጼ አምደ ጽዮን የመጀመሪያ ልጅ ነበር። በዚህ ንጉስ ዘመን አሊ ኢብን ሳብር አድ ዲን የተባለ የወላሽማ ስረወ መንግስት በማመጹ ንጉሱ በይፋት እና አዳል ዘመቻ አደረገ። በዚህ ዘመቻ መሪውና ልጆቹ ስለተማርኩ የይፋት ሱልጣኔት በታሪክ አበቃለት። ንጉሱ ሁሉን ለእስር ቢዳርጉም የመሪውን ልጅ አህመድን ግን የይፋት አስተዳዳሪ አድርገው ሾሙት። ይህ በዚህ ቆይቶ ከ...
31500
ሆሣዕና በዓል ሆሣዕና በዓል የሆሣዕና በዓል ሆሣዕና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ከስምንቱ የዐቢይ ጾም እሑዶች አንዱና የመጨረሻው ሳምንት ተብሎ የሚጠራው ከትንሣኤ ቀድሞ የሚገኝ የሕማማት መግቢያ ዋዜማ ነው። ‘አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ እጅግ ደስ ይበለሽ ፣አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ እልል በይ እነሆ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው ትሑትም ሆኖ በአህያም በአህያያቱም ግልገል በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል… ሰላምን ይናገራል’’ ‘‘ሁሉም ፈጥነው ልብሳቸውን ወሰዱ በሰገነቱም...
31501
አንኮበር አንኮበር አንኮበር የከተማነት ታሪኳ የጐላው ግን ከግራኝ ወረራ በኋላ ተበታትኖ የቆየውን የጥንታዊ ሸዋን ግዛት አንድ ለማድረግ የሸዋ ስርወመንግሥት በአቤቶ ነጋሲ በመንዝ አጋንቻ ላይ በ፲፮፻፷፭ ዓም ተጀምሮ በተከታታይ እስከ ፲፰፻፹፩ ዓም የጥንት ኢትዮጶያ ግዛትን ለማስመለስ በተደረገው እንቅስቃሴ ነው። የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ወደ ፲፫ኛው መቶ ክፍለዘመን ሥር መሠረቱ የረር እንጦጦ እስከዞረበትና በኋላም አዲስ አበባ እስከተቆረቆረችበት ጊዜ ድረስ በቀዝቃዛ አየሯ የምትታወቀው አንኮበር ለአምስት ...
31502
ግሸን ተራራ ግሸን ተራራ ግሸን ተራራ በአሁኑ ደቡብ ወሎ የሚገኝ ጥንታዊና ታሪካዊ ተራራ ነው። የታሪካዊነቱ ምንጭ የዕርስ በርስ ጦርነትን ለማስወገድ ሲባል እንደ ደብረ ዳሞ ትግራይ እና ወህኒ ጎንደር የነገስታት ወንድ ተገዳዳሪ ዝርያወች በአምባው ላይ ይታሰሩ ስለነበር ነው። አጼ ጅን አሰገድ ወንድሞቻቸውንና ወንድ ልጆቻቸውን በአምባ ግሸን እንዳሳሰሩ በዜና መዋዕላቸው ላይ ሰፍሮ ይገኛል። ሆኖም ግን ይህን ስራ እኒህ ንጉስ ያስጀምሩት ወይም ከሳቸው በፊት ይጀመር በታሪክ ተመዝግቦ የተገኘ እርግጠኛ ማስታወሻ ...
