doc_id
stringlengths
1
5
text
stringlengths
42
393k
31516
ቤንች ቤንች ቋንቋ ቤንች ብሔረሰብ በቤንች ማጅ ዞን ውስጥ ከሚገኙ ስድስት ብሔረሰቦች መካከል አንዱ ነው፡፡ የብሔረሰቡ አሰያየም ‹‹ቤንችቲያት›› ከተባለው ጥንታዊ የብሔረሰቡ መሪ እንደተወለደ ይነገራል፡፡ ‹‹ታት›› የሚባለው ቃል ‹‹ጌታ›› ማለት ሲሆን ለብሔረሰቡና ለቋንቋው መጠሪያ ነው፡፡ ብሔረሰቡ ግጭቶችን የሚፈታበት የተለያዩ መንገዶች ያሉት ሲሆን፤ ግድያ ከተፈፀመ ወንጀሉ አፈፃፀም ከተጣራ በኋላ በሁለቱ ደመኞች ድንበር ላይ በሬ ታርዶ በደም ይታረቃሉ፡፡ ልጃገረድም ከገዳይ ወገን በካሳ ትሰጣለች፡፡ ...
31517
ጨረቃ ላይ መውጣት ጨረቃ ላይ መውጣት ጨረቃ ላይ መውጣት የምንለው ማናቸውም ሰው ሰራሽ መንኮራኩሮች ጨረቃ ገጽ ላይ ሲያርፉ ያለውን ክንውን ነው። ይህ እንግዲህ ሰውንም ሆነ ያለሰው የተደረጉ በጨረቃ የማረፍ ክንውኖችን ይጠቀላላል። ለመጀመሪያ ጊዜ ሰው ሰራሽ የሆነ ነገር ጨረቃ ላይ ያረፈው በመስከረም 13፣ 1959 እኤአ ሲሆን ይኸውም የሶቭዬት ህብረት ሉና 2 ሚሲዮን ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜ የሰው ልጅ እራሱ ጨረቃ ላይ የወጣው ሐምሌ 20፣ 1969 እኤአ ሲሆን ይኸውን በአሜሪካው የአፖሎ 11 ሚሲዮን መንኮራ...
31518
ሀዲያ ሀዲያ ቋንቋ የደጋማው ምሥራቃዊ ኩሽ የቋንቋ ቤተሰብ የሆነው ‹‹ሀዲይኛ›› የሀዲያ ብሔረሰብ ከአፍ መፍቻ ቋንቋቸው በተጨማሪ ከምባታ፤ ኦሮምኛንና ስልጢኛ በሁለተኛ ቋንቋነት ይናገራሉ፡፡ ሀዲይኛ ከንግግር ቋንቋነት አልፎ የጽሑፍ ቋንቋ መሆን የጀመረው በ1920ዎቹ ዓለም አቀፍ የእንግሊዝ መጽሐፍ ቅዱስ ማኀበር መጽሐፍ ቅዱስን በሀዲይኛ ቋንቋ አስተርጉም ካሳተመበት ወቅት ጀምሮ እንደሆነ መጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ከ1967 እስከ 1968 ዓም በነበረው የእድገት በኀብረት ዘመቻ ወቅት የሳባን ፊደላት በመጠቀም ለመ...
31519
ሀመር ሀመር ወይም ሐመር የኢትዮጵያ ብሔር ነው። ሐመሮች የአፍ መፍቻ ቋንቋቸውን ‹‹ሐመር አፎ›› በማለት የሚጠሩ ሲሆን፣ ሌሎች ግን ‹‹ሐመርኛ›› ይሉታል። ቋንቋው በኦሞአዊ የቋንቋ ቤተሰብ ሥር ይመደባል። የብሔረሰቡ አባላት ከራሳቸው ቋንቋ በተጨማሪ የበና፣ የአርቦሬ፣ የካራ እና የዳሰነች ብሔረሰቦች ቋንቋዎችን በሁለተኛ ደረጃ የናገራሉ። የሐመር ቋንቋ ከንግግር ወይንም ከግባቢያነት አልፎ የትምህርት ወይም የሥራ ቋንቋ ለመሆን አልበቃም። በ1999 ዓም በተደረገ የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ውጤት መሠረት የብሔረ...
31520
የኅልውና ድንጋጤ የኅልውና ድንጋጤ የኅልውና ድንጋጤ በኅልውነት ፍልስፍና እያንዳንዱ ግለሰብ ባለው የኅልውና ነጻነት ምክንያት የሚሰማው መሰረታዊ የመንፈስ አለመረጋጋትፍርሃት ነው። ለምሳሌ አንድ ሰው ከገደል ጫፍ ላይ ቢቆም ሁለት ድንጋጤወች ይጋፈጡታል፣ አንደኛው «ወድቄ ብከሰከስስ» የሚል ሲሆን ሁለተኛውና ለምንነጋገርበት ርዕስ ጠቃሚ የሆነው ደግሞ «ምናልባት እራሴን ብወረውርስ» የሚል ፍርሃቻ ናቸው ። በዚህ አጣብቂኝ ግለሰቡ ምንም የሚይዘኝ ነገር የለም ወይም ደግም በተፈጥሮየ እራሴን እንዳልወረውር የሚጠ...
31521
የኅልውና ቀውስ የኅልውና ቀውስ የኅልውና ቀውስ የምንለው አንድ ግለሰብ በህይወት ጎዳናው ላይ በድንገት ቆም ብሎ በአጠቃላይ የህይወቱ መሰረቶች ላይ ጥያቄ ሲያቀርብ ነው፡ ለምሳሌ ህይወቴ ትርጉም፣ ዋጋ ወይም አላማ አለው ወይ ብሎ ሲጠይቅ። ይህ ጉዳይ በኅልውነት ፍልስፍና ከፍተኛ ቦት ተሰጥቶት የሚጠና ነው። የኅልውና ቀውስ ብዙ ጊዜ የሚነሳው ባንድ ግለሰብ ህይወት ውስጥ ክፍተኛ ግምት የሚሰጣቸው ክንውኖች ሲፈጸሙ ነው፣ ለምሳሌ ያልን እንደሆን እንግዲህ ይህን ቀውስ ከሌሎች ለየት የሚያደርገው ጉዳይ አለ። አ...
31522
የኢትዮጵያ ሶማሊያ ጦርነት የኢትዮጵያ ሶማሊያ ጦርነት የኦጋዴን ጦርነት እየተባለ የሚታወቀው የ1977 እኤአ1978 እኤአ ጦርነት በኢትዮጵያና በሶማሊያ መንግስታት የተካሄደ ግቡም ኦጋዴን የተባለውን ስፍራ ለመያዝ ነው። በዚህ ጦርነት ሶቪየት ህብረት መጀመሪያ ሶማሊያን ትደግፍ እንጂ በኋላ ላይ ወደ ኢትዮጵያ በማዘንበል ኢትዮጵያን ረድታለች። ኢትዮጵያ በመጀመሪያ ዙር በአሜሪካ ስትረዳ ቆይታ በኋላ ላይ አሜሪካ ሶማሊያን ረድታለች። ጦርነቱ የቆመው የሶማሊያ ጦር ወደ ድንበሩ ሲመለስና የሰላም ስምምነት ሲፈጠር ነ...
31523
አይባ አይባ ከጎንደር ከተማ በስተምስራቅ በኩል 11ኪሜ ርቆ በወገራ የሚገኝ ቦታ ነው። የአካባቢው ህዝብ በገብስ፣ ስንዴምርትና በግ፣ ፍየል እርባታ መስኮች የተሰማራ ነው። የዓፄልብነ ድንግል ሚስት እቴጌ ሰብለ ወንጌል መኖሪያዋን በአይባ አድርጋ ሳለች ከ3ዓመት በኋላ በ1537 በምርኮ ወደ የመን ተሰዶ የነበረው ልጇን ሚናስን እዚሁ ቦታ እንደተረከበች የዜና መዋዕሏ ያትታል ። በኋላ፣ የአጼ ሚናስ ልጅ የነበረው አጼ ሠርፀ ድንግል ለጤንነት ሲል ከጉዛራ ለቆ የአገሪቱን ዋና ከተማ በ1582 በዚሁ በአይባ መሰረ...
31524
አመድ በር አመድ በር አመድ በር በአሞራ ገደል እና ደብረ ታቦር መካከል የምትገኝ በፎገራ ወረዳ ስር ያለች ትንሽ ከተማ ናት። አመድ በር ውስጥ፣ እንደ 2005 ህዝብ ቆጠራ፣ 5፣ 517 ሰዎች ይኖራሉ። እቴጌ ሰብለ ወንጌል 1560 ዓም አመድ በር ላይ እንዳረፈች ይጠቀሳል። ከዚያ ዘመን ጀምሮ ነገሥታቱ ክረምትን በ አመድ በርና በአካባቢው በሚገኙት አሪንጎና ቃሮዳ ያሳልፉ እንደንበር ዜና መዋዕላቸው ያትታል። ይሄውም እንደይባባ፣ አይባ፣ እንፍራዝ፣ ጣዳ፣ ወይናረብ፣ መንዘሮ ወዘተ መሆኑ ነው ። ሐዋርያ የተ...
31525
መንግሥቱ ንዋይ መንግሥቱ ንዋይ መንግሥቱ ንዋይ በ፲፱፻፰ ዓም አዲስ አበባ ላይ አራዳ ጊዮርጊስ ገዳም ሠፈር አካባቢ ተወለዱ። አባታቸው ዓለቃ ንዋይ የደብሩ ዓለቃ ነበሩ። ትምሕርታቸውን በተፈሪ መኮንን ትምሕርት ቤት ተከታትለው አዲሱ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሁለተኛ ደረጃ ትምሕርት ቤት ሲመሰረት ወደዚያ ተዛውሩ። የገነት ጦር ትምሕርት ቤት ሲከፈት ደግሞ፣ መንግሥቱ ንዋይ ተመልምለው ከገቡት ዕጩ መኮንኖች አንዱ ነበሩ። ሌሎች በኋላ ጄነራሎች እንደነ አቢይ አበበ፣ አሰፋ አያና፣ ኢሳያስ ገብረሥላሴና ከበደ ገብሬ...
31526
ቆምጬ አምባው ቆምጬ አምባው እዚህ የጎጃም ክፍለ ሀገር የአንድ ወረዳ ገዢ ነበሩ ። ቆምጬ አስተዳዳሪ ሳሉ የአንበሳ ሰል አሰርተው ከግርጌው «ጎጃም አንበሳ ነው» የሚል ጽሁፍ አሰፈሩበት ። ህዝቡም በዚህ ተደስቶ ሲኖር ሳለ ገበሬው ግብር በጊዜ አላስገባ ብሎ አስቸገራቸው ። ይህእኔ ቆምጬ ገበሬውን ሰብስበው «አሁን ይሄን አምበሳ ላም ላድርገው » በማለት ግዳጁን እንዲወጣ አደረጉት ይባላል ። አዎን፣ በቆምጬ ስም የሚነገሩ በርካታ ቀልዶች አሉ ። ያለማጋነን ቆምጬ የዘመነ ደርግ አለቃ ገብረሀና ነበሩ ። እርሳ...
31527
አናሲሞስ ነሲብ አናሲሞስ ነሲብ አባ ገመቺስ 18421923 በ 1842 በቀድሞ አጠራር ኢሉባቦር ክ ሀገር ሀሩሙ በምትባል ትንሽ መንደር የተወለደው አናሲሞስ ወላጆቹ «ሂካ» የሚል ስም አወጡለት ይህ ሂካ የሚለው ስም ተርግዋሚ ለሚለው የአማርኛ ቃል አቻ ቀረቤታ እንዳለው የቋንቅዋው አዋቂዎች ይናገራሉ በአራት አመቱ ወላጅ አባቱን በሞት ያጣው ህፃኑ ሂካ 12 አመት ሲሆነው በባርያ ፈንጋዮች ከተወለደበት ቀዬ ከዕናቱ እቅፍ ተመንጭቆ ተወሰደ ከዚያ በህዋላ የባርነት ኑሮውን በመቀጠል የምፅዋን አፈር ረግጦ ባር...