31504
ደብረ ዳሞ ደብረ ዳሞ ደብረ ዳሞ በ6ኛው ክፍለ ዘመን የተቆረቆረ ገዳምና ይህ ገዳም የሚኖርበት ተራራ ስም ነው። ደብረ ዳሞ ከአዲግራት በስተምዕራብ በመካከለኛው ትግራይ ይገኛል። ከተራራው ቀጥ ብሎ ለመውጣት አዳጋችነቱ የተነሳ ወደገዳሙ ለመድረስ ከቆዳ በተሰራ ገምድ ላይ መንጠላጠል ግድ ይላል። ቤተ ክርስቲያኑ በኢትዮጵያ ውስጥ ጥንታዊ የአሰራር ዘዴን ተከተሎ እስካሁን ዘመን ድረስ በመዝለቅ ቀደምትነት ስፍራን ይይዛል። የተሰራውም በአቡነ አረጋዊ በ6ኛው ክፍለ ዘመን እንደነበር ትውፊት አለ። ቶማስ ፓከናም ...
31505
የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት እንግሊዝኛ፡ Organisation of African Unity OAU፣ ፈረንሳይኛ፡ Organization de lUnité Africaine OUAግንቦት ፲፯ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓም አዲስ አበባ ላይ ተመሥርቶ የድርጅቱ መመሪያ ውል OAU Charter በ፴፪ቱ መሥራች አገር መሪዎች ጸድቆ ተፈርሟል። የድርጅቱም ጠቅላይ መሥሪያ ቤቱ በአዲስ አበባ እንዲቆይ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ባቀረቡት ግብዣ መሠረት እስካሁን ድረስ እዚያው አዲስ አበባ ላይ ይገኛል። ይህ ድርጅት በ፲፱...
31506
ግስበት ግስበት ግስበት ማናቸውም ግዝፈት ያላቸው ቁስ ነገሮች እርስ በርሳቸው እንዲሳሳቡ ግድ የሚላቸው የተፈጥሮ ጉልበት ነው። በዕለት ተለት ኑሯችን ግዝፈት ያላቸው ነገሮች በአየር ከመንሳፈፍ ይልቅ ከመሬት ጋር እንዲላተሙ የሚያደረጋቸው፣ በሌላ አነጋገር ለነገሮች ክብደት የሚሰጣቸው ግስበት ነው። የመሬት ግስበት ወይም በተለምዶ የመሬት ስበት መሬት ባላት ግዝፈት ምክንያት ሌላ ግዝፈት ያለውን ነገር የምትስብበት የተፈጥሮ ጉልበቷ ነው። ጨረቃ ከመሬት በራ የማትጠፋው የመሬት ግስበት አንቆ ስለያዛት ነው። ሜር...
31507
ሸዋ ሸዋ ሽዋ በኢትዮጵያ ገጸ ምድር መሃል ላይ የሚገኝ ታሪካዊ ሥፍራ ነው። ለብዙ መቶ ዓመታት በሉዐላዊነት በራሱ መሪዎች ሲተዳደር የኖረ የኢትዮጵያ አካል ሲሆን፣ ርዕሰ ከተማው እስከ ፲፰፻፹፱ ዓም በሰሜን ሸዋ ውስጥ በየጊዜው በተለያዩ ሥፍራዎች ሲፈራረቅ ቆይቶ ባለፉት መቶ በላይ ዓመታት ግን አዲስ አበባ ሆናለች። ደብረ ብርሃን፤ አንኮበር፤ አንጾኪያ፤ ልቼ እና እንጦጦ በተለያዩ ጊዜያት የሸዋ ርዕሰ ከተማዎች ነበሩ። አብዛኛው የሰሜን ሸዋ ግዛቶች፣ ማለትም መንዝ፤ ተጉለት፤ ይፋት፤ ምንጃር እና ቡልጋ ሕዝብ...