31528
የዘመነ መሳፍነት ዜና መዋዕል የዘመነ መሳፍንት ዜና መዋል በግዕዝ እንደተጻፈና በኸርበርት ጆሴፍና ዌልድ ብለንዴል ወደ እንግሊዝኛ እንደተተረጎመ ፣ በ1922 በካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ እንግሊዝ እንደታተመ ከጎን ቀርቧል። ይህ መጽሃፍ ዘመነ መሳፍንት ተብሎ በሚታወቀው ጊዜ የተነሱትን የተለያዩ ነገሥታት ግዛት በግዕዝ በኢትዮጵያውያዊ አይን እማኞች የሚመዘግብና ወደ እንግሊዝኛ የሚተረጉም ነው። መጽሃፉ የነገሥታትን ታሪክ ብቻ ሳይሆን ሌሎች ጉልበተኛ ጌቶችንመኳንንቶችንና መሳፍንቶችን ታሪክ ይዳስሳል
31529
ፓስታ ፉርኖ ፓስታ ፉርኖ አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች 2 የሾርባ ማንኪያ ዘይት 2 መካከለኛ ጭልፋ 200 ግራም ቺዝ 4 የሾርባ ማንኪያ 100 ግራም የገበታ ቅቤ 5 መካከለኛ ጭልፋ ቢሻሜል ሶስ 5 መካከለኛ ጭልፋ ቦሎኔዝ ሶስ 3 እንቁላል 1 ፓስታውን ትልቅ ብረት ድስት ውስጥ በማድረግ ቦሎኔዝ ሶስና ሦስት ጭልፋ ቢሻሜል ሶስ መጨመር፤ 2 በጭልፋ አገላብጦ በደንብ ማቀላቀልና እንቁላሉን መትቶ በመጨመር ማዋሃድ፤ 3 የዳቦ መጋገሪያ ትሪ ዘይት ቀብቶ የተዘጋጀውን ውሁድ እንደ ዳቦ መጠፍጠፍ፤ 4 የተረፈውን ቦሎኔዝ ሶስ...
31530
ቁና ሒሳብ ቁና ሒሳብ ቁና በሂሳብ ጥናት በሁለት ጠፍጣፋወች መካከል የሚገኝ የሾጣጣ ክፍል ማለት ነው። በሌላ አነገጋገር ቁንጮው የተቆረጠበት ሾጣጣ ማለት ነው። ሁለቱ ከላይና ታች ያሉ ጠፍጣፋወች መሰረት ይሰኛሉ። መሰረቶቹ ክብ የሆኑ ቁና ክባዊ ቁና፣ የቁናው አክሲስ ሁልቱን መሰረቶች በ900 ሰንጥቋቸው ካለፈ፣ ቀጥተኛ ቁና ይባላል አለዚያ የተንጋደደ ይባላል። አንድ ቁና የአንደኛው መሰረቱ ክብ ወገብ ስፋት 20 ሳንቲ ሜቲር ቢሆን እና ሁለተኛው መሰረቱ ክብ ወገብ 40 ሳንቲ ሜትር ቢሆን፣ በሁለቱ መሰረቶች...
31531
የቤት ዕቃ አቀማመጥ የቤት ዕቃ አቀማመጥ የቤት እቃ አቀማመጥ ፩ የክፍልወ ዋና አትኩረት ከሆነው ለምሳሌ እሳት ማንደጃ፣ ወይም ቴሌቪዥን ወይም መስኮት ፊት ለፊት ትልቁን መቀመጫ ብዙ ጊዜ ሶፋ በሳሎንወ ወይም ትልቁን መመገቢያ ጠረጴዛ በመመገቢያ ክፍልወ ወይም ደግሞ መኝታወን ከመኝታወ ክፍልው ያስቀምጡ። ፪ ቀጥሎ ሌሎች መቀመጫወችን ብዙ ጊዜ ወምበሮች ወይም ደግሞ ላቭ ሲት በ900 ከትልቁ እቃወ አጠገብ ያስቀምጡ። ፫ እኒህ እቃወች ከሚሰሩት “L” ቅርጽ በአግድም ትይዩ ሌሎች ታናና ሁለት መቀመጫወች ያድር...
31532
ፍካሬ ዞራሳተር ፍካሬ ዞራሳተር ፍካሬ ዞራስተር ወደ ሁሉምና ወደ ማንም በፍሬድሪች ዊልሄልም ኒሺ የተደረሰ የፍልስፍና ልቦለድ ነው። መጽሐፉ በ1883 እና 1885 እኤአ መካከል በ4 ክፍል የተደርሰ ሲሆን በጊዜው ይሰራበት ከነበረው የአስተሳሰብ ዘዴ ለየት ባለ መልኩ የፍልስፍናን እና የግብረገብን ጥናቶች መርምሯል። የመጽሃፉ አትኩሮቶች፡ የዘላለማዊ ምልልስ፣ ኃይልን መፍቀድ ፈቃድ እዚህ ላይ ጠንካራ ፍላጎት ማለት ነው፣ የአዳዲስ ዋጋ ወይም ህግጋት አስፈላጊነት፣ የአምላክ በጊዜው በነበሩ አውሮጳውያን ልብ ውስ...
31533
የዞራስተር ፍካሬ የዞራስተር ፍካሬ የዞራስተር ፍካሬ ወደ ሁሉምና ወደ ማንም በፍሬድሪች ዊልሄልም ኒሺ የተደረሰ የፍልስፍና ልቦለድ ነው። መጽሐፉ በ1883 እና 1885 እኤአ መካከል በ4 ክፍል የተደረሰ ሲሆን በጊዜው ይሰራበት ከነበረው የአስተሳሰብ ዘዴ ለየት ባለ መልኩ የፍልስፍናን እና የግብረገብን ጥናቶች መርምሯል። የመጽሃፉ አትኩሮቶች፡ የዘላለማዊ ምልልስ፣ ኃይልን መፍቀድ ፈቃድ እዚህ ላይ ጠንካራ ፍላጎት ማለት ነው፣ የአምላክ በጊዜው በነበሩ አውሮጳውያን ልብ ውስጥ መሞት፣ ስለዚህም የአዳዲስ ዋጋ ወይ...
31534
የዞራስተር ፍካሬ ክፍል ፩ የዞራስተር ፍካሬ ክፍል ፩ ክፍል ፩ በዚህ የመጽሃፉ ክፍል የዞራስተር ዋና ነጥቦች በስድስት ዋና ዋና ሃሳቦች ይጠቃላል። ትርጉሙም የመጀመሪያው የመንፈስ ለውጥ ወደ ግመል ሲሆን ይህም ትሁት መንፈስን ያመላክታል፡ እራስን መካድ፣ በሃብት መቆጠብን፣ መታዘዝንና ችግርን መቋቋምን። ይህም ግመልን እራሷን ዝቅ አድርጋ የጭነት እንስሳ እንደሚያደርጋት ባህርይ ነው። ከዚህ የግመል አለም ወደ አንበሳነት የሰው መንፈስ ለሁለተኛ ጊዜ ይሻገራል። በዚህ ጊዜ ከጭነት ነጻ ይሆናል፣ ከላይ ወደታች ...
31535
የዞራስተር ፍካሬ ክፍል ፪ የዞራስተር ፍካሬ ክፍል ፪ ዞራስተር በዚህ ወቅት ከተራራው ወርዶ ስላጋጠመው ሁኔታ ማንሰላሰል ጀመረ፣ በተለይ ኃይልን መፈለግ ኃይልን መፍቀድ የሚለውን ጽንሰ ሃሳብ ተገነዘበ። በዞራስተር አስተያየት ኃይልን መፍቀድ ህይወት ያለው ነገርን ሁሉ የሚገፋፋ መሰረታዊ ጉልበት ነው። ይህ ሃይል፣ በዞራስተር አስተያየት፣ ለመኖር ከመፍቀድ ሁሉ በላይ የሆነ ኃይል ነው። ኃይልን መፍቀድ በብዙ መንገድ ይገለጻል፣ ለምሳሌ፡ ባህታዊወች በመብላት ፍላጎታቸው ላይ ያላቸው ሃይል፣ ግለሰቦች በህብረ...
31536
ፒተር ኡስቲኖቭ ፒተር ኡስቲኖቭ ስር ፒተር አለክሳንደር ኡስቲኖቭ ከሚያዚያ 1921 መጋቢት 28 ቀን፣ 2004 እኤአ የነበረ የእንግሊዝ ተዋናይ፣ ጸሃፊና ተውኔት ደራሲ ነበር። በተለይ ደግሞ ፊልም ሰሪ፣ ቲያትር አዘጋጅ እና ኦፔራ መሪ፣ ፊልም አዘጋጅ፣ መድረክ ተላሚ፣ ፊልም ደራሲ፣ ቀልደኛ፣ ኮሜዲያን፣ ጋዜጣ አዘጋጅ፣ መጽሔት አዘጋጅ፣ ራዲዮ አስተላላፊና ቴሌቪዥን አቅራቢ ነበር። ፒተር ኡስቲኖቭ የአካዳሚ አዋርድስ፣ ኤሚ አዋርድስ፣ ጎልደን ግሎብስና ባፍታ አዋርድስን አሸናፊ ሲሆን የመንግስት ሽልማትንም ከ...
31537
ወታደሮች መዝሙር የወታደሮች መዝሙር የወታደሮች መዝሙር የሚባሉት አስራ ሁለት በጥንቱ አማርኛ የተጻፉ ግጥሞችን ነው። ከነዚህ ግጥሞች አራቱ በ1300ወቹ በአጼአምደ ጽዮን ዘመን የተጻፉ ሲሆን ምናልባትም በጣም ቀደመትና እስካሁን ካልጠፉ የአማርኛ ጽሁፎች መካከል ናቸው። እኒህ አራቱ ግጥሞች በኤድዋርድ ኡልንድሮፍ የበለጠ ተጠንተዋል። የመጀመሪያዎቹ ግጥሞች ስለ 15ኛው ክፍለ ዘመን ንጉስ፣ ስለ ቀዳማዊ አፄ ይስሐቅ የተገጠሙ ሲሆን ጣሊያናዊው ታሪክ ተማሪ ሴሩሊ የኢትዮጵያ ሥነጽሑፍ ፈርጥ ካላቸው ወገን ናቸው።...
31538
ዓፄ ይስሐቅ ዓፄ ይስሐቅ ቀዳማዊ አጼ ይሥሓቅ በዙፋን ስማቸው ዳግማዊ ገብረ መስቀል ሲባሉ እኤአ ከ14141429 የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት የነበሩ ናቸው። የቀዳማዊ አጼ ዳዊት ሁለተኛ ወንድ ልጅ ሲሆኑ የቀዳማዊ ቴዎድሮስ ታናሽ ወንድም ናቸው። ከአክሱም ነገሥታት በኋላ የመጀመሪያውን ከአውሮጳውያን መሪወች ጋር ግንኙነት ያደረገው ይሄው ንጉስ ነበር። ለምሳሌ ለአራጎን መሪ ለነበርው አልፎንሶ አምስተኛ በ1428 ዓም በእስላሞች ላይ የተባበረ ሃይልን ለመመስረት ደብዳቤ ልኳል። በዚሁ ደብዳቤ የጋብቻን ነገር ያወ...
31539
ምስካዬ ኅዙናን መድኀኔ ዓለም ምስካዬ ኅዙናን መድኀኔ ዓለም ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሥዩመ እግዚአብሔር ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የአዲሱን የምስካዬ ኅዙናን መድኀኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን መሠረት ድንጋይ ሚያዝያ ፳፯ ቀን ፲፱፻፵ ዓም ሲያስቀምጡ አትኩሮታቸው ወጣቱ ትውልድ ላይ እንደነበር ያደረጉት ንግግር ያመለክታል። “… በተፈሪ መኮንን ተማሪ ቤት ክበብ ውስጥ ይህን የአዲሱን ቤተ ክርስቲያን መሠረት ስንመሠርት በዚህ ተማሪ ቤት የሚማሩት ክርስቲያናውያን ወጣቶች የኦርቶዶክሳዊት ሃይ...
31540
የበግ እግር አሮስቶ የበግ እግር አሮስቶ ለ7 ሰው 3 መካከለኛ የበግ እግር ከነአጥንቱ 4 መካከለኛ ካሮት 4 ዝንጣፊ ሲለሪ 2 ቀጫጭን ባሮ ሽንኩርት 5 መካከለኛ ቀይ ሽንኩርት 6 የሾርባ ማንኪያ 100 ሚሊ ሊትር ዘይት 6 የሾርባ ማንኪያ 100 ሚሊ ሊትር ቬጅቴብል ስቶክ የአትክልት መረቅ 3 የሾርባ ማንኪያ የወይን ጠጅ 3 የሾርባ ማንኪያ የፉርኖ ዱቄት 1 የሻይ ማንኪያ ጨው 1 የሻይ ማንኪያ ቁንዶ በርበሬ 5 ትላልቅ ፍሬ ነጭ ሽንኩርት 1 ሥጋውን ማጽዳት፤ 2 ካሮቱንና ቀይ ሽንኩርቱን በ...
31541
የሩዝ ቅቅል የሩዝ ቅቅል የሩዝ ቅቅል ለ3 ሰው አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች 3 የቡና ስኒ 300 ግራም ሩዝ 1 መካከለኛ ጭልፋ 150 ግራም የደቀቀ ቀይ ሽንኩርት 6 የሾርባ ማንኪያ ዘይት 1 የሻይ ማንኪያ ጨው 1 የሻይ ማንኪያ ቁንዶ በርበሬ 1 ሩዙን በደንብ አጥቦ ደረቅ እስኪል ማንጠፍጠፍ፤ 2 ዘይት በደረቅ ብረት ድስት ውስጥ አሙቆ ቀይ ሸንኩርቱን በመጨመር ማቁላላት፤ 3 ሩዙን በላዩ ጨምሮ ደርቆ ቀላ ያለ መልክ እስኪያወጣ ማቁላላት፤ 4 ሩዙ በተለካበት ዕቃ እጥፍ የሚሆን ውሃ መጨመር፤ 5 አንዴ ብቻ...
31542
በቅመም የተዘፈዘፈ አትክልት በቅመም የተዘፈዘፈ አትክልት ጥሬ እቃ ግማሽ ኩባያ በቀጭኑ ሆኖ በክብ የተከተፈ ዝኩኒ ግማሽ ኩባያ ቢጫ የፈረንጅ ቃሪያ በክብ የተከተፈ ግማሽ ኩባያ በክብ የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት 16 ትልልቅ ፍሬ ፍሬሽ መሽሩም 16 ትንንሽ ቲማቲም ግማሽ ኩባያ ሶያ ሶስ ቀዩ አንድ ትልቅ የነጭ ሽንኩርት ዘለላ የተፈጨ 1 አትክልቶቹን በሙሉ ትልቅ ጎድጓዳ ሳህን ውስጥ መጨመር 2 አነስ ባለ ዕቃ ደግሞ ዘይት፣ ሶያ ሶስ፣ የሎሚ ጭማቂው እና ነጭ ሽንኩርቱን ቀላቅሎ፣ በአትክልቱ ውስጥ መጨመር፤ ከዚያ...
31543
አንድ ላይ የበሰለ አትክልት አንድ ላይ የበሰለ አትክልት ጥሬ ዕቃ ለ10 ደቂቃ ብቻ የተቀቀሉ 2 ራስ ድንቾች ልጦ በሦስት መአዘን መክተፍ 4 ካሮቶች በክብ መክተፍ 1 ራስ አበባ ጐመን የአበባው ቅርጽ ተጠብቆ መክተፍ 4 ዝኩኒዎች በክብ መክተፍ 1 የሾርባ ማንኪያ ኦሊቭ ኦይል ሌላ አይነት ዘይት መጠቀም ይቻላል 1 ሲኒ መሽሩም ሊበላ የሚችል እንጉዳይ ደርቆ ለሾርባነት የተዘጋጀ አትክልት ክኖር የደረቀ አትክልት 1 በ400 ዲግሪ ፋራናይት ወይም በ205 ድግሪ ሴሊሽየስ ኦቭን የምግብ ማብሰያውን ማሞቅ፡፡ ከዚ...
31544
የድንችና የእንቁላል ሰላጣ የድንችና የእንቁላል ሰላጣ በ15 ደቂቃ ውስጥ የሚዘጋጅ የሚያስፈልጉ ነገሮች አንድ ትልቅ ድንች፣ የተከተፈ በፈለጉት ቅርጽ መክተፍ ይቻላል ሁለት የሻይ ማንኪያ የተፈጨ ዝኩኒ Pickle relish አራት የሻይ ማንኪያ ድሬሲንግ ክሬም miracle whip መጠቀም ይቻላል ሁለት የሻይ ማንኪያ ሰናፍጭ mustard የፈረንጅ ቃሪያ ተቆራርጦ 1 እንቁላሎቹን ለመቀቀያ በተዘጋጀ ድስት ሁለት ሴንቲ ሜትር በላይ ውሃው እስኪሸፍነው ድረስ ውሃ መጨመር፤ በእሳት ላይ ከጣዱ በኋ...
31545
ጌባል ጌባል አረብኛ፦ جبيل ጁባይል፤ ግሪክ፦ Βύβλος ቢውብሎስ በሊባኖስ የሚገኝ ጥንታዊ ከተማ ነው። የጥንቱ ፊንቄ ታሪክ ጸሐፊ ሳንኩኒያቶን እንዳለ፣ ጌባል ከሁሉ ጥንታዊ ከተማ ሲሆን በንጉሡ ክሮኖስ ወይም ኤሎስ በፊንቄ ከነዓን አገር ተመሠርቶ ነበር። ለረጅም ጊዜ ከተማው የምስር ፈርዖን ጓደኛ ነበር። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በመዝሙረ ዳዊት 83፡7 እና ትንቢተ ሕዝቅኤል 27፡9 ይጠቀሳል። በኋላ 747 ዓክልበ ጌባል ለአሦር ንጉሥ 3 ቴልጌልቴልፌልሶር ተገዥ ሆነ። እንዲሁም በየተራው ወደ ፋርስ፣ መቄዶን...
31546
እንደወጣች ቀረች እንደወጣች ቀረች «እንደወጣች ቀረች» 189 ገጾች ያሉትና በ፲፱፻፵፮ ዓም የተፃፈ ሲሆን በውስጡም ከ፲፱፻፳፰ እስከ ፲፱፻፴፫ ዓም በኢትዮጵያ ላይ የተፈፀመው የኢጣልያ ወረራና በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ያመጣው አያሌ ቀውሶች በሰፊው ያትታል። በተለይም በህዝቡ መንፈስ ላይ፣ በአገሪቱ ልማድና የኑሮ ባህል ላይ በአጠቃላይ በማህበራዊ ህይወቱ ላይ ታላቅ ቀውስን ያስከተለ መሆኑንም ያብራራል። የነበረውን የጦርነት አስከፊነት መጽሐፉ ሲያትት ኢጣሊያኖች እጅግ ጨካኞች ነበሩ። በተለይም ከሀገሬው ተወላጆች...
31547
እንቆቅልሽ እንቆቅልሽ፣ የአነጋገር ዘይቤና ፍቺ እንቆቅልህ ምን አዉቅልህ ዙርያዉ ዘንዶ ማህሉ ብርንዶ ምንድ ነዉ እወቁልኝ ዙርዉ ዘንዶ ማለት እንደ ዘንዶ ተጠቅልሎ የተኛዉ፣ የምድጃ ከተር ሲሆን፣ መሃሉ ብርንዶ፣ እንደ ብርንዶ ስጋ የቀላዉ ደግሞ ፍም ነዉ። አብዛኞቹ እንቆቅልሾቻችን እና ወጎቻችን በግጥም መልክ የሚቀርቡ ሲሆን ዘዩ ጠቀስም ናቸዉ። ታድያ ፍቻቸዉን ለማወቅ ባህሉን የህብረተሰቡን አኗር ጠንቅቀን ማወቅ ያስፈልገናል። ለምሳሌ ይላሉ መምህር መስፍን መሰለ በመቀጠል ተብሎ ሲጠየቅ ጉድ መጣ ጉድ መ...
31548
የዓመፅ ኑዛዜ የዓመፅ ኑዛዜ የዓመፅ ኑዛዜ በደራሲ አቤ ጉበኛ በ፲፱፻፶፭ ዓም የተፃፈ ሲሆን 85 ገጾች አሉት። በመፅሐፉም የተገለፀው ታሪክ ሰፊ ሆኖ ደራሲው ባጭሩ ለመግለፅ ቀላልና አጭር በሆነ ዘዴ የፃፈው ነው። ታሪኩም አንድ ራሱን ወዳድ ሰው ታሪክ በኑዛዜ መልክ የሚገለፅበት ሲሆን፣ በአንድ የገጠር መንደር ውስጥ ጥሩ ኑሮ አላቸው ከሚባሉ ቤተሰቦች ውስጥ የወጣው ባለታሪክ ቤተሰቦቹን በድንገተኛ ህመምወያጣል። በድንገትም ያልተጠበቀ የቤተሰብ መበታተን ይደርሳል። በአጎቱ ሚስት ይፈፀምበት በነበረው ድርጊት ተ...
31549
ልብወለድ ታሪክ ጦቢያ ልብወለድ ታሪክ ጦቢያ ጦቢያ ወይም ልብወለድ ታሪክ ጦቢያ በአፈወርቅ ገብረ እየሱስ በ፲፱፻ ዓም በሮማ የታተመ ሲሆን 90 ገጾች አሉት። በኢትዮጵያ የሥነ ፅሑፍ ታሪክ የመጀመሪያ ልብወለድ መፅሐፍ ለመሆኑ የሚነገርለት ይህ መጽሐፍ በወቅቱ ተነስቶ የነበረውን የአረማውያንንና የክርስቲያኖችን ጦርነት ይተርካል። ደራሲው በመፅሐፉ ውስጥ ስለተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ማለትም ስለደግነትና ክፋት፣ ስለሀይማኖትና ፍቅር በሰፊው ያትታሉ። መፅሐፉ በተለይ የፍቅርን ሀያልነት ለማሳየትና የሀይማኖት ልዩነ...
31550
ማንዴልብሮት ማንዴልብሮት ቤንዋ ማንዴልብሮት 20 ህዳር 1924 – 14 ጥቅምት 2010 እኤአ ታዋቂ የ20 ና የ21ኛው ክፍለዘመን ሒሳብ ፈልሳፊና ተመራማሪ ነበር። የፍርክስክስ ጂዖሜትሪ አባት ተብሎ የሚታወቀው ይህ ሰው በዚህ በፈጠረው የሂሳብ ጥናት ዘርፍ ቅጥ የለሽና የተፈረካከሱ የጂዖሜትሪ ቅርጾችን ፣ በተለይ ባጎላናቸው ቀረብ ብለን ባየናቸው ጊዜ ሁሉ ከራሳቸው ጋር ተመሣሣይነት ያላቸውን ክስተቶችን በሂሳብ እኩልዮሽ ለመግለጽ ችሏል።ማንድልብሮት ፖላንድ አገር ተወልዶ በህጻንነቱ ፈራንሳይ አደገ ኋላም ቀሪ...
31551
መንግሥትና የሕዝብ አስተዳደር መንግሥትና የሕዝብ አስተዳደር መንግሥትና የሕዝብ አስተዳደር በቢትወደድ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ ተጽፎ በ፲፱፻፲፮ ዓም የታተመ መጽሐፍ ነው። ይህ መጽሐፍ ከመስራት የተነሳ የሰው ልጅ እንዴት ከተፈጥሮ ጥገኝነት ተላቅቆ ከኋላ ቀር አኗኗር ወደ ተሻለ ሕይወት እንደሚለወጥ የሚያስረዳ ሲሆን የዓለም ሕዝቦች የዕውቀታቸውና የሀብታቸው ደረጃ ከፍና ዝቅ ያለ መሆኑ ምክንያቱ ከጦርነት የተነሳ ነው ይላል። ጦርነቱንም የሚነሱ ነገሥታትና አለቆቹ ሁሉ ልባቸው ሀብት እንደፈለጉ አይገልፅም። ነገ...