31508
ሰሎሞን ተካልኝ ሰሎሞን ተካልኝ ሰሎሞን ተካልኝ አቋም የለለው ፖለቲከኛ ዘፋኝ ከመሆኑ በፊት ከተዋጣላቸው ኢትዮጵያዊያን ዘፋኞች አንዱ ነበር። ሰሎሞን በተለይ በ70ዎቹ ውስጥ «ወደድ ወደድ» የተባለው ዘፈኑ ነበር ወደ እውቅና ብቅ ያረገው። ሰሎሞን ኢሕአዴጎች ኢትዮጵያን እንደተቆጣጠሩ በስደት ወደ አሜሪካን አገር ሎሳንጀለስ ከተማ ከመጣ በኋላ «ሁሉም ዜሮ ዜሮ» የሚል ዘፈኑን አውጣና ታዋቂነቱን አተረፈ። ከዚያም ጊዜ ጀምሮ ሕይወቱን ከፖለቲካው ዓለም ሙሉ በሙሉ መዝፈቅ ብቻ ሳይሆን ዓላማውንና አቋሙን በመቀያየ...
31509
ላፕላስ ሽግግር ላፕላስ ሽግግር በሒሳብ ጥናት ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ ስራ ላይ የሚውል የመደመራዊ ሽግግር ቢኖር ይሄው ላፕላስ ሽግግር Laplace Transform የሚባለው ነው። ይህ ሽግግር በፊዚክስ፣ሒሳብ፣ በምህንድስናና በእድል ጥናት የዕውቀት ዘርፎች በከፍተኛ ስራ ላይ ይውላል። ሎጋሪዝም ማባዛትን ወደ መደመር እንደሚቀይርና ማባዛትን እንደሚያቃልል ሁሉ የላፕላስት ትራንስፎርም የካልኩለስን ሥነ ለውጥና ሥነ ማጎር ወደ ማባዛትና ማካፈል በማሻገር የካልኩለስን ተግባር ያቃልላል። የላፕላስ ሽግግር ከፎሪየ...
31510
ሌብኒትዝ ሌብኒትዝ ጎትፍሪድ ቪልሄልም ሌብኒትዝ July 1 June 21 OS 1646 – November 14 1716 እኤአ የ17ኛው ክፍለ ዘመን የጀርመን የሒሳብ ሊቅ፣ ሳይንቲስት፣ ፈላስፋ፣ ፍርድ አጥኝና ባጠቃላይ መልኩ ሁለ ገብ ተመራማሪ ነበር። ሌብኒዝ ከኢሳቅ ኒውተን ትይዩ ካልኩለስ የተባለውን የዕውቀት ዘርፍ ፈጥሯል። አሁን ድረስ ተማሪወች የሚጠቀሙበት የካልኩለስ የአጻጻፍ ስልት በዚህ ሰው የተፈለሰፈ ነው። ለኮምፒዩተር ስራ እጅግ ወሳኝ የሆነውን የሁለትዮሽ ቁጥር ስርዓት ባይናሪ ቁጥር ዘመናዊ ኮምፒዩተ...
31511
ጎፋ ጎፋ ቋንቋ በ1999 ዓም በተደረገው የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ውጤት የብሔረሰቡ ሕዝብ ብዛት 363ሺ9 ነው፡፡ ጎፋ ብሔረሰብ በጋሞጎፋ ዞን ውስጥ ከሚገኙ ብሔረሰቦች መካከል አንድ ሲሆን፣ ብሔረሰቡ በዋናነነት በጎፋ ዙሪያ፣ ዛላ፣ ዑባ፣ ደብረፀሐይ እና መሎካዛ በሚባሉ ወረዳዎች ይኖራል፡፡ የብሔረሰቡ ዋና የኢኮኖሚ መሠረት ጥምር ግብርና ሲሆን፤ የገቢ ምንጭ በሚያስገኙ ምርቶች ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ ብሔረሰቡ ጋብቻ የማፈጸመው የጎሣ አቻነትን፣የሀብት ደረጃ እና የሥጋ ዝምድና አለመኖርን መሠረት በማድረግ ነ...