31552
ሞኝ ባልና ሚስት ሞኝ ባልና ሚስት ሁለት ሞኝ ባልና ምሰት አብረው ሲኖሩ እንጨት ለቀማ ጫካ ሲሄዱ መንገድ ላይ ያገኚትን ሌላውን ከጫካ የሚመለሰውን ሰው ያገኙና እዛ የሚታየው ቤት ውስጥ እንዳትገቡ ረሰተን ሳንዘጋ ወተናል እቤት ውሰጥ ያሉት ማናቸውም ንብረቶች እነዳለ ነው አደራ ቢለው አንጨታቸውን ለቅመው ሲመለሱ ቀደም ሲል አደራ ያሉቸው ሰው እቤት ውሰጥ ምንም ሳያሰቀር ዘርፉቸው መቀየቱን ሳያውቁ ሲመለሱ እቤታቸው ውሰጥ ምንም ንብረት ባለማግኘታቸውና መዘረፋቸውን ሲያረጋገጡ ቀደም ሲል አደራ ያልናቸው ሰዎች...
31553
ጎልጎታ ጎልጎታ በአዲስ ኪዳን ወንጌሎች መሰረት በኢየሩሳሌም አካባቢ ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ቦታ ስም ነው። ይህ ቦታ በዮሐንስ 19፡20 «ለከተማ ቅርብ ነበረ» ሲባል እንዲሁም በዕብራውያን 13፡12 «ከበር ውጭ» መሆኑን ይመሰክራል። በአራቱ ወንጌሎች ሁሉ ስለ ስፍራው ተመሳሳይ ታሪክ አለ፦ አዲስ ኪዳን ከኢየሩሳሌም በር ውጭ እንደ ነበር ምንም ቢገልጽም፣ በ317 ዓም የሮሜ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ እናት ቅድስት ሄሌና ወደ ከተማው ሄዳ፣ የዛኔ በከተማው ውስጥ የአረመኔ ጣኦት ቤተ መቅደስ በሆነበት ስፍራ ...
31554
ፅጌ ማርያም ገብሩ ደስታ ፅጌ ማርያም ገብሩ ደስታ እማሆይ ፅጌ ማርያም ገብሩ ደስታ ዝነኛ ኢትዮጵያዊ ሙዚቀኛ ሲሆኑ የኢትዮጵያ ክላሲካል ሙዚቃዎች እናት ተብለው ይጠራሉ። ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ለመጀመሪያ ጊዜ በጀርመን ሀገር በሸክላ እንዳስቀረፁ ሁሉ እማሆይ ፅጌ ማርያምም ከዓመታት በኋላ የኢትዮጵያን ክላሲካል ሙዚቃዎች በሲዲ በማስቀረፅ ለዓለም ሕብረተሰብ ያስተዋወቁ የመጀመሪያዋ እንስት ሆነዋል። የህይወት ታሪክ ከጣሊያን ሽንፈት በኋላም በካይሮ የሙዚቃ ትምህርታቸውን ቀጠሉ። በ21 ዓመታቸ...
31555
አፖሎ ፲፩ አፖሎ ፲፩ አፖሎ 11 ለመጀመሪያ ጊዜ ሰወችን ከመሬት ወደ ጨረቃ ለማጓጓዝ የተዘጋጀ የመንኮራኩር ሚስዮን ነው። ይህ ጉዞ የተቀናበረው በአሜሪካው የጠፈር አጥኝ ተቋም ናሳ ነበር። መንኮራኩሩ ሐምሌ16 1961ዓም ከመሬት ሲመጥቅ፣ በውስጡ ሶስት ጠፈርተኞችን፣ ማለትም ኔል አርምስትሮንግ፣ በዝ አልድሪንና ማይክል ኮሊንስን የያዘ ነበር። መጓጓዣ መንኮራኩሩ ጨረቃ ላይ ከ4 ቀን በኋላ ሐምሌ 20 ሲደረስ፣ በዚሁ ቀን አርምስትሮንግና አልድሪን የጨረቃን ምድር በእግራቸው በመርገጥ የመጀመሪያወቹ ሰዎች ሆኑ።...
31556
ለማ ገብረ ሕይወት ለማ ገብረ ሕይወት ለማ ገብረ ሕይወት በሀገር ባሕል ዜማ የታወቀና በተለይም ኃይለኛ የሆነ ድምፅ የነበረው ኢትዮጵያዊ ድምፃዊና የዜማና መጽሐፍ ደራሲ ነበር። የህይወት ታሪክ በጠላት ወረራ ጊዜ ጥሩ ድምጸኛ በመሆኑና በአካባቢው ሽለላ፣ ቀረርቶ እና ፉከራ የሚችለው እንዳልነበር የሚነገርለት ለማ፣ አርበኞችን እየዘፈነ እየሸለለ ያዝናና እና ያበረታታ እንደነበር ተዘግቧል። ለማ ከ፲፯ ዓመት ዕድሜው እስከ ፲፱፻፵፪ ዓም ድረስ በጦር ሠራዊትና በክብር ዘበኛ ወታደርነት ተቀጥሮ አገልግሏል። ለማ ...
31557
ኦኩስ ወዩስ ኦኩስ ወዩስ ኦኩስ ወዩስ ሮማይስጥ፦ Ochus Veius በጣልያናዊ መኖኩሴ አኒዩስ ዴ ቪቴርቦ ጽሑፍ ዘንድ 1490 ዓም የታተመ፣ ከአባቱ ኮሜሩስ ጋሉስ ቀጥሎ በጣልያን ሀገር ለ50 ዓመት የነገሠ ነበር 23702320 ዓክልበ ግድም ማለት ነው። አኒዩስ እንዳለው፣ ይህ የታወቀ ከቤሮሶስ ሳይሆን ከጥንታዊ የጣልያ ዜና መዋዕሎች በማግኘቱ ነበር። የአኒዩስ ታሪክ በአውሮፓ መምህሮች ዘንድ ለጥቂት ዘመን ተቀባይነት ቢያገኝም፣ በኋላ ግን ምንጮቹን ሁሉ በሐሠት እንደ ፈጠራቸው የሚል ክስ ወጣና የአኒዩስ ...
31558
ሽፈራው ሽፈራው ሽፈራው ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ተክል ነው። የሞሪንጋሽፈራው ዛፍ ምንነትና ጠቀሜታው የሞሪንጋ ዛፍ በኢትዮጵያ በተለምዶ ሽፈራው በሚል የሚታወቅ ሲሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ13 በላይ ዝርያዎች ያሉትና በሁለገብ ጠቀሜታቸው ከሚታወቁት ዛፎች መካከል አንዱ ነው። በአለም ላይ ካሉት የሞሪንጋ ዛፍ ዝርያዎች ውስጥ ሰባት የሚሆኑት በምስራቅ አፍሪካ በተለይ ደግሞ በኢትዮጵያ፣ በኬንያ፣ በጅቡቲና በሶማሊያ አካባቢዎች ይገኛሉ። ሽፈራው ከሚለው ስያሜ ባሻገር የጎመን ዛፍ ወይም የአፍሪካ ሞሪንጋ Mori...
31559
ሳክሶፎን ሳክሶፎን ሳክሶፎን አንዳንድ ጊዜም ሳክስ እየተባለ የሚጠራው ዘመናዊ የትንፋሽ የሙዚቃ መሣሪያ ነው። ይህ መሣሪያ በዋናነት የሚሠራው ከነሐስ እና በውስጡ አየርን የሚያስተጋባ ኃይል ያለው ድምፅ እንዲፈጥር ተደርጎ ነው። ይህ መሣሪያ እንደ ክላርኔት ባለ ነጠላ ምላስ መንፊያ አለው። በመሳሪያው ለመጫወት በመንፊያው በኩል አስፈላጊውን ድምፅ የሚመጥን ኃይል ያለው አየር በማስገባት ነው። በመሣሪያው ወገብ ላይ ያሉትን ቁልፎች በእጅ ጣት በመጫን የድምፁን ቅጥነት እና ውፍረት መቀያየር ይቻላል። መሣሪያው ...
31560
ክላርኔት ክላርኔት ክላርኔት ዘመናዊ የትንፋሽ የሙዚቃ መሣሪያ ነው። የዚህ መሣሪያ ስያሜ የመጣው et ከምትለው የመጨረሻ ቅጥያ ትርጉሟ ትንሽ ማለት ነው። ጋር clarino የሚለውን የጣልያንኛ ቃል ትርጉሙ ትራምፔት ማለት ነው። ጋር በማያያዝ ትንሽ ትራምፔት የሚል ትርጉም በመስጠት ነው። ይህ መሣሪያ እንደ ሳክሶፎን ሁሉ ባለነጠላ መንፊያ አለው። መሣሪያውን ለመጫወት በመንፊያው ለተፈለገው የድምፅ መጠን የሚመጥን አየር በማስገባት እና በእጅ ጣቶች መሳሪያው ወገብ ላይ ያሉትን ቁልፎች በመጫን የሚወጣውን ድምፅ...
31561
አሉላ ዮሐንስ አሉላ ዮሐንስ አሉላ ዮሐንስ ታዋቂ ኢትዮጵያዊ ድምፃዊ ከመሆኑም በተጨማሪ፣ ጊታር፣ ኪቦርድ፣ አርሞኒካ፣ ከበሮ ድረምና ፒያኖን በደንብ የሚጫወት ሁለገብና ዘመናዊ አርቲስት ነው። የህይወት ታሪክ ከሙዚቃ መሳሪያዎች ጊታር በደንብ መጫወት የጀመረው ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ትንሽ እንደቆየ ነበር። በ፲፱፻፶ ዓም መጨረሻዎች ለትምህርት ወደ ጀርመን ሀገር ሄደ። ከዚያም ለሦስት ዓመት ተኩል የሕክምና ትምህርቱን ከተማረ በኋላ በማቋረጥ ወደ ኮንሰርቫቶሪ የሙዚቃ ትቤት ገባ። እዚህ የሙዚቃ ትቤት እያለም...
31562
ሙላቱ አስታጥቄ ሙላቱ አስታጥቄ ሙላቱ አስታጥቄ በጅማ ከተማ በ፲፱፻፴፭ ዓም ተወለደ። የልጅነት ጊዜውን አዲስ አበባ ውስጥ ያሳለፈው ሙላቱ በትምህርቱ ጎበዝ ስለነበረ ቤተሰቦቹ ለትምህርት መሐንዲስነት ኢንጅነሪንግ አንዲያጠና ወደ ታላቋ ብሪታኒያ ቢላክም ውስጡ በነበረው የሙዚቃ ፍቅር ተልእኮው የሙዚቃ ሆነ። ብርቅዬው የሙዚቃ ቀማሪ ላለፉት ፵ ዓመታት በጃዝ ሙዚቃ ውስጥ ኖሯል። ኢትዮጵያን ለዓለም በጃዝ ያስተዋወቀው ሙላቱ አለማኛ ውስጥ በስሙ መንገድ ተሰይሞለታል፣ በአሜሪካም የበርክሊ የሙዚቃ ኮሌጅ የመጀመሪያው...
31563
ሥልጣኔና እንጉርጉሮው ሥልጣኔና እንጉርጉሮው ሥልጣኔና እንጉርጉሮው በስነልቡና ተመራርማሪው ሲግመንድ ፍሩድ በ1929 ዓም የተጻፍ እንዲሁም በ1930 ዓም በጀርመንኛ የታተመ መጽሃፍ ነው። ከፍሩድ ስራወች ዋና ከሚባሉት ወገን ሲሆን በምዕራቡ አለም ከፍተኛ ተነባቢነት ያለው መጽሃፍ ነው። ፍሩድ መጽሃፉን የሚጀመረው የሃይማኖታዊነት ስሜት መነሻ ሊሆን ይችላል ያለውን የውቅያኖሳዊነት ስሜትን በመመርመር ነው። ውቅያኖሳዊነት ስሜት የሚለው ጽንሰ ሃሳብ አንድ ግለስብ በአንድ ወቅት ምሉዕነት፣ ወሰን አልባነትና ዘላለ...
31564
የሞንቲ ሖል ዕድል ጥያቄ የሞንቲ ሖል ዕድል ጥያቄ በዕድል ጥናት ውስጥ በቅርብ ጊዜ ታዋቂነትን ያተረፈ ጥያቄ ነው። ጥያቄው እንዲህ ነው፡ በዘልማድ እንግዲህ መኪናውን የማሸነፍ እድሉ በሁለቱም የተዘጉ በሮች ዘንዳ አንድ አይነት ይመስላል። ብዙ ሰወች እንደሚያስቡት፣ ተጫዋቹ ሃሳቡን ቀየረ አልቀየረ መኪናውን የማግኘት እድሉ አይጨምርምም አይቀንስም። ነገር ግን እውነተኛ የሂሳብ ጥናት እንደሚያስተውል የተጨዋቹ የማሸነፍ እድል ከ 13ኛ ወደ 23ኛ ያድጋል፣ ስለሆነም ሃሳቡን መቀየሩ የማሸነፍ ዕድሉን ይጨምርለ...
31565
ዕድል ጥናት ዕድል ጥናት የዕድል ጥናት የአንድን ወይም ከዚያ በላይ ኩነት እውን የመሆን ዕድል መጠነ አዝማሚያ የሚያጠና የሒሳብ ክፍል ነው። ለምሳሌ ሳንቲም በአየር ላይ ተወርውሮ መሬት ላይ ሲያርፍ ፊት ወይም ግልባጭ የመሆን ኩነት ያጋጥማል። ፊት የመሆን አዝማሚያውን የምንለካው በዕድል ጥናት ሲሆን በአጠቃላይ ሁለት ኩነቶች ስላሉ፣ ከሁለቱ አንዱ የመሆን ዕድሉ 12ኛ ወይም 05 ነው እንላለን። በአጠቃላይ መልኩ እድል ጥናት ማለት የአንድን ወይም ከዚያ በላይ ኩነት የመሆን አዝማሚያ እምነት ወይም እውቀት የ...
31566
ልዩ አንጻራዊነት ልዩ አንጻራዊነት በአልበርት አይንስታይን የተጻፈ፣ በ፲፱፻፭ ዓም ለህትመት የበቃ የተፈጥሮ ህግጋት ጥናት መጽሃፍና ርዕዮተ አለም ነው። ይህን ርዕዮተ አለም እንዲያዳብር እና እንዲያስፋፋ አይንስታይንን ከገፋፋው ዋናው ምክንያት በጊዜው የነበረው አጥጋቢ ያልሆነ የኮረንቲና ማግኔት ማዕብል ጽንሰ ሃሳብ ነበር። በአይንስታይን አስተያያት፣ በጊዜው የነበረው ርዕዮት የኮረንቲና ማግኔት ማዕበሉን ከሚከታተሉ ሰወችመሳሪያወች መርጦ ለአንዱ የሚያደላ እንደሆነ ተገነዘበ። ሆኖም ግን ጋሊልዮ የተባለው የጣ...
31567
ቲራስ ቲራስ በኦሪት ዘፍጥረት 10 መሠረት እንዲሁም ቴሬስ በዜና መዋዕል፤ ቴሬስ በመጽሐፈ ኩፋሌ የያፌት ታናሽ ወንድ ልጅ ነበረ። በዕብራይስጥ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ቲራስ ምንም ተጨማሪ መረጃ ባይጠቀስም፣ በኩፋሌ ዘንድ ምድር በተከፋፈለበት ወቅት የቲራስ ርስት በውቅያኖስ ውስጥ 4 ታላላቅ ደሴቶች ሆነ። የአይሁድ ታሪክ ጸሐፊ ዮሴፉስ 1ኛው ክፍለ ዘመን በጻፈው ታሪክ ዘንድ፣ ቲራስ የ«ጢራስያውያን» አባት ሆነ። እነዚህ በኋላ ስማቸው ጥራክያውያን እንደ ተባለ ይነግረናል። ጥራክውያንም በጥንታዊ ዘመን «ነበልባል...
31568
ደብረ ሊባኖስ ደብረ ሊባኖስ በአቡነ ተክለ ሃይማኖት ገድል መሠረት፣ ይህ ገዳም የተመሰረተው በ1300ዎቹ መጀመሪያ በራሳቸው በአቡነ ተክለ ሃይማኖት ነበር። ተክለ ሃይማኖት የግራርያን ስዩም የነበረውን ሰሜን ሰገድን ክርስትና እንዲቀበል ካደረጉ በኋላ፣ ይሄው ሹም ለተክለ ሃይማኖት አስቦ ከተባለው ስፍራ መሬት ለክርስትና ግልጋሎት በፈቃድ ስለሰጠ፣ በዚሁ ቦታ ለቅድስት ማሪያም መታወሻ የሚሆን ቤክርስቲያን ተቋቋመ። ይህ በንዲህ እንዳለ በ15ኛው ክፍለ ዘመን የቤክርስቲያኑ ቄስ ገበዝ ቴዎድሮስ ለራሳቸው ለጻዲቁ ...
31569
ከቁርሾ ወደ ሥርየት ከቁርሾ ወደ ሥርየት ሰሞኑን በሀገራችን ታሪክ እምብዛም ከማይዘወተሩ ነገሮች አንዱ ተፈጽሟል። በሥልጣን ላይ ያለ መንግሥት ከእርሱ በፊት ለነበረ መንግሥት ባለ ሥልጣናት ምሕረት አድርጓል። መግደል ያባቴ ነው ጠላቴን ማደን የምኒሊክን ዘመን ብንወቅስም የምኒሊክን ስሕተት እንደግማለን፡፡ የዐፄ ኃይለ ሥላሴን ጥፋት ብናማርርም የዐፄ ኃይለ ሥላሴን ጥፋት በእጥፍ እንደግማለን፡፡ የደርግን ወንጀል ብንኮንንም የደርግን ወንጀል እንደግመዋለንለን፡፡ ለምን ያለፈውን አጥርቶ በማየት፤ በመፈተሽ እና ...
31570
ነፍስ ነፍስ ነፍስ የአንድ ሰው ምንነት ማለት ሲሆን በብዙ ሃይማኖቶች ዘንድ ይህ ምንነት አንድ ሰው ከሞተ በኋላ እንኳ የማይጠፋ ነው። ስለሆነም ነፍስ ከአዕምሮ ጋር በብዙ ፍልስፍናዎችና ሃይማኖቶች ዘንድ የተቆራኙ ናቸው። ነፍስና መንፈስ በተለምዶ አንድ ተደርገው ቢታዩም ሁለቱ ይለያያሉ። ነፍስ፣ የአንድ ሰው ምንነት እንደመሆኑ መጠን የራሱ የሆነ መለያ ጠባዮች አሉት ስለሆነም ከሌሎች ነፍሶች ጋር አንድ ላይ ሆኖ ሊቀናጅ አይችልም። መንፈስ ባንጻሩ ለምሳሌ መንፈስ ቅዱስ አለም አቀፍ እንደመሆኑ መጠን ብዙ ነፍ...
31571
በቂና አስፈላጊ በቂና አስፈላጊ በስነ አምክንዮ በቂ እና አስፈላጊ የሚሉት ቃላቶች በጣም የጠራ ትጓሜና አጠቃቀም አላቸው። አስፈላጊ ሁኔታ P የተባለ አረፍተ ነገር ድንጋጌ Q ለተባለ ድንጋጌ እውነት መሆን አስፈላጊ ነው ከተባለ በግልባጭ ሲተረጎም P እውነት እንዲሆን የግዴታ Q እውነት መሆን አለበት ወይም P ውሸት ከሆነ Q ም ውሸት ነው እንደማለት ይቆጠራል። ለምሳሌ ማየት በQ ቢወከልና አይን በP ቢወከል፣ P ለመሆን Q አስፈላጊ ነው። Q ከሆነ ከታየ፣ P እውነት ነው ማለት ነው አይን አለ። ይህ ጉ...
31572
ኡርኑንጋል ኡርኑንጋል ኡርኑንጋል ወይም ኡርሉጋል የኡሩክ 5ኛው ንጉሥ ነበረ። በሱመራዊ ነገሥታት ዝርዝር ላይ 30 ዓመታት እንደ ነገሠ ይላል። ነገር ግን ከርሱ አስቀድሞ እንደ ነገሡት 4 የኡሩክ ነገሥታት ኤንመርካር፣ ሉጋልባንዳ፣ ዱሙዚድና ጊልጋመሽ ሳይሆን፣ በኡርኑንጋል ስም ምንም አፈ ታሪክ አይታወቅም። ከነገሥታት ዝርዝር በቀር ስሙ የሚጠቀሰው በቱማል ዜና መዋዕል ብቻ ሲሆን፣ የቱማል መቅደስ በኒፑር ከአባቱ ጊልጋመሽ ቀጥሎ እንደ ጠበቀው ይገልጻል። ከኡርኑንጋል ዘመን በኋላ 6 ነገሥታት በኡሩክ እንደ ...
31573
የሷሶን ግዛት የሷሶን ግዛት በስሜን ጋሊያ የዛሬው ፈረንሳይ አገር የተገኘና ከሮሜ መንግሥት ውድቀት በ468 ዓም በኋላ ትንሽ የቆየ የሮማውያን ግዛት ነበረ። የሷሶን መንግሥት መነሻ የሮሜ ንጉሠ ነገሥት ማዮሪያኑስ በ449 ዓም አይጊዲዩስን የጋሊያ አውራጃ ዋና አለቃ እንዲሆን በሾሙበት ወቅት ሆነ። በ5ኛው ክፍለ ዘመን የጀርመናውያን ብሔሮች ወደ ሮሜ ግዛት እየፈለሱ ነበር፣ በተለይም ቪዚጎቶች የተባለው ትልቅ ሕዝብ ለሮሜ ሰዎች እንደ ወታደሮች ስላገለገላቸው፣ መሬት በደቡብምዕራብ ጋሊያ ተሠጥተው ነበር። ብ...
31574
ተኖረና ተሞተ ተኖረና ተሞተ ተኖረና ተሞተ 69አንዲት እድሜ ልኩዋን በድህነት የኖረች አሮጊት በነ አለቃ ገብረሀና ሰፈር ውስጥ ታርፍና ሰው ለቀብር ጉድ ጉድ ሲልና ሲሯሯጥ ሲጣደፍ አለቃ በዚያው መንገድ ሲያልፉ “ምንድን ነው እጅብ እጅቡ” ብለው ይጠይቃሉ። “እንዴ አለቃ አልሰሙም እንዴ ”፥ “ምኑን”፥ “ያቺ ደሀ አሮጊት መሞቷን”። አለቃም ቀጠል ያደርጉና “አሄሄሄ ተኖረና ተሞተ” ብለው ተናገሩ። በህይወትም እያለች የቁም ሙት ሞታለች ያም ኑሮ ሆኖ ሞት ለሷም መጣባት ወይ እንደማለት ነው። መሞትዎት ነው መሞ...
31575
ፍሮይድ ፍሮይድ ሲግመንድ ፍሮይድ 1856 1939 ኦስትሪያ የተወለደ የነርቭ ሃኪም እና ስነ ልቡና ተመራማሪ ነበር። የትንተናዊ ስነ ልቡና የሳይኮአናላይሲስ አባት እየተባለ ይጠቀሳል። ፍሮይድ የአይሁድ ሃይማኖት ተከታይ ስለነበር በ1930ወቹ የሱ መጽሃፎች ተሰብስበው እንዲቃጠሉ ናዚወች አደረጉ። በ1938 የአዶልፍ ሂትለር ሰራዊት ፍሮይድና ቤተሰቦች ላይ ጉዳት ለማድረስ እንደሚሹ ሲያረጋግጥ ፍሮይድ ከነቤተሰቦቹ ቪየና ኦስትሪያን ለቆ ውወደ እንግሊዝ ተሰደደ።
31576
ደጋ እስጢፋኖስ ደጋ እስጢፋኖስ ደጋ እስጢፋኖስ በጣና ሃይቅ ውስጥ በሚገኘው ደጋ ደሴት ውስጥ የሚገኝ ቤክርስቲያን ሲሆን ወደ200 የሚጠጉ መነኮሳትን ያስተዳድራል። ቤክርስቲያኑ የተቆረቆረው በ13ኛው ክፍለ ዘመን፣ በአጼ ይኩኖ አምላክ የወንድም ልጅ በሂሩተ አምላክ ነበር። ሂሩተ አምላክ ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት ጋር በወሎ በሚገኘው ሃይቅ እስጢፋኖስ በአስተማሪያቸው እየሱስ ሞዓ የተማሩ የአንድ ክፍል ሰወች ናቸው። ቀደምቱ ደጋ እስጢፋንኖስ በ19ኛው ክፍለ ዘመን በእሳት ሲቃጠል አሁን የቆመው ቤክርስቲያን በም...