31512
ቱዊስኮን ቱዊስኮን የቱዊስቶ ወይም ቱዊስኮ ስም ከሮሜ ጸሐፊው ታኪቱስ ታሪክ ገርማኒያ 90 ዓም የተጻፈ ተጠቅሶ ይታወቃል። ታኪቱስ እንደ ገለጸው፣ በጀርመናውያን «ጥንታዊ ዘፈኖች» ውስጥ ይህ ቱዊስቶ «ከምድር የተወለደ አምላክ» ሆኖ ይከብር ነበር። በተጨማሪ በነኚህ ዘፈኖች በኩል፣ ልጁ ማኑስ እራሱ ሶስት ልጆች ነበሩት፣ እነኚህም 3 ልጆች የኢንጋይዎን፣ የኢስታይዎን እና የሄርሚኖን ብሔሮች ወለዱ። በ1490 ዓም አኒዩስ ዴ ቪቴርቦ የተባለ ጣልያናዊ መነኮሴ ባሳተመው ጽሑፍ ዘንድ፣ የባቢሎን ታሪክ ጸሓፊ ቤሮሶ...
31513
ሥነ ቁጥር ሥነ ቁጥር የሰው ልጆች ከጥንት ጀምሮ ሥነ ቁጥርን ተጠቅመዋል። ለምሳሌ አፍሪቃ ውስጥ የተገኘ 22፣000 ዓመት እንዳለው የሚቆጠር የአጥንቶች ቁርጥራጭ ለመቁጠርና ለመደመር ያገለግል እንደነበር ይጠቀሳል። በኋላም የግብጽ እና ባቢሎን ሰወች ቁጥርን መጻፍ እንደጀመሩና ይህን ፈጠራቸውን ለመደመርና ለመቀነስ እንደተገለገሉበት አሁን የተገኙ ቅርሶች ያስገነዝባሉ። የግብጽን የአጻጻፍ ስልት የተከተሉ ግሪኮችም በዩክሊድ እና ሌሎች የግሪክ ተማሪዎች አማካይነት ጥናቱን ለማሳደግ ችለዋል። ሆኖም እስከዚህ ዘመ...
31514
ኮንታ ኮንታ ቋንቋ የኮንታ ብሔረሰብ የአፍ መፍቻ ቋንቋ ኮንቲኛ ሲሆን፣ ከ1990 ዓም ጀምሮ ከንግግር ቋንቋነት ባሻገር የትምህርትና የሥራ ቋንቋ በመሆን አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። አብዛኛው የብሔረሰቡ አባላት ከአፍ መፍቻ ቋንቋቸው በተጨማሪ ዳውሮኛ፣ ጋሞኛ፣ ወላይትኛና አማርኛ ይናገራሉ። የኮንታ ብሔረሰብ በዋናነነት በኮንታ ልዩ ወረዳ በሚገኙ በገጠር እና የከተማ ቀበሌዎች ውስጥ የሚኖር ሲሆን፣የተወሰኑ የብሔረሰቡ አባላት በተለያየ የሥራ መስክ ተሰማርተው በአጎራባች አካባቢዎች እንደሚገኙ መረጃዎች ይጠቁማ...
31515
ኦሮሞ ኦሮሞ በኢትዮጵያ፣ በኬንያና፣ በሶማሊያ የሚኖር ማህበረሰብ ነዉ። ኦሮሞ ማለት በገዳ ስርኣተ መንገስት ስር ይተዳደር የነበረ በራሱ የሚኮራ ህዘብ ነው፡በ ገዳ መንግስት ስር የ አገር መሪ በየ ፰ስምንት አመት የሚቀይር ሲሆን በተለያዩ የ ኦሮሚያ ክልሎች ንጉሳት እንደነበሩም ታሪክ ይነግረናል። በኦሮሚያ ክልሎች ከነበሩት ንጉሳት መካከል የታወቁት አባ ጂፋር ናቸው። ኦሮሚያ በ አንድሺ ስምንት መቶ ክፍለዘመን ማለቂያ ላይ በ ንጉስ ሚኒሊክ አማካኝነት ከ አቢሲኒያ ጋር ተቀላቀላ ኢትዮጵያ ስትመሰረት፣የ ቀዳሚ...