31577
ሠርፀ ድንግል ሠርፀ ድንግል ዓፄ ሠርፀ ድንግል 1542 መስከረም 27 1590 በዙፋን ስማቸው መለክ ሰገድ ኢትዮጵያን ከ1555 1590 ዓም የመሩ ንጉሥ ነበሩ። አባታቸው ዓፄ ሚናስ ሲሆኑ እናታቸው ደግሞ እቴጌ አድማስ ሞገስ ነበሩ። ከግራኝ ወረራ ጀምሮ እስከ ዓፄ ሚናስ ዘመን የቀጠለው አለመረጋጋት በኒህ ንጉሥ ዘመን አንጻራዊ እልባት አግኝቷል። ለዚህ ተጠያቂ የሚሆኑ አራት ጉልህ ክስተቶች፡ ፩ በሰሜን የቱርኮች ወረራ በንጉሡ ወታደራዊ ብቃት በመክሸፉ ፪ በደቡብ የባሬንቱ ኦሮሞዎች ሐረርን በመውረራቸው...
31578
ኤላም የሴም ልጅ ኤላም የሴም ልጅ ኤላም עֵילָם በብሉይ ኪዳን ኦሪት ዘፍጥረት የዕብራይስጥ መጽሐፍ ቅዱስ 10፡22 መሠረት ከኖኅ ልጆች መካከል የሴም በኩር ልጅ ነበረ። «ኤላም» ማለት በብሉይ ኪዳን ደግሞ ጥንታዊት ሀገር ኤላምና ሕዝቧ ያመለከተ ነው። እኚህ ሕዝብ ከኤላም ሴም ኖኅ እንደ ተወለዱ ይታመናል። የአሁኑ ሊቃውንት ኤላምኛ ከሴማዊ ቋንቋዎች መካከል አለመገኘቱ ቢያወቁም፤ በኦሪት ዘፍጥረት አስተያየት የሰው ልጅ ልሳናት ሁሉ በባቢሎን ግንብ ስለ ተደበለቁ የቋንቋ አለመዛመድ ጥያቄ ምንም አያስቸግ...
31579
አሦር የሴም ልጅ አሦር የሴም ልጅ አሦር ዕብራይስጥ፦אַשּׁוּר አሹር በብሉይ ኪዳን ኦሪት ዘፍጥረት የዕብራይስጥ መጽሐፍ ቅዱስ ምዕራፍ 10 መሠረት ከኖኅ ልጆች መካከል የሴም ሁለተኛ ልጅ ነበረ። የጥንታዊ አሦር ሀገርና ሕዝብ አባት መሆኑ ይታመናል። በዘፍጥረት 10፡11 መሠረት ይህ አሦር ከሰናዖር ወጥቶ «ነነዌን፥ የረሆቦትን ከተማ፥ ካለህን፣ በነነዌና በካለህ መካከልም ሬሴንን ሠራ፤ እርስዋም ታላቂቱ ከተማ ናት።» አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ግን ከፊተኛው ቁጥር ከ10፡10 በመውሰድ አድራጊው ...
31580
ክሪስታቮ ደጋማ ክሪስታቮ ደጋማ ክሪስታቮ ደጋማ ከ፲፭፻፰ አካባቢ እስከ ነሐሴ ፳፮ ቀን ፲፭፻፴፬ ዓም በኢትዮጵያ የፖርቹጋሎችን ጦር መሪ የነበረ 154143 ሲሆን የግራኝ አህመድን ሰራዊት ቁጥሩ በጣም ባነሰ ሰራዊት አራት ጊዜ አሸንፎች በአምስተኛው ጊዜ ተማርኮ ሃይማኖቴን አልቀይርም ሲል የተገደለ አዋጊ ነበር። ሪቻርድ በርተን የተባለ የታሪክ ተመራማሪ ክሪስታቮን በጀግኖች ዘመን የተወለደ ቀደምት ጀግና ነበር ሲል አድንቆታል። በሌላ በኩል ክሪስትቮ የታዋቂው አለም አቀፍ ተጓዥ ቫስኮ ደጋማ ልጅ ነበር። ክሪ...
31581
ባቲ ድል ወምበሬ ባቲ ድል ወምበሬ ባቲ ድል ወምበሬ 1543 1552 የአዳል ገዢ እንዲሁም የዘይላ አስተዳዳሪ የነበረው ኢማም ማህፉዝ ልጅ የነበረች ሲሆን አባቷ ከሞተ በኋላ ግራኝ አህመድን አግብታ በባሏ ዘመቻ ሁሉ ተሳታፊ የነበረች ሴት ናት። ግራኝ ከተገደለ በኋላ የእህቱ ልጅ የነበረውን ኑር ኢብን ሙጃሂድ በማግባት የባሏን ሞት የተበቀለች የአዳል መሪ ናት። ባቲ የሚለው ቃል ማዕረጓን ሲያሳይ፣ «ድል ወምበሬ» የሚለው ስያሜ ደግሞ በአማርኛ «የብዙ ድል ባለቤት ነኝ» የሚል ሃሳብ በጠላቶቿ ላይ ለማስረፍ ...
31582
ሰብለ ወንጌል ሰብለ ወንጌል እቴጌ ሰብለ ወንጌል 1482 1560ዓም የዓፄ ልብነ ድንግል ሚስት ስትሆን ከንግስት እሌኒ ሞት በሁዋላ በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ ቦታ የነበራት ሴት መሪ ናት። የነበረችበት ዘመን፣ የአህመድ ግራኝ ጦር በቱርክ ጠመንጃ አንጋቢወች ታግዞ ብዙ የኢትዮጵያን ክፍል የተቆጣጠረበት ወቅት ነበር። በዚህ የጦርነት ዘመን የመጀምሪያ ልጇ ፍቅጦር ሲገደል አራተኛው ልጇ የወደፊቱ አጼ ሚናስ በምርኮ ወደ የመን ተግዞ ነበር። ዓፄ ልበነ ድንግል በ1540 ዓም በደብረ ዳሞ በህመም ከሞተ በኋላ ...
31583
ጥሩነሽ ዲባባ ጥሩነሽ ዲባባ ጥሩነሽ ዲባባ ቀነኔ የተወለደችው ከአባትዋ ከአቶ ዲባባ ቀነኔ እና ከእናትዋ ከወይዘሮ ጉቱ ቶላ በ 1978 ዓም በኢትዮጵያ በአርሲ ክፍለ ሀገር በቼፋ ወረዳ ከኦሮሞ ብሄረሰብ ነው። ጥሩነሽ ለቤተሰብዋ ከአምስት ልጆች ሶስተኛዋ ናት። የጥሩነሽ ዲባባ አስተዳደግ ከሌሎች አትሌቶች ትንሽ ለየት ያለ ነው። ይሀውም ትምህርት ቤት ለመሄድ መሮጥ አልነበረባትም። ምክንያቱም ትምህርት ቤቷ ከቤቷ ርቀቱ የአስር አምስት ደቂቃ የእግር ጉዞ ስለነበር። ጥሩነሽ መሮጥ አያስፈልጋትም ነበር ካላረፈደች...
31584
ኢቤሩስ ኢቤሩስ ኢቤሩስ ወይም ኢቤር፣ ኢቤሮ በእስፓንያ አፈ ታሪክ ዘንድ ከቶቤል በኋላ ለ37 አመት ምናልባት 22652228 ዓክልበ የእስፓንያ 2ኛው ንጉሥ ነበረ። ከኢቤሩስ ስም የእስፓንያ ጥንታዊ መጠሪያ «ኢቤሪያ» Iberia እንዳገኘው ይባላል፤ እንዲሁም ኢቤራውያን ሕዝብ ስለርሱ እንደ ተሰየሙ ተብሏል። በተጨማሪ በሮማይስጥ «ኢቤሩስ» ማለት በእስፓንያ የሚፈስሰው አሁን ኤብሮ ወንዝ የሚባለው ወንዝ ሲሆን፣ ይህ ወንዝ ስሙን ከቶቤል ልጅ ኢቤሩስ እንደተቀበለው ይታመናል። እንዲሁም ይህ ንጉሥ ኢቤሩስ በደ...
31585
እሌኒ እሌኒ ንግስት እሌኒ የአጼ ዘርዓ ያዕቆብ ሚስት ስትሆን ከንጉሱ ሞት በኋላ በሌሎች ሶስት ነገስታት ዘመን ከፍተኛ የአስተዳደር ስራ ፈጽማ በ1522 ከዚህ አለም በሞት አርፋለች። የተቀበረችውም በትልቅ ጥበብ ባሰራችው ቤክርስቲን መርጡለ ማርያም፣ ጎጃም ነው። እሌኒ የሃድያው ንጉስ መሐመድ ልጅ ስትሆን ዘርዓ ያዕቅብን ባገባች ጊዜ ክርስቲያን ሆናልች። አንዳንድ ታሪክ ጸሃፊያን ለምሳሌ ባላዛር ቴሌዝ ፖርቱጋላዊው ልጅ እንዳልነበራት ሲዘግቡ ፍራንሲስኮ አልቫሬዝ ግን በልብነ ድንግል ዘመን አንዱ ወንድ ልጇ ከ...
31586
የፍሎሬንታይን ሐዘን Michelangelo የፍሎሬንታይን ሐዘን Michelangelo የፍሎሬንቲን ሐዘን ወይም ኢየሱስ ክርስቶስ ከመስቀል እንደወረደ ሐዘናቸውን ለማሳየት የተቀረጸ ሐውልት ነው። ይህ ሐውልት የተቀረጸው ከ እምነ በረድ ነው። ሐውልቱ የተቀረጸው በ እንደገና መወለድ ቀራጭ ማይክል አንጄሎ ቡናሮቲ ነው። ማይክል አንጄሎ በዚህ ሐውልት ላይ ከ1547 እስከ 1553 ድረስ ስርቶበታል። በሐውልቱ ላይ አራት ሰዎች ይታያሉ። ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱ ክርስቶስ ሞቶ ከመስቀል ላይ ሲያወርዱት ኒቆዲሞስ ወይ...
31587
ውርዴ ወይም ፈንጣጣ ውርዴ ወይም ፈንጣጣ በተጋባ ከ10 እስከ 90 ቀናት ባሉት ውስጥ የበሽታው የመጀመሪያ ምልክቶች ይታያሉ። የውርዴ ቁስል ይወጣል፣ ካልታከመም የውርዴው ቁስል እየባሰ ይሄዳል። በመጀመሪያ ደረጃ የሚገኝ ውርዴ በቀላሉ ሊታከምና ሊድን ይችላል። ግን በሓኪም ትእዛዝ እንጂ ከፋርማሲ ማንም ሰው የሚገዛቸው መድሓኒቶች ባክተሪያውን ሊያጠፉት ኣይችሉም። ሓኪም የሚያዝዘው መድሓኒት ውርዴውን ቢያጠፋውም እንኳን በኣካል ላይ ለደረሰውጉዳትና ጠባሳ ለማከም ኣይቻል ይሆናል። ውርዴን መከላከል ይቻላል። እን...
31588
ሉሉቢ ሉሉቢ ሉሉቢ ወይም ሉሉቡም በ24001900 ዓክልበ ግድም በዛግሮስ ተራሮች በዛሬው ኩርዲስታን ኢራቅና ኢራን የነበረ ጥንታዊ አገር ነበረ። ከተማቸው ሉሉባን ወይም ሉሉቡና በዘመናዊው ሐለብጄ ሥፍራ እንደ ነበር ይታስባል። ከዚህ በኋላ በአካድ መንግሥት ዘመን፣ ሉሉቡም ከታላቁ ሳርጐን ተገዥ አገሮች መካከል አንድ ሆኖ ይታያል። ከሉሉቢ ወደ ደቡብ ከሆነው ከጉቲዩም ጋር ይገዛ ነበር። የሳርጐን ልጅልጅ ናራምሲን ደግሞ ሉሉባውያንን ከነንጉሳቸው ሳቱኒ አሸንፎአቸው 2034 ዓክልበ ግ፣ ድል ማድረጉን ለማስታወ...
31589
ማርኮ ፖሎ ማርኮ ፖሎ ማርኮ ፖሎ 1254 ጥር 8፣ 1324 ጥንታዊው የጣሊያን ተጓዥ እና ነጋዴ ነበር። ታዋቂነትም ያተረፈው በተለይ ወደቻይና እና ሞንጎሊያ ከተጓዙት አውሮጳውያን ቀደምትነት ስለነበረው ነው። በዚህ ምክንያት ከሱ በኋላ ዘግይተው የተነሱት እነ ክርስቶፎር ኮሎምበስ ሳይቀር ለሱ ከፍተኛ ግምት እና አድንቆት እንደነበራቸው ታሪክ ይዘክራል። ት 1 17 አመት ሲሞላው ከጣሊያን ቬኒስ ከተማ በመነሳት፣ መጀመሪያ በጀልባ ከዚያም በእግሩና በግመል ተራሮችን በርሃን አቆራርጦ ቤይቺንግ ቻይና በድሮ ስሟ...
31590
ይግባ ጽዮን ይግባ ጽዮን ዓጼ ይግባ ጽዮን በዘውድ ስማቸው ቀዳማዊ ሰለሞን ከ1285 1294 እኤአ ሲነግሱ ከአባታቸው ይኩኖ አምላክ ጋር ከንግስናቸው በፊት አገሪቱን አብረው አስተዳድረዋል። በዚህ ንጉስ ዘመን የነበረው ታዋቂው የአውሮጳ ተጓዥ ማርኮ ፖሎ ስለአጠቃላይ የኢትዮጵያ ግዛትና በተለይ ንጉሱ በአዳል ላይ ያደረገውን ውጊያ በ1290 ባሳተመው መጽሃፉ ላይ ጠቅሷል፡ የእስልምና መስፋፋት በዚህ ድል ምክንያት ሰላም በመገኘቱ የእስልምና ተከታይ የሆኑ ነጋዴወች ለመጀመሪያ ግዜ የኢትዮጵያውን ውስጠኛውን ...
31591
ሰይፈ አርድ ፬ኛ ሰይፈ አርድ ፬ኛ አጼ ሰይፈር አርድ ፬ኛ የአጼ ይግባ ጽዮን ልጅ የአጼይኩኖ አምላክ የልጅ ልጅ ሲሆኑ ከ12941295 ለአንድ አመት ንግሱ ነገስት ነበሩ። ታሪክ ጻህፍት እንደሚሉት አባታቸው ይግባ ጽዮን 5 ወንድ ልጆች ስለነበሩዋቸውና የትኛው ንጉስ እንዲሆን መምረጥ ስላልቻሉ እያንዳንዱ ወንድ ልጅ አንድ አንድ አመት እንዲነግስ ቃል ስላስገቡዋቸው 1 አመት ብቻ ነግሰዋል ህዝብ አስገድ ህዝብ አስገድ አጼ ህዝብ አሰገድ የአጼ ይግባ ጽዮን ልጅ የአጼይኩኖ አምላክ የልጅ ልጅ ሲሆኑ ከ12951...
31592
ኪሽ ኪሽ ኪሽ የሱመር የዛሬው ኢራቅ ጥንታዊ ከተማ ነበረ። የሱመር ነገሥታት ዝርዝር በተባላው ሰነድ ዘንድ፣ ከማየ አይኅ በኋላ መጀመርያው ነገሥታት የነበሩበት ከተማ ኪሽ ሲሆን መጀመርያው ንጉሣቸው ጙሹር ነበር። የጙሹርም ተከታይ ኩላሢናቤል ሲባል፣ ይህ ስያሜ ግን በአካድኛ «ሁላቸው ባል ሆኑ» የሚለው ዓረፍተ ነገር ነው። ምናልባት በኪሽ መሃል ሥልጣን አለመኖሩን ለማመልከት እንደ ጠቀመ ይታስባል። በሰነዱ የሚከተሉት 9 ስሞች ደግሞ ሁላቸው በአካድኛ የእንስሳት ስሞች ናቸው ለምሳሌ ዙቃቂፕ «ጊንጥ»። አካድ...
31593
የፍርድ ቀን የፍርድ ቀን የፍርድ ቀን በማይክል አንጄሎ ቡናሮቲ የፍርድ ቀን የተባለው ስዕል የሚገኘው በቫቲካን ከተማ በሲስቲኒ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከመንበሩ በስተ ጀርባ በኩል ከሚገኘው ግድግዳ ላይ ነው። ማይክል አንጄሎ ቡናሮቲ ይህን ስራ ለመጨረስ አራት አመት ፈጅቶበታል። ማይክል አንጄሎ ይህን የፍርድ ቀን የተባለውን ስእል የሰራው ዘፍጥረትን በዚሁ ቤተ ክርስቲያን ጣሪያ ላይ በሰራ በሰላሳ አመቱ ነው። ስራው በጣም ትልቅ እና ግድግዳውን በሙሉ ያካተተ ነው። ስራው በ1537 ተጀምሮ በ 1541 ተፈጸመ ።...
31594
የታኅሣሥ ግርግር የታኅሣሥ ግርግር ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ፣ ከግርግሩ ክሽፈት በኋላ ለውጭ ጋዜጠኞች ከሰጡት ቃለ ምልልስ። ወጣቱ ትውልድ በሚያየው የኤሊ እርምጃ እና ለዚህም ምክንያት ናቸው ብሎ ባመነባቸው በንጉሠ ነገሥቱና አስተዳደራቸው እጅግ ተደናገረ። እነዚህ ወጣት መሪዎች፣ አንዳንዶቹም ውጭ የተማሩ የጥንታዊው ስርዓት ባለሥልጣናት ልጆች ቢሆኑም እርምጃው እንዲፋጠን፤ ዘመናዊ አዲስ ስርዓት እንዲመሠረት ያላቸውን ምኞትና ዓላማ ለማራመድ ሲሹ በግድ የንጉሠ ነገሥቱና የስርዓታቸው ተቃራኒ ኃይሎች መሆናቸው አልቀ...
31595
የኤልያስ ራዕይ የኤልያስ ራዕይ በጥንት ለአይሁዶችና ለክርስቲያኖች የታወቀ ትንቢት ነው። ይህ ትንቢት በ2 የተለያዩ መጽሐፍት ይገኛል። እነርሱም የዕብራይስጥ አይሁድ ትርጉም ሠፈር ኤሊያሁ፣ እና በቅብጢኛ የተጻፈው በክርስቱያኖች የተዘጋጀ ትርጉም ናቸው። እነዚህ ብርቅ ጽሑፎች በሰፊ አልታወቁምና መቸም ቀኖናዊ ሳይቆጠሩ ከአዋልድም መጻሕፍት ውጭ ቀሩ። እያንዳንዱ ትርጉም የነቢይ ኤልያስ ስም ስላለበት፣ ለዚህ ነው «የኤልያስ ራዕይ» የተባለው እንጂ በኤልያስ እራሱ እንደ ተጻፈ አይመስልም ወይም አይልም። ዛሬ ያ...
31596
ጣይቱ ብጡል ጣይቱ ብጡል የሸዋው ንጉሥ ምኒልክ በሸዋ የዓፄ ቴዎድሮስ እንደራሴ ከነበሩት አቶ በዛብህ ጋር ነሐሴ ፲፯ ቀን ፲፰፻፶፯ ዓም በጋዲሎ አካባቢ በተደረገው ጦርነት ድል አድርገው ወደ አንኮበር ገብተው በነሐሴ ፳፬ ቀን ነገሡ። በነገሡም በአሥራ ሁለት ዓመታቸው የፋሲካን በዓል በባሕር ዳር አቅራቢያ ሱሉልታ ላይ ዋሉና ደብረ መይ በጣይቱ ብጡል እናት በወይዘሮ የውብዳር ቤት ከጣይቱ ብጡል ጋር ተጫጭተው ስለጋብቻቸው ተነጋገሩ። ከዚያም ዋና ከተማቸው ወደነበረችው ደብረ ብርሃን ተመልሰው መጡ። እቴጌ ጣይቱ...
31597
ዞራስተር ዞራስተር ዞራስተር በጥንቱ የፋርስ ግዛት ያሁኑ ኢራን የኖረ የዛራጡሽትራ ሃይማኖት መስራች ነበር። ሃይማኖቱ በጣም ረጅም ታሪክ የነበረውና በሳሳሲን ስርወ መንግስት የፋርስ አገር ብሄራዊ ሃይማኖት ነበር። አብዛኛው ተመራማሪወች እንደሚስማሙ፣ ዞራስተር በርግጥ በህይወት የነበረ ሰው ነው። በግምት ከዛሬ 3200 አመት በፊት እንደኖረ ማለት ከክርስቶስ ልደት በፊት በ13ኛው ክፍለ ዘመን ይተመናል። ሆኖም ግን ይህ እርግጠኛ ጊዜ አይደለም፣ አንዳንዶች የነቢዩን ዘመን ከ18ኛው እስከ 9ኛው ከክርስቶስ ል...
31598
አባ ጎርጎርዮስ አባ ጎርጎርዮስ አባ ጎርጎሪዮስ እስክንድር 1595 1658 ከመካነ ስላሴ ወሎ የመጡ ቄስና የኳንንት ዘር ነበሩ። ከጀርመናዊው ሉዶልፍ እዮብ ጋር በመሆን በአማርኛና በግዕዝ ብዙ መዝገበ እውቀቶችን ጽፏል። በ1652 ሉዶልፍና እሱን ይደጉመው የነበረው የሳክስ ጎታ እና አምስታድት መስፍን ኸርነስት ዘ ፒየስ ባደረጉለት ግብዣ፣ ጎርጎሪዮስ ለጥያቄያቸው መልስ በመስጠት የግዕዝ መዝገበ ቃል እና ከዚያም የአማርኛ ሰዋሰው እና መዝገበ ቃል ሊያሳትሙ በቁ። ከዚህና መሰል ስራወቻቸው በሁዋላ ወደ ኢትዮጵ...
31599
አበበ ቢቂላ አበበ ቢቂላ አበበ ቢቂላ ነሐሴ ፴ ቀን ፲፱፻፳፭ ዓም በሸዋ ጠቅላይ ግዛት በደብረ ብርሃን አውራጃ፣ ደነባ ልዩ ስሟ ጃቶ ከምትባል ሥፍራ ላይ ከአባቱ አቶ ቢቂላ ደምሴና ከእናቱ ከወይዘሮ ውድነሽ መንበሩ ተወለደ። ወጣቱ አበበ እንደአካባቢው ልምድ በእረኝነትና በትምሕርት ተሰማርቶ በአሥራ ሁለት ዓመቱ የቄስ ትምሕርቱን አጠናቀቀ። በዚህ በጨቅላ ዕድሜው ስመ ጥሩ የገና ተጫዋች እንደነበር ይነገርለታል። በ፲፱፻፵፬ ዓም አዲስ አበባ ሄዶ በክብር ዘበኛ በወታደርነት ይቀጠርና በገና ጨዋታ እና በስፖርት...
31600
በገና በገና በገና በተወጠሩ ክሮች የሚሰራ የኢትዮጵያ የሙዚቃ መሳሪያ ነው። በገና ሌላው ስሙ በግዕዝ እንዚራ ተብሎ ይጠራል። ቁመቱ ረዘም ገበታው ሰፋ ያለ ከ 90 ሳንቲ ሜትር እስከ 140 ሳንቲ ሜትር ርዝመት ያለውና 10 ጅማቶች አውታሮች ያሉት ጥንታዊ የኢትዮጵያ የባህል የሙዚቃ መሳርያ ነው። ሳጥኑ፣ ምሰሶዎቹ፣ ብርኩማውና ቀምበሩ ከንጨት የሚሰሩ ናቸው። አውታሮቹም ከጅማት ይሰራሉ። ሳጥኑ በበግ ወይም በከብት ቆዳ ይሸፈናል። ድዝና ጥዝ እንዲል 10 ቁርጥራጭ ቆዳዎች በብርኩማውና በአውታሮቹ መካከል ይስተ...
31601
ሆ ቺ ሚን ሆ ቺ ሚን ሆ ቺ ሚን ከ18901969 እኤአ የኖረ የቬትናም ኮሚኒስት ፓርቲ መሥራችና መሪ ነበር። ሆ ቺ ሚን ከወጣትነት ጊዜው ጀምሮ ለአብዮታዊ ተግባራት የቆመ ነበር። ሆ ቺ ሚን በሥራ ምክንያት ፈረንሳይ ውስጥ በነበረበት ወቅት የካፒታሊስት ሥርዓት ምን ያህል ሠርቶአድሩን ሕዝብ ለሥቃይና ለመከራ እንደዳረገውና የዓለም ወዛደሮች በቀለም በቋንቋና በባህል ቢለያዩም ብሶታቸው አንድ መሆኑን በቅርብ ተገነዘበ። በአፍሪካና በእስያ የኢምፔሪያሊስቶች መምጣት ምን ያህል ሥቃይና ውርደት በእነዚህ ሕዝቦች ላ...
31602
ዓፄ በካፋ ፋ ዓጼ በካፋ የዘውድ ስም መሲህ ሰገድ ወይም አድባር ሰገድ የነገሡት ከእኤአ ከግንቦት18፣ 1721 እስከ መስከረም 19፣1730 ነበር። በካፋ የቀዳማዊ እያሱ ልጅ ሲሆን ከሱ ቀድሞ የነገሱት ቀዳማዊ ተክለሃይማኖትና ሳልሳዊ ዳዊት ወንድም ነበር። ባካፋ ህጻንነቱን ያሳለፈው ወህኒ አምባ ላይ ነበር። ሆኖም ግን በንጉስ ዮሥጦስ መጨረሻ ዘመን አካባቢ በተነሳ ግርግር ሳቢያ ከወህኒ አምልጦ ከኦሮሞ ቡድኖች ስር ተደበቀ። ሳይቆይም በመማረኩ ለወደፊት እንዳይነገስ አፍንጫው ላይ ጠባሳ ተደረገበት። ነገ...
31603
ወልደ ጊዮርጊስ ወልደ ዮሐንስ ወልደ ጊዮርጊስ ወልደ ዮሐንስ ፀሐፊ ትዕዛዝ ወልደ ጊዮርጊስ ወልደ ዮሐንስ ፲፰፻፺፫ ዓም ፲፱፻፷፰ ዓም በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት በተላለያዩ ጊዜያት የፅሕፈት፤ የእርሻ፤ የአገር ግዛት እና ገንዘብ ሚኒስቴር እንዲሁም የጠቅላይ ግዛት አስተዳዳሪ በመሆን አገልግለዋል። በሥነ ፅሁፍም መስክ ላይ የድርሰት መፅሐፍቶችን ያበረከቱ እንደዚሁም በትውልድ አገራቸው ቡልጋ ቤተ ክርስቲያን ያሠሩ ትልቅ ሁለ ገብ ሰው ነበሩ። ወደፊት የንጉሠ ነገሥቱን መንግሥት የሚደመድመው የስድሳ ስድ...
31604
መባዓ ጽዮን መባዓ ጽዮን መባዓ ጽዮን በሌላ ስማቸው ተክለ ማርያም በዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመን የነበሩ ጻድቅ ሰው ሲሆኑ በተወለዱ በ፸፬ ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ተለይተዋል። ገድላቸው እንደሚጠቅሰው በሸዋ ግዛት አንዳገብጣን ይባል እነበር ቦታ ከአባታቸው ሀብተ ጽዮንና እናታቸው ጽዮን ትኩና በስለት ተወለዱ። ቀጥሎም ከአባታቸውና ከተለያዩ ቀሳውስት ትምህርት በመቅሰም አድገው እራሳቸውን በጾምና ጸሎት በማነጽ ቅድስናን አግኝተዋል። በዚህም መካከል ወደ ዳሞት በመሄድ ገብረ ክርስቶስ ለሚሰኙ ቄስ ጋር በ እንግድነት...
31606
ደብረ ታቦር ዓመት በዓል ደብረ ታቦር ወይንም ቡሄ በመላው ሀገራችን በየዓመቱ ነሐሴ ፲፫ ቀን የሚከበር በዓል ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከምታከብራቸው ዓቢይ ዋና በዓላት አንዱ ይሄ ደብረ ታቦር የምትለው የቡሄ በዓል ነው። የበዓሉ መሠረት ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው። በፊታቸውም ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ። በዋዜማው የሠፈር ልጆች በየቤቱ እየዞሩ ሆያ...
31607
ሾጣጣ ሾጣጣ ሾጣጣ እንግሊዝኛ፦ cone ሰፋ ካለ መሰረት ተነስቶ ቀስ በቀስ በለሰለሰ መልኩ ሳይቆረፍድ እየጠበበ በመሄድ መጨረሻው ቁንጮ ከምትባል ነጥብ ላይ የሚያበቃ፣ 3 ቅጥ ያለው የጂኦሜትሪ ቅርጽ ነው። ብዙ ጊዜ በሂሳብ ሾጣጣ ሲባል ክብ መሰረት ያለውን የጂኦሜትሪ ቅርጽን ይወካላል። ነገር ግን ይህ አንዱ ታዋቂ አይነት ሾጣጣ እንጂ ሌሎች አይነቶችም ለምሳሌ እንደ ፒራሚድ አሉ። ሾጣጣ ሰፋ ያለ ትርጉም ያለውና ብዙ ቅጾችን ያስተናግድ እንጂ በተለምዶው ሂሳብ የምንጠቀምበት ሾጣጣ የእንዝርት ፈትልን ይመስ...
31608
ገብረ ክርስቶስ ገብረ ክርስቶስ ገብረ ክርስቶ በሌላ ስሙ አብዱል መሲህ የቆንስታቲኖፕሉ ንጉስ ቲወዲሰይስ ልጅ የነበረ ጻድቅ ነው። የዚህ ጻዲቅና መባዓ ጽዮን የተባለው የኢትዮጵያ ጻዲቅ ገድሎች ተከለ ሃይማኖት በተባለ ሃብታምና ሚስቱ ወለተ ጽዮን አነሳሽነት ምክሖ ጊዮርጊስ በተባለ ፀሐፊ በአንድ መጽሃፍ እንዲጻፉ ተደረገ። ይህ መጽሐፍ እጅግ በተዋቡ ደማቅ ስዕሎች ያሸበረቀ ሲሆን ሰአሊው ኢግናጦስ የሚባል ሰው ሊሆን ይችላል በማለት ታሪክ ተመራማሪው ዋሊስ በጅ ገምቷል መጽሃፉ በዓፄ ቴወድሮስ መቅደላ ላይ ሊያ...
31609
አፈወርቅ ተክሌ አፈወርቅ ተክሌ የዓለም ሊቀ ሊቃውንት፣ የኪነ ጥበብ ምሑር የተከበሩ ሰዓሊ አፈወርቅ ተክሌ ጥቅምት ፲፫ ቀን ፲፱፻፳፭ ዓም ሚያዝያ ፪ ቀን ፳፻፬ ዓም፤ ‘’ኪነ ጥበብ የሰው ልጅን መንፈስ ለማዳበር፣ ሀገራችንን ለማሳደግ፣ ለማሳወቅ እና ለሕይወታዊ ኑሮ ተስፋ ለመፍጠር የላቀ ሚና ይጫወታል’’ ይላሉ። ለጥቀውም ‘’ዛሬ የምንሠራው ሥራ የዛሬን ሕይወት እያንጸባረቀ ለነገው ትውልድ ፈር መቅደድ አለበት፡፡” በሚል ስሜት ኪን ማንኛውንም የሰው ኑሮ ረገድ የሚነካ እንደሆነ ያስረግጣሉ። አፈወርቅ ተክሌ...
31610
ንጥረ ነገር ንጥረ ነገር ንጥረ ነገር በታሪክ ንጥረነገር elements ፡ በግእዝ የሚታወቅ ክስተት ነው። «ፎር ኤሌሜንት» በግእዝ አራቱ ባሕርያት ይባላል ። ይህ ዕውቀት በጥንቱ ዘመን ተንሰራፍቶ የነበረ ሲሆን አብዛኞች ከባቢሎኒያኑ ኤኑማ ኤሊኒስ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ1816ኛው ክፍለ ዘመን መካከል የተጻፈ ጽሁፍ እንደተነሳ ያምናሉ። በዚህ ጽሁፍ መሰረት የሁሉ ነገር መሰረቶች ፡ ባህር፣ ሰማይ፣ መሬትና ነፋስ ናቸው። ለዚህ ሌላ አምራጭ ያለው ፤ ስረመሰረት ስረምንጭ፡ የሚለው ቃል ነው ። ነገር ግን በ...
31611
መናፍቅ መናፍቅ መናፍቅ መናፍቅ ማለት ከፍሎ የሚያምን ሙሉ እምነት የሌለው ማለት ነው። በክርስትና ትምህርት የማያምን ሰው መናፍቅ አይባልም። ከሀዲ ወይም አህዛብ ይባላል እንጂ። 1 መጽሐፍ ቅዱስ አምላክ በአንድነት በሦስትነት ይኖራል እያለ አምላክ አንድ አካል ብቻ አለው የሚሉ መናፍቃን ይባላሉ፡፡ 2 መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ነው እያለ የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት የማይቀበሉ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ የአብ ልጅ ሳይሆን የአብ ፍጡር ነው የሚሉት መናፍቃን ይባላሉ። 3 የእግዚአብሔር ቃል ሰው ለ...
31612
አነር አነር በሳይንሳዊ ስሙ Leptailurus serval የሚባል መካከለኛ ክብደት ያለው የዱር ድመት አይነት ነው። አነር ከኢትዮጵያ በተጨማሪ በተለያዩ የአፍሪካ አገራት ይገኛል። አነር፣ አነስተኛ ከሆኑት የድመት አስተኔ አባሎች ሁሉ እግሩ የረዘመ፣ አንጻራዊ ከፍታ ያለው ነው። የሚገኘው በአፍሪቃ ብቻ ነው። ክብደቱ 13 ኪግ ገደማ ሲሆን፣ የሴቷ ደግሞ 11 ኪግ ገደማ ነው። ቀጠን ብሎ አንገቱ ረዘም ያለ፣ ጭራው መካከለኛ ርዝመት ያለው ነው። አንገቱ፣ ትከሻው፣ እግሮቹና ጭራው ጥቋቋር መስመሮች አላቸው። ት...
31613
ሉጋልአኔሙንዱ ሉጋልአኔሙንዱ ሉጋልአኔሙንዱ 22ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ ገደማ በሱመር የአዳብ ከተማአገር ንጉሥ ሉጋል ነበረ። በሱመራዊ ነገሥታት ዝርዝር ዘንድ፣ የዑር ንጉሥ መስኪአጝናና ከተሸነፈ በኋላ፣ የሱመር ላዕላይነት ወደ አዳብ ተዛውሮ ሉጋልአኔሙንዱ ለ90 አመታት እንደ ነገሠ ይላል። በተለይ የሚታወቀው በኋላ ዘመን በተቀረጸው ጽላት ቅጂ ነው። የርሱ መንግሥት በመሞቱ ተከፋፈለ። በነገሥታት ዝርዝሩ መሰረት፣ ላዕላይነቱ «ቅዱስ ከተማው» ኒፑር የሰጠው መጀመርያ ወደ ማሪ ከተማ ሥርወ መንግሥት ተዛወረ። ...
31614
ሐረ ሼይጣን ሐረ ሼይጣን ሐይቁ ከኢትዮጵያ ተፈጥሯዊ የቱሪስት መስህቦች አንዱ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ የሐይቁ ይዘት አስገራሚ ሁኔታዎች አሉበት፡ ሐይቁ የሚገኘው ከመሬት ንጣፍ በታች ሲሆን፣ የተለያዩ ተፈጥሯዊ ሀብቶችና ገጽታዎች እንዲሁም ክስተቶችን የያዘ ሐይቅ ነው፡፡ በመሆኑም የገበቴ ቅርጽ ያለውን ሐይቅ ከጉድጓዱ አፋፍ አንስቶ ቁልቁል ውኃው እስካለበት ለመድረስ በአማካይ የ ፪፻፷ ሜትር ርቀት ጉዞ ይጠይቃል፡፡ በሌላ አገላለጽ ከአፋፉ እስከ ውኃው ያለው አምዳዊ Vertical ርቀት አማካይ ከፍታ ፻፱ ሜትር ነ...